TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63K photos
1.61K videos
216 files
4.38K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Mekelle

የኢትዮ ቴሌኮም ሰራተኞች ዛሬ ወደ መቐለ መጓዛቸውን ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ (የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ) ለቪኦኤ ተናግረዋል።

በመቐለ ያሉት የኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎት መስጫ እቃዎች ማከማቻ ላይ ጉዳት መድረሱንና ይህም እንደሚጠገን አሳውቀዋል።

ከቴሌ ታውሮች ጋር የሚያገናኙ በርካታ የፋይበር ኬብሎችም ተቆርጠዋል ይህም ይጠገናል ብለዋል ወ/ሪት ፍሬህይወት።

የመቐለ ከተማን ጨምሮ በመላው ትግራይ ክልል የቴሌኮም አገልግሎት ለማስጀመር በመቐለ ያለው (core site) ጉዳት መጠን መለይት አለበት ፤ ጉዳቱ ከፍተኛ ከሆነ አገልግሎቱን ለመመለስ 'ረጅም ጊዜ' ሊወስድ እንደሚችል ተናግረዋል።

በሌላ በኩል #ሽረ አካባቢ ያለ ፋይበር ኦብቲክ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል ፤ ጉዳቱ ረጅም ኪሎ ሜትር ስለሆነ ጥገናው እስካሁን #እንዳልተጠናቀቀ ወይዘሪት ፍሬህይወት ለቪኦኤ ራድዮ ጣቢያ ገልፀዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ለረጅም ጊዜ ኤሌክትሪክ ኃይል ተቋርጦባት የቆየችው ላሊበላ ከተማ ዛሬ እንደገና የኤሌክትሪክ ኃይል እንዳገኘች የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አሳውቋል። ከላሊበላ ከተማ በተጨማሪ ላስታ ወረዳና ሙጃ ከተማ ኤሌክትሪክ እንዳገኙ ተገልጿል። እነዚህን አካባቢዎች መልሰው ኃይል ያገኙት በጦርነቱ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት የአላማጣ - ላሊበላ የ66 ኬ.ቮ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ…
#Update

" የሁመራና ወልቃይት ከተሞች #በአጭር_ጊዜ የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲያኙ ይሰራል ። " - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል

የሁመራ - ወልቃይት - ሽሬ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር እየተጠገነ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዛሬ ገልጿል።

በጦርነት የወደሙ መሰረተ ልማቶችን ለመጠገን ስራዎች እየተሰሩ ሲሆን ስራዎቹን በአጭር ጊዜ አጠናቆ ህብረተሰቡ #ብርሃን እንዲያገኝ ለማድረግ ርብርብ እየተደረገ ነው ብሏል።

#የሁመራ - #ወልቃይት - #ሽረ የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች እና የማከፋፈያ ጣቢያ የፍተሻና የጥገና ሥራ እየተከናወነ እንደሚገኝ የገለፀው ተቋሙ " ከሁመራ እስከ ሽሬ ባለው ባለ 230 ኪሎ ቮልት ከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር በተደረገው የፍተሻና ጥገና ሥራ 67 ቦታዎች ላይ የኮንዳክተር እንዲሁም 3 ቦታዎች ላይ የፋይበር ኦፕቲክስ መቆራረጥ አጋጥሟል። " ብሏል።

የሁመራና ወልቃይት ከተሞች እና አካባቢያቸው ለረጅም ጊዜ ያህል ኃይል ተቋርጦ የቆየ በመሆኑ #በአጭር_ጊዜ የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲያኙ ይሰራል ሲል አክሏል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል

@tikvahethiopia
👍694🕊87👎3225🙏17😱6😢5
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " በሁለት ሶስት ቀን ውስጥ ሽረ ላይ ስብሰባ ይደረጋል ፤ በአንዳንድ ቴክኒካል ጉዳዮች ዘሪያ የሁለቱም ጦር ተወካዮች ተገናኝተው ይወያያሉ " ትላንት በኢትዮጵያ መንግስት እና በህወሓት መካከል የተካሄደውን የሰላም ድርድር / ስምምነቱን የመሩት የቀድሞው የናይጄሪያው ፕሬዜዳንት የአሁኑ የአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሊሴንጉን ኦባሳንጆ የትግራይ መዲና ፤ #መቐለ መግባታቸው…
#Update #ሽረ

የኢፌዴሪ መንግስት ኮሚኒኬሽን ፤ የትግራይ ታጣቂዎች ትጥቅ የሚፈቱበትን ዝርዝር ዕቅድ የሚሠራው የባለሞያዎች የጋራ ኮሚቴ ሽረ ላይ እየመከረ መሆኑን አሳውቋል።

" በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መሠረት ሕወሓት ትጥቅ የሚፈታበትን ዝርዝር ዕቅድ የሚያዘጋጀው የባለሞያዎች የጋራ ኮሚቴ ከትናንት ሕዳር 21 ቀን ጀምሮ ሽረ ላይ ሥራውን ጀምሯል " ያለው የኮሚኒኬሽን አገልግሎት ፤ " ከፌዴራል መንግሥትና ከትግራይ ታጣቂዎች የተውጣጣው የባለሞያዎች የጋራ ኮሚቴ በቀጣይ ጥቂት ቀናት ሥራውን ያጠናቅቃል ተብሎ ይታመናል " ብሏል።

ኮሚቴው የሚያወጣው ዝርዝር ዕቅድ ትጥቅ የማስፈታት፣ ካምፕ የማስገባትና ተያያዥ ጉዳዮችን የሚመልስ እንደሚሆንም ተመላክቷል።

የኢፌዴሪ መንግስት ኮሚኒኬሽ ፤ ዝርዝር ዕቅዱን የማውጣት ተግባሩ፣ በቴክኒክ ጉዳዮች ምክንያት መዘግየቱን ገልጿል።

ፎቶ ፦ ፋይል

@tikvahethiopia
👍543🕊72👎5922🙏13
#ሽረ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሰኞ ታህሳስ 24 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ሽረ ከተማ በቀን አንድ በረራ ማድረግ እንደሚጀምር ዛሬ ገልጿል።

አየር መንገዱ ፤ ወደ መቐለ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ በቀን ወደ ሶስት ከፍ የሚያደርግ መሆኑንም አሳውቋል።

በተከታታይም የመንገደኛ ፍላጎት ቁጥርን ከግምት ውስጥ በማስገባት በቀን የሚያደርገውን የበረራ ምልልስ ብዛት እንደሚጨምርም ገልጿል።

አየር መንገዱ ደንበኞቹ ባሉበት ቦታ ሆነው ባድረ ገፀ እና የተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪያ ተጠቅመው ምዝገባ ማድረግና ትኬት መቁረጥ ይችላሉ ተብሏል።

www.ethiopianairlines.com
bit.ly/ET-android-app
bit.ly/ET-iOS-App

#የኢትዮጵያአየርመንገድ

@tikvahethiopia
👍801🕊18072🙏50😱26😢13🥰11👎1