TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63K photos
1.61K videos
216 files
4.38K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Mekelle

የኢትዮ ቴሌኮም ሰራተኞች ዛሬ ወደ መቐለ መጓዛቸውን ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ (የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ) ለቪኦኤ ተናግረዋል።

በመቐለ ያሉት የኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎት መስጫ እቃዎች ማከማቻ ላይ ጉዳት መድረሱንና ይህም እንደሚጠገን አሳውቀዋል።

ከቴሌ ታውሮች ጋር የሚያገናኙ በርካታ የፋይበር ኬብሎችም ተቆርጠዋል ይህም ይጠገናል ብለዋል ወ/ሪት ፍሬህይወት።

የመቐለ ከተማን ጨምሮ በመላው ትግራይ ክልል የቴሌኮም አገልግሎት ለማስጀመር በመቐለ ያለው (core site) ጉዳት መጠን መለይት አለበት ፤ ጉዳቱ ከፍተኛ ከሆነ አገልግሎቱን ለመመለስ 'ረጅም ጊዜ' ሊወስድ እንደሚችል ተናግረዋል።

በሌላ በኩል #ሽረ አካባቢ ያለ ፋይበር ኦብቲክ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል ፤ ጉዳቱ ረጅም ኪሎ ሜትር ስለሆነ ጥገናው እስካሁን #እንዳልተጠናቀቀ ወይዘሪት ፍሬህይወት ለቪኦኤ ራድዮ ጣቢያ ገልፀዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia