TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.62K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#CustomsCommission " ትልቁ ስህተት የተፈጠረው የጉምሩክ ኮሚሽን 'በርቀትና ኤክስቴንሽን የተመረቃችሁ ተወዳዳሪዎች አትካተቱም' ማለቱ ነው "  - ቅሬታ አቅራቢ አመልካቾች ➡️ " የማጣራት ሂደቶች መደረጋቸው አይቀርም። ማንኛውም የቅጥር ማስታወቂያ ሲወጣ ሁሉም የተመዘገበው ያልፋል ማለት አይደለም " - ጉምሩክ ኮሚሽን የጉምሩክ ኮሚሽን ለሥራ ቅጥር ከ2,000 በላይ ሥራ ፈላጊዎችን ክልሎችና…
#Update
#CustomsCommission

" ኮሚሽኑ በመደበኛው የትምህርት መርሃ ግብር የተማሩትን አመልካቾች ብቻ ወደ ቀጣዩ የቅጥር ሂደት መግባት የሚችሉብትን ሁኔታ ውሳኔ አሳልፏል " - ጉምሩክ ኮሚሽን

የጉምሩክ ኮሚሽን ባወጣው የቅጥር ማስታወቂያ ከ200ዐ በላይ ተወዳዳሪዎችን እንዲመለምሉ ለክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች በሰጠው ኮታ መሰረት የተመለመሉ አመልካቾች ዝርዝር ከተላከለት በኋላ በኢ-መደበኛው መርሃ ግብር የተመረቅነውን " ኮሚሽኑ በቅጥሩ 'አትካተቱም' አለን " የሚል ቅሬታ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አቅርበው ነው።

ይህ ቅሬታ ያላቸው የተሰባሰቡት ብቻ ወደ 300 እንደሆኑ የገለጹ ሲሆን፣ ለምን ይህን እንዳደረገ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ የቀረበለት ጉምሩክ ኮሚሽን ጉዳዩን አጣርቶ ምላሽ ሊሰጥ ቀጠሮ ሰጥቶን ነበር፡፡

ኮሚሽኑ ለቀረበበት ቅሬታ ምን መለሰ ?

የኮሚሽኑ የኮሚዩኒኬሽን ዳሬክተር አቶ ዘሪሁን አሰፋ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ፣ " ኮሚሽኑ በመደበኛው የትምህርት መርሃ ግብር የተማሩት አመልካቾች ብቻ ወደ ቀጣዩ የቅጥር ሂደት መግባት የሚችሉበትን ሁኔታ ውሳኔ አሳልፏል። በመደበኛው የትምህርት መርሃ ግብር ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ናቸው በዚህኛው ቅጥር የተጋበዙት " ብለዋል።

ማስታወቂያው የመንግስት ዩኒቨርሲቲ፣ በግል ኮሌጆች ተመርቀው ትምህርት ሚኒስቴር ያረጋገጠላቸው ምሩቃን መወዳዳር እደሚችሉ በሚገልጸው መሰረት ካመለከቱ በኋላ " አትካተቱም " እንደተባሉና አሰራሩ ልክ እንዳልሆነ ነው አመልካቾቹ የገለጹት፤ ለዚህ ያላችሁ ምላሽ ምንድን ነው ? ስንል አቶ ዘሪሁንን ጠይቀናቸዋል፡፡

እሳቸውም፣ " ማስታወቂያ ላይ ዝርዝር ጉዳዮች ላይጠቀሱ ይችላሉ " ብለው፣ " ሌሎችን ዲቴይል መስፈርቶችን ኮሚሽኑ በኋላ ላይ ማጣራት አድርጎ ሁሉም ተመሳሳይ አካባቢ በመደበኛና ኤክስቴሽን የተማሩትን፣ ሌሎችን ደግሞ በሌላ መስፈርት ሳይሆን ለሁሉም ወጥ የሆነ ውሳኔ ነው የወሰነው " ብለዋል፡፡

ቲክቫህ ኢትዮጵያም ማስታውቂያው ወጥቶ ተወዳዳሪዎች ካመለከቱ በኋላ ኮሚሽኑ ይህን መወሰኑ ለምንድን ነው ? የገጠማችሁ ችግር ምንድን ነው ? በኢ-መደበኛው መርሃ ግብር የተመረቁት በቅጥሩ የማይካተቱ ከሆነስ ለምን ቀድማችሁ አላሳወቃችሁም ? የሚል ተጨማሪ ጥያቄ አቅርቧል፡፡

አቶ ዘሪሁን፣ " ኮሚሽኑ በኋላ ላይ አጠቃለይ የምልመላ ሂደት ይህን ብቻ ሳይሆን ሌሎች የማጣራት ሂደቶችን አድርጎ ካሉ ዝርዝሮች ውስጥ እነዚህ ወደቀጣዩ ዙር የምልመላ ሂደት ይለፉ ብሎ የወሰነው ወደ ቀጣይ ዙርም የተገባበት ሁኔታ አለ፡፡ ይህን ነው ልገልጽ የምችለው " ሲሉ አስረድተዋል።

ፕሮግራሙ ቢለያይም በሀገሪቱ ተመሳሳይ ይዘት ያለው ትምህርት ነው የሚሰጠው ስለዚህ መደበኛውን ብቻ ለይቶ ለመቅጠር ህጉ ይፈቅዳል ? ሁሉንም ምሩቃን ማካተት አልነበረባችሁም ? ለሚለው ጥያቄም፤ " ኮሚሽኑ ያስቀመጠው አሰራር ነው፡፡ መደበኛዎቹን ነው በዚህ የቅጥር ሂደት ውስጥ የማካትተው የሚል መስፈርት ወጥቶ ውሳኔ ተሰጥቶበት እየተሰራ ያለ ጉዳይ ነው " የሚል ምላሽ ተሰጥቷል፡፡

በሌላ በኩል፣ በክልሎች በኩል የነበረው የምልመላ ሂደት " በቢሮዎች ዘመድ ላላቸው ቅድሚያ እየተሰጠ ዘመድ የሌላቸው ከመንከራተታቸውም በላይ እድሉን እንዳላገኙ "፣ በአዲስ አበባ ያለው ምልመላም ኦፊሻል ወጥቶ እንዳልተመለከቱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታ ያደረሱ እንዳሉ በመግለጽ፤ ለዚሁ ቅሬታ ጉምሩክ ኮሚሽንን ምላሽ ጠይቀናል፡፡

አቶ ዘሪሁን " ቅሬታዎች የሉም ማለት አይደለም፤ እኛ ጋርም የመጡ ቅሬታዎች ነበሩ፤ ከተቀመጠው መስፈርት አንጻርም ይሁን በግለሰብ 'በዚህ ቀን ተመዝግበን፤ እኔ ማለፍ ሲገባኝ እከሌ/እከሊት ያላግባብ አልፋለች/ፏል' የሚል ቅሬታ አለ " ብለው፤ ፍትሃዊ እንዲሆን ጉዳዩን ወደ ክልል መልሶ ኮሚሽኑ ማጣራት እያደረገ ምላሽ እየሰጠ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ቅሬታ ያላቸው በክልል በኩል አጽፈው ቅሬታቸውን ቢያቀርቡ ኮሚሽኑ አጣርቶ ማስተካከያ የማያደርግበት ምክንያት እንደማይኖር፣ በዚሁ መሰረትም ምላሽ የተሰጣቸውና በሂደት ላይ ያሉም እንዳሉ ገልጸዋል፡፡

የአዲስ አበባውን ቅሬታ በተመለከተ በሰጡት ምላሽ አመልካቾች ተመልምለው እንደተላኩላቸው ተናግረው፣ " አይደለም አዲስ አበባ በሁሉም ወረዳዎች ተደራሽ መደረጉን ኮሚሽኑ ክትትል ሲያደርግ ነበር " ብለዋል፡፡

በዚህ የቅጥር ማስታወቂያ መሰረት ኮሚሽኑ የሚፈገውን ያህል የሰው ኃይል እንዳገኘና አመልካቾቹ በቀጣይ ስልጠና ወስደው ወደ ስራ የሚገቡበት እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን የገለጹት አቶ ዘሪሁን፣ በአጠቃላይ ምን ያክል ሰዎች አመልክተው እንደነበር ስንጠይቃቸው ለጊዜው ዳታውን እንዳልያዙና መግለጹ አስፈላጊ እንዳልሆነ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል፡፡

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
1.17K😡172😭61🙏46💔37🤔21👏17😢14🕊13🥰12😱7