#እናትፓርቲ #ምርጫቦርድ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ " እናት ፓርቲ በአዋጅ እና በመመሪያ ከተደነገገው ውጭ የፋይናንስ አስተዳደሩን እየመራ እና እያስተዳደረ ይገኛል " በማለት በዚህ አመት የሚሰጠውን የመንግስት የፋይናንስ ድጋፍ ሊያገኝ አይገባውም ሲል ውሳኔ አሳልፏል።
ከዚህ በተጨማሪ የፖርቲውን የባንክ ሒሳብ ወጪ ሆኖ ከታለመለት አላማ ውጪ የመንግስት ድጋፍ ገንዘብ እንዲውል አድርገዋል ባላቸው ሒሳቡን በጣምራ የሚያንቀሳቅሱት የፓርቲው አመራሮች ፦
- ዶ/ር ሰይፈሥሰላሴ አያሌው የፓርቲው ፕሬዚደንት፤
- ወ/ሪት ሜሮን ታደለ የፓርቲው ዋና ፀሐፊ
- ወ/ሪት ኩሪ አሠፋ የፓርቲው የሂሳብ ክፍል ኃላፊ ላይ የፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ ተገቢውን ምርመራ እንዲያደርግ የወሰነ መሆኑን ቦርዱ አሳውቋል።
ቦርዱ ተገኙ ያላቸው የፋይናንስ ግኝቶች ምንድናቸው ?
እናት ፖርቲ ከመንግስት ስለአገኘው የ2016 የበጀት ድጋፍ ሂሳቡን በራሱ የውጭ ኦዲተር አሰርቶ ሪፖርት ለቦርዱ ማቅረቡን አመልክቷል።
በፖርቲው የተሰየመው የውጭ ኦዲተር በኦዲት ሪፖርቱ ላይ ፦
➡ ፓርቲው ከአባላት ለሰበሰበው መዋጮ የገንዘብ መቀበያ ደረሰኝ ያለመስጠቱን በዚህ ምክንያት በሶስት ባንኮች ላይ የሚገኘውን 65,315ብር ትክክለኛነት ማረጋገጥ አለመቻሉን፤
➡ ለቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ወጪ የሆኑ ገንዘቦች ህጋዊ በሆኑ የወጪ ደረሰኞች አለማስደገፉን ፤
➡ ፓርቲው ለዕርዳታ በሚል ወጪ አድርጎ ብር 158,425 መክፈሉን ይገልጻል።
ቦርዱ ከላይ የተገለፁት ግኝቶች ከውጭ ኦዲተሩ ሲቀርብለት እንዲሁም የፓርቲው አባላት ጥቅምት 3/2017 ዓ/ም በተጻፈ አቤቱታ የፓርቲው ፋይናንስ አስተዳደር ችግር ላይመሆኑን ጠቅሰው ተገቢው ማጣራት በቦርዱ እንዲደረግ በመጠየቃቸው ጉዳዩን የፌደራል ዋና አዲተር መ/ቤት እንዲያየው ማድረጉን አስረድቷል።
የፓርቲው አባላት ያቀረቧቸውን ቅሬታዎች እና የፓርቲው የውጭ ኦዲተር የዘረዘሯቸውን ግኝቶች የያዘውን የኦዲት ሪፖርት ለፌደራል ዋና ኦዲተር በመላክ ፓርቲው ከመንግስት ያገኘውን ድጋፍ ለታለመለት ዓላማ መዋል /አለመዋሉን አጣርቶ እንዲገልጽ መጠየቁን አመልክቷል።
የፌደራል ዋና ኦዲተር መ/ቤትም የፓርቲውን የመንግስት በጀት ድጋፍ ኦዲት አድርጎ ውጤቱ እንዳሳወቀው ገልጿል።
በዋና ኦዲተር የኦዲት ሪፖርቱ ላይ የታዩት ግኝቶች በዋናነት ምንድናቸው ?
🔴 ፓርቲው በአዋጅ እና በመመሪያ ከመንግስት የተሰጠውን የበጀት ድጋፍ በተለየ የሒሳብ መዝገብ በየወጪ አርእስቱ ዘርዝሮ መያዝ እንዳለበት ቢደነግግም የሒሳብ መዝገብ እንደሌለው፤ የሒሳብ ማመዛዘኛ ሪፖርት እና የባንክ ሂሳብ ማስታረቂያ እንዳላዘጋጀ እንዲሁም ከቦርዱ የተሰጠውን ድጋፍ ወጪ ሲያደርግ በተለየ የሂሳብ መዝገብ በየወጪ አርእስቱ ዘርዝሮ ሳይዝ የተፈፀመ መሆኑን ይገልጻል።
🔴 ለማህበራዊ አገልግሎት በሚል ፖርቲው ከመንግስት ያገኘውን የበጀት ድጋፍን ከታለመለት ተግባር ውጪ አውሎ እንደተገኘ ይኸውም፦
• በጎፋ ዞን ለተከሰተው የመሬት መንሸራተት እርዳታ እንዲውል ሐምሌ 25/2016ዓ/ም በወጪ ማዘዣ 000098 ብር 20ሺ ማውጣቱን፤
• ለአቶ ዳዊት ብርሀኑ መሸኛ የሚውል መስከረም 18/2017ዓ/ም በወጪ ማዘዣ 000121 15 ሺ ወጪ ማድረጉን፤
• ለአቶ ተመስገን ሹመት የሐዘን በሚል ሐምሌ 25/2016ዓ/ም በወጪ ማዘዣ 000044 3,500ብር ወጪ ማድረጉን በድምሩ 38,500 ብር ከታለመለት አላማ እና ተግባር ውጪ ያወጣ መሆኑን ይገልጻል።
🔴 በተለያዩ ጊዜያት ለ13 ቅ/ጽ/ቤቶች በባንክ ቤት በኩል በዝውውር የላከው ብር 438,500ብር ለምን ተግባር እንደዋለ የወጪ ደጋፊ ሰነድ ተያይዞ ያልቀረበ መሆኑን ይህንንም ግኝት በተመለከተ የፖርቲው ፕሬዚደንት ሲጠየቁ የሰጡት መልስ አሳማኝ ያለመሆኑን ገልጿል።
በዚህም ምርጫ ቦርድ ፓርቲው ከመንግስት የተመደበለትን ድጋፍ ከታለመለት አላማ ውጭ እንዳዋለው መገንዘቡን አሳውቋል።
በዚሀ አመት የሚሰጠውን የመንግስት ድጋፍ ሊያገኝ አይገባውም ሲልም ወስኗል።
የፓርቲውን ባንክ ሒሳብ በጣምራ ሚያንቀሳቅሱት የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች ላይ የፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ ምርመራ እንዲያደርግ የወሰነ መሆኑን ይፋ አድርጓል።
(የእናት ፓርቲ ምላሽ በቀጣይ ይቀርባል)
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia

😡393❤110🤔24👏19😭13🙏10🕊7😱6😢6🥰1
TIKVAH-ETHIOPIA
#እናትፓርቲ #ምርጫቦርድ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ " እናት ፓርቲ በአዋጅ እና በመመሪያ ከተደነገገው ውጭ የፋይናንስ አስተዳደሩን እየመራ እና እያስተዳደረ ይገኛል " በማለት በዚህ አመት የሚሰጠውን የመንግስት የፋይናንስ ድጋፍ ሊያገኝ አይገባውም ሲል ውሳኔ አሳልፏል። ከዚህ በተጨማሪ የፖርቲውን የባንክ ሒሳብ ወጪ ሆኖ ከታለመለት አላማ ውጪ የመንግስት ድጋፍ ገንዘብ እንዲውል አድርገዋል ባላቸው ሒሳቡን…
#እናትፓርቲ
" በጀት በመከልከልና በማስከልከል የሚደናቀፍ ትግል አይኖርም ! " - እናት ፓርቲ
እናት ፓርቲ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በፓርቲው ላይ ያሳለፈውን የበጀት ክልከላ " ፖለቲካዊ ውሳኔ " ሲል ጠርቶት አውግዟል።
" በጀት በመከልከልና በማስከልከል የሚደናቀፍ ትግል የለም "ም ብሏል።
እናት ፓርቲ ምን አለ ?
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለፌዴራል ዋና ኦዲተር በጻፈው እና ለፓርቲው ግልባጭ በተደረገ ደብዳቤ የፌዴራል ዋና ኦዲተር ለፓርቲው በ2016 ዓ.ም የተሰጠን ድጋፍ ብር 1,702,561.65 (አንድ ሚሊዮን ሰባት መቶ ኹለት ሺህ አምስት መቶ ስድሳ አንድ ከ65/100) ኦዲት ማድረጉን አመልክቷል።
የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት በቀጥታ የኦዲት ሪፖርቱን ለኦዲት ተደራጊ እናት ፓርቲ እንዳላደረሰና ሪፖርቱ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በኩል ፓርቲው ጋር መምጣቱን ገልጿል።
የኦዲት ግኝት ተብሎ በዋነኛነት የቀረበውና ትልቅ ጥያቄ ያስነሳው ፓርቲያው ከተደረገለት ድጋፍ ፦
- በጎፋ ዞን ለተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር) መለገሱ ፤
- ለአንድ የፓርቲው ብሔራዊ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ስንብት ለማስታወሻ ብር 15,000.00 (አሥራ አምስት ሺህ ብር) ወጪ ማድረጉ፤
- የፓርቲያው የላዕላይ ምክር ቤት አባል ከዚኽ ዓለም በሞት በተለዩበት ወቅት ለባነር ማሠሪያ የወጣ ብር 3,500.00 (ሦስት ሺህ አምስት መቶ ብር) በድምሩ ፓርቲው ብር 38,500.00 (ሠላሳ ስምንት ሺህ አምስት መቶ ብር) " ከታለመለት ዓላማ እና ተግባር ውጭ ያወጣ መኾኑ" መመላከቱን አስረድቷል።
በዚህም ምክንያት ቦርዱ በዚህ ዓመት ፓርቲው የሚሰጠውን የመንግሥት ድጋፍ ሊያገኝ እንደማይገባ መወሰኑን ፤ የፓርቲውን ሂሳብ በጣምራ በሚያንቀሳቅሱት 3 አመራሮች ላይ ፌዴራል ፖሊስ ምርመራ እንዲያደርግ መወሰኑን በደብዳቤ እንደገለጸለት ጠቅሷል።
እናት ፓርቲ የቦርዱ ውሳኔ " አላግባብ ወጣ " ስለሚለው 38,500.00 ብር ሳይሆን ከጀርባው ሌላ ጉዳይ እንዳለው እገምታለሁ ብሏል።
" አላግባብ ወጣ " የተባለው ወጪ ፦
➡ ብር 20,000 የመሬት መንሸራተት ለደረሰባቸው ወገኖች የወጣ እጅግ አነስተኛ ገንዘብ መሆኑና ይህም የነገ መራጮቹን ጎን ለሚጠይቀው የስብዕና ሞራል መቆም ከማስፈለጉ አኳያ ሊደረግ ከሚችል በጣም አነስተኛው ነገር እንደሆነ፤
➡ ምንም ክፍያ ሳይከፈላቸው ለሀገራቸውና ሕዝባቸው ለመታገል ጊዜያቸውንና መላ እነሱነታቸውን ሰጥተው ለአደጋ ጭምር ራሳቸውን አጋልጠው የመጓጓዣ ወጪያቸው እንኳን ሳይሸፈን ለሀገር ከመቆም አኳያ በፓርቲው ከፍተኛ አመራርነት ያገለገሉ ከፓርቲው በሞት እንዲኹም በአካል ሲለዩ ወጣ የተባለው ወጪ እዚህ ግባ የማይባል መሆኑንና ከአግባብ ውጭ የወጣ ነው ብሎ እንደማያምን ገልጿል።
ከፓርቲው አመራር ቀብር ጋር ከተያያዘው ብር 3,500 ውጪ ሌሎቹ የተፈጸሙት ወጪዎች በፓርቲው ብሔራዊ ሥራ አስፈጻሚና መላ መዋቅሩ ውሳኔ መሠረት እንደሆነ ጠቁሟል።
ይህ ሆኖ ሳለ " አመራሮችን በተለየ መልኩ ተጠያቂ ለማድረግ የተኬደበት ርቀት ትናንት የፓርቲ አመራሮችና አባላት እሥርና አፈና ሲገጥማቸው ባሉበት ድረስ በመሄድ ያጽናና እና ለማስፈታት ግብ ግብ ይገጥም የነበረ ቦርድ በቅጽበት እንዲህ የመውጊያ ስለት አቀባይ ወደመሆን ያሽቆለቆለበት ቅጽበት ያስገርማል፣ ያሳዝናልም። የኢትዮጵያ ሕዝብም ይመዘግባል " ብሏል።
የተጠቀሰው ገንዘብ ፓርቲው በድጋፍ ከተሰጠው ገንዘብ ወጪ እንዲደረግ ያስገደደው ምክንያት በወቅቱ ፓርቲው ለማኅበራዊ አገልግሎት የሚጠቀምበትና ከአባላትና ደጋፊዎች የሚሰበሰብ ገንዘብ ከተቀመጠበት የባንክ ሒሳብ ማንቀሳቀስ ባለመቻሉና ገንዘቡ በወቅቱ ወጪ መደረግ የግድ ስለነበረ እንደሆነ አመልክቷል።
ነገር ግን የማኅበራዊ አገልግሎት የባንክ ሂሣቡን ማንቀሳቀስ በቻለበት በአሁኑ ሰዓት ግን የተጠቀሰውን በውንጀላ የተያዘበትን ገንዘብ ብር 38,500 አዛውሮ ዝግጁ ያደረገና ለመመለስም የሚችል መሆኑን ለፌዴራል ዋና ኦዲተር በፈረመው መተማመኛ ጽሑፍ መስጠቱን ገልጿል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ፓርቲው ጉዳዩን ቀለል አድርጎ ወደሥራው ባተኮረበት ወቅት ከዚህ ቀደም ' ፓርቲውን ከመፍረስ ለመታደግ በሚል ከፓርቲው የተቆረጠ ኃይል " ፓርቲውን በጀት አስከለከልኩ" ፣ " እነ እከሌንና እከሊትን ላሳስር ነው " እያለ ለተለያዩ ግለሰቦችና ሚዲያ አካላት ወሬ እየነዛ መመልከቱን በዚህም " በሬ ከአራጁ " ለማለት መገደዱን ገልጿል።
ይህን አካል ከነዝርዝር ማንነቱ በቅርቡ ለሕዝብ ይፋ እንደሚያደርግም ጠቁሟል።
ፓርቲው የመንግሥትን ሥልጣን በሕጋዊና ሰላማዊ መንገድ ለመጨበጥ እንደሚሰራ ገልጾ የገንዘብ አጠቃቀምን በተመለከተ እያንዳንዷ ሳንቲም ተጠያቂነት ባለው መልኩ ብቻ መውጣት እንዳለባት እንደሚያምን ለዚህም ተግቶ እንደሚሰራ ፤ ኦዲት መደረጉም እንደሚያስደስተው ገልጿል።
ነገር ግን የኦዲት ግኝት ተብሎ ነቀረበውና ቦርዱ ያሳለፈው ውሳኔ ከአስተዳደራዊ ውሳኔነቱ ይልቅ ፖለቲካዊ ግብ ያዘለ ነው ብሎ እንደሚያምን አመልክቷል።
" በቦርዱ ውሳኔ ላይ ዕለት ከዕለት የሚያስጨንቀንና ዘወትር የምንጮኽለት ወዲኽም ግራ ቀኝ ጥርስ ያስነከሰብን የሕዝባችን ስቃይ ከቀለለና ጊዜ ከተረፈን እንደአስፈላጊነቱ ሕጋዊ መንገድ ተከትለን ይግባኝ እንልበት ይሆናል " ብሏል።
ፓርቲው አለኝ ባለው መረጃ እንዳይሰጠው የታገደው የ2017 የበጀት ድጋፍ ብር 600 ሺህ ገደማ መሆኑን ጠቁሟል።
" በጀት በመከልከልና በማስከልከል የሚደናቀፍ ትግል አይኖርም " ሲልም አሳውቋል።

❤542😡60👏53🙏31🕊17😭11🤔10😱1😢1