TIKVAH-ETHIOPIA
#TPLF : ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህ.ወ.ሓ.ት) ጠቅላላ ጉባዔውን እንዲያደርግ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አሳስቧል። ምርጫ ቦርድ ፤ ህወሓት በኢትዮጵያ የምርጫ የፖለቲካ ፖርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነምግባር አዋጅን ለማሻሻል በወጣው አዋጅ ቁጥር መሠረት በልዩ ሁኔታ መመዝገቡን አስታውሷል። ፖርቲው ከተመዘገበበት ቀን ጀምሮ ባሉት ስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ የፓርቲውን ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያደርግ…
#TPLF
" የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ የተናጠል ውሳኔን ዛሬ ይሁን ነገ አልቀበልም " - በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር ) የሚመራው ህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ
በደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ ከጥር 5 እስከ ጥር 7 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በወቅታዊ የክልሉ ሁኔታ ላይ አተኩሮ ስብሰባ ተቀምጦ ነበር።
ይህንን ተከትሎ ዛሬ ምሽት መግለጫ አውጥቷል።
በዚህም ቡድኑ ፦
- እስከ አሁን ያልተረጋገጠው የትግራይ ግዛታዊ አንድነት፤
- ተፈናቃዮች እና ስደተኞች ወደ ቄያቸው አለመመለስ፤
- የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ ያወጣውን መግለጫ፤
- የፕሪቶሪያ የሰላም ውል አፈፃፀም በሚሉ አጀንዳዎች ላይ መወያየቱን ገልጾ " ቀጣይ የመፍትሄ እና የትግል አቅጣጫ አስቀምጫለሁ " ብሏል።
የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ ባወጣው መግለጫ ፤ በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መሰረት የኢፌዴሪ ህገ-መንግስት እውቅና የሰጠው የትግራይ ግዛታዊ አንድነት አለመረጋገጡ ጠቅሶ " ተፈናቃይ እና ስደተኞች ወደ ቄያቸው ባለመመለሳቸው ሃዘን እና ቁጣ ተስምተኞናል ይህንን አስመልክቶ ' ይበቃል ' በሚል የተካሄደው ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ እደግፋለሁ " ብሏል።
ቡድኑ በመግለጫው " የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በአግባቡ እንዳይፈፀም የኢትዮጵያ መንግስት እንቅፋት እየሆነ ነው ፡ በትግራይ ውስጥ የበቀለ #ከሃዲ_ሃይልም በተጨማሪ ስምምነቱ እያደናቀፈ ነው " የሚል ክስ አሰምቷል።
እንዴት እንደሆነ ባያብራራም " ችግሩ ከስር መሰረቱ ለመለወጥ ቆርጬ ተነስቻለሁ " ብሏል።
በመሰረተ ሃሳብ ደረጃ DDR ተቀባይነት ያለው እንደሆነ የገለፀም ሲሆን " ይሁን እንጂ DDR እንደምክንያት በመጠቀም የትግራይ ሰራዊት ለማፍረስ እየተደረገ ያለው ሴራ ተቀባይነተ የለውም " ሲል ገልጿል።
የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ ህወሓት ህጋዊ ጉባኤ እንዲያካሂድ በማስመልከት በቅርቡ ያወጣው ቀን ገደብ ያካተተ መግለጫ አስመልክቶ በሰጠው ምላሽ ፥ " ቦርዱ ' ጉባኤ አካሂዱ ' የሚል ጨምሮ በተንኮል የተተበተቡ የተለያዩ ትእዛዞች ከመስጠት ተቆጥቦ የተፈጠሩ ልዩነቶች በፓለቲካዊ ውይይት ለመፍታት የተጀመረው ጥረት በማስቀጠሉ ላይ ያተኩር " ብሏል።
" ህወሓት ሁሌም ለሁለትዮሽ ውይይት ዝግጁ ነው ፤ የትግራይ ህዝብ ትግል እና መስዋእትነት የሚያራክስ የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ የተናጠል ውሳኔ ግን ዛሬ ይሁን ነገ አልቀበልም " ሲል አቋሙን አንጸባርቋል።
ህወሓት ጊዚያዊ አስተዳደሩ በማቋቋም የአንበሳ ድርሻ እንደነበረው እና እንዳለው የጠቀሰው መግለጫው " አሁንም እንዲጠናከር ይሰራል ይሁን እንጂ ጊዚያዊ አስተዳደሩ ለማጠናከር እና ለመቆጣጠር በሚል ይቋቋማል የሚባለው ካውንስል አካል መሆን አልፈግም " ሲል ግልፅ አድርጓል።
በሊቀመንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር ) የሚመራው ህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ በመግለጫው ማጠቃለያ ፤ " የኢትዮጵያ መንግስት ከጣልቃ ገብነት ተቆጥቦ የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በቅን ልቦና በመፈፀም ለዘላቂ ሰላም እንዲሰራ " የሚል ጥሪ አቅርበዋል።
የህወሓት ቡድን ለሁለት ተከፍሎ የለየለት አለመግባባት ውስጥ ከገባ ወራት የተቆጠሩ ሲሆን ከወራት በፊት ለሁለት የተከፈሉት አመራሮች እና የጊዜያዊ አስተዳደሩ አመራሮች አዲስ አበባ ሄደው ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ውይይት አድርገው ነበር።
ወደ መቐለ ከተመለሱ በኃላ ግን እስከ ዛሬ መግባባት ሳይፈጥሩ በመግላጫ ምልልስ ላይ ናቸው።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ደግሞ ህወሓት በልዩ ሁኔታ የተመዘገበው ነሀሴ 3 ቀን 2016 ዓ.ም መሆኑን በመግለጽ ጠቅላላ ጉባኤውን እስከ የካቲት 3 ቀን 2017 ዓ.ም እንዲያደርግ አሳስቧል።
ይህ በሕግ ፓርቲው ላይ የተጣለ ግዴታ በወቅቱ ሳይፈፀም ቢቀር ቦርዱ ሕጉን መሠረት በማድረግ ተገቢ ነው የሚለውን ውሳኔ የሚሰጥ መሆኑንም ገልጾ ነበር።
ከዚህ ቀደም የህወሓት አመራሮችን ለሁለት የከፈለ ጉባኤ መደረጉ አይዘነጋም። በወቅቱም ምርጫ ቦርድ ያልተገኘበትን እና ስርዓቱን ያልተከተለ ጠቅላላ ጉባኤ እውቅና እንደማይሰጥ ማስገንዘቡ ይታወሳል።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia

❤415😡157🕊79🙏44🤔38😢23😭20🥰19👏15😱15
TIKVAH-ETHIOPIA
#TPLF " የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ የተናጠል ውሳኔን ዛሬ ይሁን ነገ አልቀበልም " - በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር ) የሚመራው ህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ በደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ ከጥር 5 እስከ ጥር 7 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በወቅታዊ የክልሉ ሁኔታ ላይ አተኩሮ ስብሰባ ተቀምጦ ነበር። ይህንን ተከትሎ ዛሬ ምሽት መግለጫ አውጥቷል። በዚህም ቡድኑ…
#TPLF
በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ማዕከላዊ ዉጥጥር ኮሚሽን ፥ የኢትየጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ ትእዛዝ እና ውሳኔን አልቀበለውም / ተቀባይነት የለውም ብሏል።
" ቦርዱ ያሳተላለፈው ውሳኔ እና ትእዛዝ ህጋዊ መሰረት የሌለው ከፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት የሚጣረስ ነው " ሲል የገለጸው ኮሚሽኑ " ቦርዱ ትዕዛዝ እና ውሳኔ ከመስጠት እንዲቆጠብ " ሲልም ገልጿል።
የቁጥጥር ኮሚሽኑ " የኢትየጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ ጥር 10/2013 ዓ.ም ህወሓትን ከህጋዊ የፓለቲካ ፓርቲዎች ዝርዝር ሰርዞ ነበር ፤ ከፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በኋላ ግን ነሃሴ 3/2016 ዓ.ም ህጋዊነቱ ተመልሶለታል " ብለዋል።
" ህወሓት ከነሃሴ 3/2016 ዓ.ም ጀምሮ እንደ አዲስ የፓለቲካ ፓርቲ መመዝገቡ ተቀባይነት እንደሌለው ፓርቲው ወድያውኑ ገልፀዋል " ሲልም ጠቁሞ " ይሁን እንጂ ቦርዱ ፓርቲው ያቀረበውን 'የአልቀበልም" ምላሽ ጆሮ ዳባ ልበስ ማለቱ 'ልክ አይደለም ' " ሲል አብራርተዋል።
" የህወሓት ህጋዊነት በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መሰረት ሙሉ በሙሉ እንዲመለስ (Reinstate) እንዲደረግ እንጠይቃለን " ያለው ኮሚሽኑ ፤ " ከዚህ ውጭ ያለው ውሳኔ እና ትእዛዝ ተቀባይነት የለውም " ብሏል።
ከቀናት በፊትም የነ ደብረፅዮን (ዶ/ር) ቡድን ባወጣው መግለጫ " ለሁለትዮሽ ውይይት ዝግጁ ነኝ የምርጫ ቦርድን የተናጠል ውሳኔ ዛሬም ይሁን ነገ አልቀበልም " ማለቱ ይታወሳል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ህወሓት በሕጉ መሰረት ጠቅላላ ጉባኤውን እስከ የካቲት 3 ቀን 2017 ዓ.ም እንዲያደርግ አሳስቧል።
ይህ በሕግ ፓርቲው ላይ የተጣለ ግዴታ በወቅቱ ሳይፈፀም ቢቀር ቦርዱ ሕጉን መሠረት በማድረግ ተገቢ ነው የሚለውን ውሳኔ የሚሰጥ መሆኑንም ገልጿል።
ከዚህ ቀደም የህወሓት አመራሮችን ለሁለት የከፈለ ጉባኤ መደረጉ አይዘነጋም። በወቅቱም ምርጫ ቦርድ ያልተገኘበትን እና ስርዓቱን ያልተከተለ ጠቅላላ ጉባኤ እውቅና እንደማይሰጥ ማስገንዘቡ ይታወሳል።
@tikvahethiopia
በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ማዕከላዊ ዉጥጥር ኮሚሽን ፥ የኢትየጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ ትእዛዝ እና ውሳኔን አልቀበለውም / ተቀባይነት የለውም ብሏል።
" ቦርዱ ያሳተላለፈው ውሳኔ እና ትእዛዝ ህጋዊ መሰረት የሌለው ከፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት የሚጣረስ ነው " ሲል የገለጸው ኮሚሽኑ " ቦርዱ ትዕዛዝ እና ውሳኔ ከመስጠት እንዲቆጠብ " ሲልም ገልጿል።
የቁጥጥር ኮሚሽኑ " የኢትየጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ ጥር 10/2013 ዓ.ም ህወሓትን ከህጋዊ የፓለቲካ ፓርቲዎች ዝርዝር ሰርዞ ነበር ፤ ከፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በኋላ ግን ነሃሴ 3/2016 ዓ.ም ህጋዊነቱ ተመልሶለታል " ብለዋል።
" ህወሓት ከነሃሴ 3/2016 ዓ.ም ጀምሮ እንደ አዲስ የፓለቲካ ፓርቲ መመዝገቡ ተቀባይነት እንደሌለው ፓርቲው ወድያውኑ ገልፀዋል " ሲልም ጠቁሞ " ይሁን እንጂ ቦርዱ ፓርቲው ያቀረበውን 'የአልቀበልም" ምላሽ ጆሮ ዳባ ልበስ ማለቱ 'ልክ አይደለም ' " ሲል አብራርተዋል።
" የህወሓት ህጋዊነት በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መሰረት ሙሉ በሙሉ እንዲመለስ (Reinstate) እንዲደረግ እንጠይቃለን " ያለው ኮሚሽኑ ፤ " ከዚህ ውጭ ያለው ውሳኔ እና ትእዛዝ ተቀባይነት የለውም " ብሏል።
ከቀናት በፊትም የነ ደብረፅዮን (ዶ/ር) ቡድን ባወጣው መግለጫ " ለሁለትዮሽ ውይይት ዝግጁ ነኝ የምርጫ ቦርድን የተናጠል ውሳኔ ዛሬም ይሁን ነገ አልቀበልም " ማለቱ ይታወሳል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ህወሓት በሕጉ መሰረት ጠቅላላ ጉባኤውን እስከ የካቲት 3 ቀን 2017 ዓ.ም እንዲያደርግ አሳስቧል።
ይህ በሕግ ፓርቲው ላይ የተጣለ ግዴታ በወቅቱ ሳይፈፀም ቢቀር ቦርዱ ሕጉን መሠረት በማድረግ ተገቢ ነው የሚለውን ውሳኔ የሚሰጥ መሆኑንም ገልጿል።
ከዚህ ቀደም የህወሓት አመራሮችን ለሁለት የከፈለ ጉባኤ መደረጉ አይዘነጋም። በወቅቱም ምርጫ ቦርድ ያልተገኘበትን እና ስርዓቱን ያልተከተለ ጠቅላላ ጉባኤ እውቅና እንደማይሰጥ ማስገንዘቡ ይታወሳል።
@tikvahethiopia
🤔165❤112😡63👏44🕊37😭14😢9🙏6😱5🥰4
TIKVAH-ETHIOPIA
#NewsAlert ህወሓት ለሦስት ወር ከፖለቲካ እንቅስቃሴ ታገደ። ➡ በሦስት ወራት የዕግድ ጊዜ የዕርምት ዕርምጃ ሳይወስድ ቢቀር የፖርቲው ምዝገባ እንዲሠረዝ ተወስኗል። የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ( ህ.ወ.ሓ.ት) ከፖለቲካዊ እንቅስቃሴ መታገዱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አሳወቀ። ፓርቲው በልዩ ሁኔታ ከተመዘገበ ጊዜ አንሥቶ ባሉት 6 ወራት ውስጥ የቦርዱ ታዛቢዎች በተገኙበት ጠቅላላ ጉባዔ…
#Update #TPLF
" ቦርዱ ከፌደራል መንግስት ጋር የጀመርነውን ተከታታይ ውይይት ከማደናቀፍ እንዲቆጠብ እንጠይቃለን " - በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ህወሓት በልዩ ሁኔታ ከተመዘገበ ጊዜ አንሥቶ ባሉት 6 ወራት ውስጥ የቦርዱ ታዛቢዎች በተገኙበት ጠቅላላ ጉባዔ ማድረግ ይጠበቅበት ነበር ፤ ይህንን ባለማድረጉ ለሦስት ወር ከፖለቲካ እንቅስቃሴ እንዲታደግ ፤ በሦስት ወራት የዕግድ ጊዜ የዕርምት ዕርምጃ ሳይወስድ ቢቀር የፖርቲው ምዝገባ እንዲሠረዝ መወሰኑ ተከትሎ ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመሩት ህወሓት ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል።
ህወሓት ግማሽ ክፍለ ዘመን ያስቆጠረ አንጋፋ ፓርቲ መሆኑ የገለፅው መግለጫው ፤ " ጥቅምት 23/2015 ዓ/ም በደቡብ አፍሪካዋ የፕሪቶሪያ ከተማ የሰላም ውል ከተፈራረመ ጀምሮ ህጋዊነት የተመለሰ ነው " ብለዋል።
የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ ህወሓት ከነሃሴ 3/2016 ዓ.ም ጀምሮ ህወሓትን በአዲስ ህግ እንደ አዲስ ፓርቲ " መዝግቤዋለሁ ማለቱን " አስገራሚ እና ተቀባይነት የሌለው ፤ ፓርቲው ከፕሪቶሪያ ስምምነት ማግስት ህጋዊነቱ ያረጋገጠ ነው " ብሏል።
" የምርጫ ቦርድ አካሄድ በመሰረቱ ተቀባይነት የሌለው ፤ ህግን መሰረት ያላደረገ ተቀባይነት የሌለው ትርጉም አልባ ውሳኔ ነው " ብሎታል።
" ህወሓት በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መሰረት ከኢትዮጵያ መንግስት እውቅና ተሰጣጥቶ የሰላም ውል የፈረመ ፓርቲ ነው " ያለው ህወሓት ፤ " ከኢፌዲሪ መንግስት ተከታታይ የፓለቲካ ውይይት በማካሄድ ላይ ነን። ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ ሰላማዊ ውይይቱ ከማደናቀፍ እንዲቆጠብ " ሲል አቋሙ ግልጿል።
ህወሓት ከኢፌዴሪ መንግስት በተከታታይ በማካሄድ ላይ ያለው ውይይት ውጤታማ በቅርቡ ወደ ፍሬ የሚቀየር መሆኑ የገለፀው ህወሓት " የምርጫ ቦርድ ይህንን መልካም ሂደት የሚፃረር አካሄድ በመሄድ ላይ ይገኛል " ሲል ከሷል።
የኢፌዴሪ መንግስት የፕሪቶሪያ ስምምነት ሙሉ በሙሉ በመተግበር ህገ-መንግስቱ እንዲያከብር እና እንዲያስከብር የጠየቀው ህወሓት ፥ የምርጫ ቦርዱ ውሳኔ 50ኛው የፓርቲው የምስረታ በዓል ከማክበር እንደማያግደው በመግለፅ " ህዝቡ በዓሉ ለማክበር የጀመረው እንቅስቃሴ አጠናክሮ ይቀጥል " ብሏል።

❤302😡92🤔45🕊45👏18😭15🥰6😱3🙏3
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#TPLF
በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጥሪ ተቋወመ።
ዛሬ ምሽት ባወጣው መግለጫ ፥ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚነንስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) የትግራይ ህዝብ ለቀጣይ አንድ ዓመት ስልጣኑ የሚራዘመውን የጊዚያዊ አስተዳደሩን የሚመራ ፕሬዜዳንት እንዲጠቁም አስመልክቶ ያወጡትን መልዕክት " የተናጠል ውሳኔና ተግባር " ሲል ተቃውሟል።
" የፕሪቶሪያ ሥምምነት ከተፈረመ ሁለት ዓመት ተኩል ሆኖታል " ያለው የደብረፅዮን (ዶ/ር) ህወሓት " ስምምነቱ በሙሉነት ተተግብሮ ትግራይ በህዝብ የተመረጠ መንግስት ሊኖራት ይገባ ነበር " ብሏል።
" የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በሙሉነት ያልተተገበረው የፌደራል መንግስት በስምምነቱ አፈፃፀምና አተገባበር በተከተለው የተሳሳተ አካሄድና ፓለቲካዊ ቀውስ እንዲፈጠር በመስራቱ ነው " ሲልም ክስ አሰምቷል።
" በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት አንቀፅ 3 መሰረት ተዋዋይ ወገን ሌላውን በቀጥታ ይሁን በተዘዋዋሪ በፕሮፓጋንዳ ማጥቃት ይከለክላል ይሁን እንጂ ይህንኑ የስምምነቱ አካል በፌደራል መንግስት በተደጋጋሚ እየተጣሰ ነው " ብሏል።
" የፌደራል መንግስት ከፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መንፈስና ይዘት በወጣ አካሄድ አግባብነት በሌላቸው 359/1995፤ ደንብ 533/2015 ህግና አዋጆች እንዳሻው እየወሰነ ይገኛል " የሚል ወቀሳም አቅርቧል።
" የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት አንቀፅ 10 የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር በህወሓትና በኢትዮጵያ መንግስት መግባባት እንዲቋቋም ያዛል " ያለው የደብረፅዮን (ዶ/ር) ህወሓት " የኢትዮጵያ መንግስት የተናጠል ውሳኔ መወሰን አይችልም " ብሏል።
" ህወሓት ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ከስልጣን ማስነሳቱ ተከትሎ ፤ ጀነራል ታደሰ ወረደ ፕረዚደንት እንዲሆኑ ማእከላይ ኮሚቴ ወስኖ የኢትዮጵያ መንግስት ተቀብሎታል " ያለም ሲሆን " ይህንን ወደ ጎን በመተው በጠቅላይ ሚንስትሩ የተናጠል ውሳኔ በሚያስመስል መልኩ የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት የሚጥስ አካሄድ ተቀባይነት የለውም " ሲል ገልጿል።
" የፌደራል መንግስት ህዝብን ከሚጎዱ ግልፅ ተግባራት በመቆጠብ ዘላቂ ጥቅምና የጋራ ሰላም በሚያረጋግጡ ተግባራት እንዲያተኩር ጥሪ እናቀርባለን " ያለው የደብረፅዮን (ዶ/ር) ህወሓት " የተናጠል ውሳኔዎች እንዲቆሙ " ብሏል።

👏855😡279🤔217❤177🕊94😭44😢19💔18😱17🥰13🙏12
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#TPLF : " ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት ሆኖው መሾማቸው እደግፋለሁ " ሲል በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት አሳውቋል።
የፕሬዜዳንቱን ሹመት ከኢትዮጵያ መንግስት የተስማመበት የሚቀበለውና የሚደግፈው መሆኑ ገልጿል።
ፓርቲው ፥ ስልጣኑ ባከተመው በአቶ ጌታቸው ረዳ ሲመራ የነበረው ጊዚያዊ አስተዳደር የጠፋው ጊዜን ለማካካስ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ገልፆ " የፌደራል መንግስት የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት የሚፃረሩ የተናጠል አዋጆች ፣ ደንቦችና መመሪያዎች ከማውጣት እንዲቆጠብ " ብሏል።
ድርጅቱ " ብሄራዊ የክህደት ቡድን " ሲል የገለፀው አቶ ጌታቸው ረዳ በበላይነት ሲመሩት የነበሩት ጊዚያዊ አስተዳደር ከስልጣኑ እንዲወገድ " የህዝቡ አስተዋፅኦ " ከፍተኛ ነበር በማለት ገልጿል።
የቀድሞው የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዚዳንት እና የአሁኑ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ ከቀናት በፊት ከቢቢሲ ፎከስ ኦን አፍሪካ ጋር በነበራቸው ቆይታ አዲሱ ፕሬዚዳንት ሊገጥማቸው ስለሚችል ተግዳሮት ተናግረው ነበር።
በዚህም ፥ " ፓርቲው ፕሬዝዳንቱን እንደሾመው ያስባል ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ደግሞ ራሳቸው እንደሾሙት ይናገራሉ እንደ አለመታደል ያጋጥመዋል ብዬ የማስበው አንዱ ተግዳሮት አሁንም ሥልጣኑን ጠቅልሎ ለመያዝ ከሚፈልገው የህወሓት አንጃ የሚመጣው ከቁጥጥር ውጪ የሆነ የሥልጣን ጥማት ነው " ብለው ነበር።
ፕሬዜዳንቱ ይህንን የመጋፈጥ አቅምና ክህሎቱ ይኖራቸዋል ወይ ? የሚለው ጉዳይ ወደፊት የሚታይ እንደሆነ ገልጸዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ

🤔270🕊128❤88😡42😭19😱9😢7🥰6👏6🙏2
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" የፓርቲው መሠረዝ ውጤት በህ.ወ.ሓ.ት እና አመራሮቹ ላይ ይፈጸማል " - ምርጫ ቦርድ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምን አለ ?
- ህ.ወ.ሓ.ት በዐመጻ ድርጊት ላይ በመሣተፉ ምክንያት ከፖለቲካ ፓርቲነት ተሰርዞ ነበር። ይሁንና የፕሪቶሪያ ስምምነት ከተደረገ በኋላ የህ.ወ.ሓ.ት ሕጋዊ ሰውነት እንዲሰረዝ የተላለፈው ውሣኔ እንዲነሣ ቦርዱን ሚያዝያ 13 እና ሚያዝያ 28 ቀን 2015 ዓ.ም. ጠይቋል። ሆኖም ቦርዱ በዐመጻ ድርጊት በመሣተፍ ከፖለቲካ ፓርቲነት የተሠረዘ የፖለቲካ ፓርቲ ሕጋዊ ሰውነቱ ከተሠረዘ በኋላ ሕጋዊ ሰውነቱን ለመመለስ የሚያስችል ሕግ ስለሌለ ጥያቄውን ውድቅ አድርጎበታል።
- የኢትዮጵያ የምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ-ምግባር ዐዋጅ ቁጥር 1162/2013 ለማሻሻል የወጣውን ዐዋጅ ቁጥር 1332/2016 መታወጁን ተከትሎ ህ.ወ.ሓ.ት በዐዋጁ መሠረት " በልዩ ሁኔታ " ፓርቲ ሆኖ ለመመዝገብ መቅረብ የሚገባቸውን ሠነዶች በማያያዝ ባቀረበው ጥያቄ እንዲሁም ህ.ወ.ሓ.ትን አስመልክቶ የፍትሕ ሚኒስቴር በሕግ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ሰኔ 17 ቀን 2016 ዓ.ም. በጻፈው ደብዳቤ መነሻ ቦርዱ በማሻሻያ ዐዋጁ መሠረት ፓርቲውን " በልዩ ሁኔታ " መዝግቦ ነሐሴ 3 ቀን 2016 ዓ.ም. ሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ ሰጥቷል።
- ህ.ወ.ሓ.ት ምዝገባውን ተከትሎ ቦርዱ እንዲፈጽም የሰጠውን ትዕዛዝ ባለማክበሩ በተለያየ ጊዜ ማሳሰቢያ ቢሰጥም ፓርቲው ግን በሕግ የተጣለበትን ግዴታ አልፈጸመም።
- ህ.ወ.ሓ.ት የፓርቲውን ህጋዊነት የሚያረጋግጥበትን እና በወቅቱም #አምኖበትና_ተስማምቶ_የተቀበለውን የፖለቲካ ፖርቲ ሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ " አላውቅም፤ ሕጋዊ ሰውነቴ በዚህ ሠነድ አይረጋገጥም " በማለት ሕግንና መመሪያን ባለማክበርና ለማክበርም ፈቃደኛ ባለመሆን ሲገልጽ ቆይቷል።
- ቦርዱ በዐዋጅ ቁጥር 1162/2011 መሠረት በዐመጻ ተግባር በመሠማራቱ የተሠረዘን ፓርቲ ሕጋዊ ሰውነት የምመልስበት የሕግ ድንጋጌ የለኝም በማለት ግንቦት 4 ቀን 2015 ዓ.ም. ለህ.ወ.ሓ.ት ምላሽ ከሰጠ ከአንድ ዓመት በኋላ ዐዋጅ ቁጥር 1332/2016 ግንቦት 27 ቀን 2016 ዓ.ም. ሲታወጅ ህ.ወ.ሓ.ት ይህንኑ ፓርቲዎችን በልዩ ሁኔታ የሚመዘግብ ዐዋጅ በታወጀ በሁለተኛው ወር ሐምሌ 19 ቀን 2016 ዓ.ም. በዐዋጁ ላይ " በልዩ ሁኔታ " የፖለቲካ ፓርቲ ሆኖ ለመመዝገብ እንዲቀርቡ በሕጉ የተመለከቱትን ዝርዝር ሠነዶች ይኸውም ፦
• የፓርቲውን ፕሮግራም፣
• የፓርቲውን መተዳደሪያ ደንብ
• የፓርቲው አመራሮች ስም ዝርዝር ከፊርማ ጋር ለቦርድ አቅርቧል።
- ህ.ወ.ሓ.ት ሕጋዊ ሰውነቱ እንዲሠረዝ የተላለፈውን ውሣኔ እንዲነሣ በማለት ሚያዝያ 13 እና ሚያዝያ 28 ቀን 2015 ዓ.ም. ለቦርዱ ባቀረበው ጥያቄ በዐዋጅ ቁጥር 1332/2016 " በልዩ ሁኔታ " ፓርቲ ሆኖ ለመመዝገብ እንዲቀርቡ የተጠየቁትን ሠነዶች አንዳቸውንም አያይዞ አላቀረበም። ይህ በግልጽ የሚያስረዳው ህ.ወ.ሓ.ት ሐምሌ 19/ 2016 ዓ.ም. ያቀረበው ጥያቄ ሚያዝያ 13 እና ሚያዝያ 28 ቀን 2015 ዓ.ም. ካቀረበው ጥያቄ በተለየ መልኩ በዐዋጅ ቁጥር 1332/2016 መሠረት " በልዩ ሁኔታ " ፖርቲ ሆኖ ለመመዝገብ እንዲቀርብ ሕጉ በሚጠይቀው መሠረት የፖለቲካ ፓርቲ ምዝገባ ጥያቄ ማቅረቡን ነው።
- ህ.ወ.ሓ.ት ሐምሌ 19 ቀን 2016 ዓ.ም. ጥያቄውን ሲያቀርብ ዐዋጅ ቁጥር 1332/2016 ታውጆ ፤ ለሕዝብ በይፋ ተገልጾ፤ በሥራ ላይ ከዋለ ሁለት ወር ካለፈው በኋላ ነው። ህ.ወ.ሓ.ትም ለሕዝብ ይፋ የሆነውን ዐዋጅ ዐላማና አፈጻጸም በግልጽ በማወቅና በመረዳት በዐዋጁ ላይ የተመለከቱትን ሠነዶች አያይዞ በማቅረብ በዐዋጁ የተጠየቀውን የምዝገባ ሥርዓት በመፈጸም " በልዩ ሁኔታ " ምዝገባው ተከናውኗል።
- ህ.ወ.ሓ.ት ሐምሌ 19 ቀን 2016 ዓ.ም. በጻፈው ደብዳቤ ላይ " የቀድሞው ሕጋዊ ሰውነት ይመለስልኝ " ብሎ ጠይቋል። ያቀረባቸው ሠነዶችና ጥያቄው የቀረበው የተሻሻለውን ዐዋጅ መውጣት ተከትሎ ነው። ቦርዱ ለህ.ወ.ሓ.ት ነሐሴ 3 ቀን 2016 ዓ.ም. " በልዩ ሁኔታ '' በመመዝገብ የሰጠው የሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ ሠርትፊኬት፣ ከሠርተፊኬቱም ጋር አብሮ በሰጠው ነሐሴ 3 ቀን 2016 ዓ.ም. ደብዳቤ ላይ የህ.ወ.ሓ.ት የቀድሞው ሕጋዊ ሰውነት እንደማይመለስለት በግልጽ ተመልክቶ ይገኛል።
- ህ.ወ.ሓ.ት የቀድሞው ሕጋዊ ሰውነት እንደማይመለስለት በግልጽ በደብድቤ ሰፍሯል። የፓርቲው ከፍተኛ አመራር በቦርዱ ዋና መ/ ቤት በመገኘት በልዩ ሁኔታ መመዝገቡን የሚገልጽ ሠርትፊኬት እና ደብዳቤውን በሚገባ አይተው፣ አንብበውና ተስማምተው በፈቃዳቸው ፈርመው ከወሰዱ በኋላ ይህ " በልዩ ሁኔታ " ተመዝግቦ የተሰጠን የሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ " አንቀበለውም " ማለት ተቀባይነት የለውም።
- ቦርዱ በሕግ የተጣለበትን ኃላፊነት ለመወጣትና ፓርቲው ያለበትን ኃላፊነትና ግዴታ እንዲወጣ ለማድረግ በተለያየ ወቅት በጽሑፍ ማሳሰቢያ ሲሰጥ ቆይቷል።
- ፓርቲው ግዴታውን እንዲወጣ ዕድል ለመስጠት ቦርዱ ፓርቲውን ለሦስት ወራት ከማንኛውም የፖለቲካ ፖርቲ እንቅስቃሴ በማገድ ፖርቲው የዕርምት ዕርምጃ በመውሰድ በሕጉ መሠረት ግዴታውን እንዲፈጽም ቦርዱ ጥረት ቢያደርግም ፓርቲው የተጣለበትን የሕግ ግዴታ ለመወጣት ፈቃደኛ አልሆነም።
- ቦርዱ የካቲት 5 ቀን 2017 ዓ.ም. በጻፈው ደብዳቤ ፓርቲው በሦስት ወር ዕግድ ጊዜ የዕርምት ዕርምጃ ሳይወስድ ቢቀር የፓርቲውን ምዝገባ እንደሚሰረዝ አሳውቋል።
- ህ.ወ.ሓ.ት ግን የዕርምት ዕርምጃ ባለመውሰዱ ቦርዱ ግንቦት 5/2017 ዓ.ም. ባደረገው ስብሰባ ፓርቲው ከግንቦት 5 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ ከፖለቲካ ፖርቲነት የተሠረዘ መሆኑን ወሥኗል።
- ውሣኔው ለህ.ወ.ሓ.ት፣ ለፍትሕ ሚኒስቴር በጽሑፍ እንዲደርስና ለሕዝብ ይፋ እንደረግና ተወስኗል።
- የፓርቲውን መሠረዝ ውጤትን በተመለከተ የዐዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀጽ 99 እንደ አግባብነቱ በህ.ወ.ሓ.ትና አመራሮቹ ላይ እንዲፈጸም ቦርዱ ወሥኗል።

👏432😡128❤112🤔33🕊26🙏17🥰10😢8😭5😱4
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#TPLF
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከፓርቲነት የሰረዘው ህወሓት ባሰራጨው ደብዳቤ የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት አሸማጋዮች ሁኔታውን የሚመለከት አስቸኳይ ስብሰባ እንዲቀመጡ ጥሪ አቅርቧል።
ህወሓት ለአፍሪካ ሕብረትና የተለያዩ ተቋማት እና የስምምነቱ አፈፃፀም ተከታዮች ላላቸው በፃፈው ደብዳቤ " ህወሓት እና የኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት በፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት መሰረት እርስበርስ እውቅና ተሰጣጥተዋል " ሲል ገልጿል።
" ነገር ግን አሁን እየታየ ባለው ሁኔታ የፌደራሉ መንግስት ይህንኑ እየጣሰ ነው " ሲል ህወሓት ከሷል።
#DeutscheWelle

🤔334❤140👏85😡82🕊31🙏12😱9😢8😭8🥰6