TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" የፓርቲው መሠረዝ ውጤት በህ.ወ.ሓ.ት እና አመራሮቹ ላይ ይፈጸማል " - ምርጫ ቦርድ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምን አለ ?
- ህ.ወ.ሓ.ት በዐመጻ ድርጊት ላይ በመሣተፉ ምክንያት ከፖለቲካ ፓርቲነት ተሰርዞ ነበር። ይሁንና የፕሪቶሪያ ስምምነት ከተደረገ በኋላ የህ.ወ.ሓ.ት ሕጋዊ ሰውነት እንዲሰረዝ የተላለፈው ውሣኔ እንዲነሣ ቦርዱን ሚያዝያ 13 እና ሚያዝያ 28 ቀን 2015 ዓ.ም. ጠይቋል። ሆኖም ቦርዱ በዐመጻ ድርጊት በመሣተፍ ከፖለቲካ ፓርቲነት የተሠረዘ የፖለቲካ ፓርቲ ሕጋዊ ሰውነቱ ከተሠረዘ በኋላ ሕጋዊ ሰውነቱን ለመመለስ የሚያስችል ሕግ ስለሌለ ጥያቄውን ውድቅ አድርጎበታል።
- የኢትዮጵያ የምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ-ምግባር ዐዋጅ ቁጥር 1162/2013 ለማሻሻል የወጣውን ዐዋጅ ቁጥር 1332/2016 መታወጁን ተከትሎ ህ.ወ.ሓ.ት በዐዋጁ መሠረት " በልዩ ሁኔታ " ፓርቲ ሆኖ ለመመዝገብ መቅረብ የሚገባቸውን ሠነዶች በማያያዝ ባቀረበው ጥያቄ እንዲሁም ህ.ወ.ሓ.ትን አስመልክቶ የፍትሕ ሚኒስቴር በሕግ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ሰኔ 17 ቀን 2016 ዓ.ም. በጻፈው ደብዳቤ መነሻ ቦርዱ በማሻሻያ ዐዋጁ መሠረት ፓርቲውን " በልዩ ሁኔታ " መዝግቦ ነሐሴ 3 ቀን 2016 ዓ.ም. ሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ ሰጥቷል።
- ህ.ወ.ሓ.ት ምዝገባውን ተከትሎ ቦርዱ እንዲፈጽም የሰጠውን ትዕዛዝ ባለማክበሩ በተለያየ ጊዜ ማሳሰቢያ ቢሰጥም ፓርቲው ግን በሕግ የተጣለበትን ግዴታ አልፈጸመም።
- ህ.ወ.ሓ.ት የፓርቲውን ህጋዊነት የሚያረጋግጥበትን እና በወቅቱም #አምኖበትና_ተስማምቶ_የተቀበለውን የፖለቲካ ፖርቲ ሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ " አላውቅም፤ ሕጋዊ ሰውነቴ በዚህ ሠነድ አይረጋገጥም " በማለት ሕግንና መመሪያን ባለማክበርና ለማክበርም ፈቃደኛ ባለመሆን ሲገልጽ ቆይቷል።
- ቦርዱ በዐዋጅ ቁጥር 1162/2011 መሠረት በዐመጻ ተግባር በመሠማራቱ የተሠረዘን ፓርቲ ሕጋዊ ሰውነት የምመልስበት የሕግ ድንጋጌ የለኝም በማለት ግንቦት 4 ቀን 2015 ዓ.ም. ለህ.ወ.ሓ.ት ምላሽ ከሰጠ ከአንድ ዓመት በኋላ ዐዋጅ ቁጥር 1332/2016 ግንቦት 27 ቀን 2016 ዓ.ም. ሲታወጅ ህ.ወ.ሓ.ት ይህንኑ ፓርቲዎችን በልዩ ሁኔታ የሚመዘግብ ዐዋጅ በታወጀ በሁለተኛው ወር ሐምሌ 19 ቀን 2016 ዓ.ም. በዐዋጁ ላይ " በልዩ ሁኔታ " የፖለቲካ ፓርቲ ሆኖ ለመመዝገብ እንዲቀርቡ በሕጉ የተመለከቱትን ዝርዝር ሠነዶች ይኸውም ፦
• የፓርቲውን ፕሮግራም፣
• የፓርቲውን መተዳደሪያ ደንብ
• የፓርቲው አመራሮች ስም ዝርዝር ከፊርማ ጋር ለቦርድ አቅርቧል።
- ህ.ወ.ሓ.ት ሕጋዊ ሰውነቱ እንዲሠረዝ የተላለፈውን ውሣኔ እንዲነሣ በማለት ሚያዝያ 13 እና ሚያዝያ 28 ቀን 2015 ዓ.ም. ለቦርዱ ባቀረበው ጥያቄ በዐዋጅ ቁጥር 1332/2016 " በልዩ ሁኔታ " ፓርቲ ሆኖ ለመመዝገብ እንዲቀርቡ የተጠየቁትን ሠነዶች አንዳቸውንም አያይዞ አላቀረበም። ይህ በግልጽ የሚያስረዳው ህ.ወ.ሓ.ት ሐምሌ 19/ 2016 ዓ.ም. ያቀረበው ጥያቄ ሚያዝያ 13 እና ሚያዝያ 28 ቀን 2015 ዓ.ም. ካቀረበው ጥያቄ በተለየ መልኩ በዐዋጅ ቁጥር 1332/2016 መሠረት " በልዩ ሁኔታ " ፖርቲ ሆኖ ለመመዝገብ እንዲቀርብ ሕጉ በሚጠይቀው መሠረት የፖለቲካ ፓርቲ ምዝገባ ጥያቄ ማቅረቡን ነው።
- ህ.ወ.ሓ.ት ሐምሌ 19 ቀን 2016 ዓ.ም. ጥያቄውን ሲያቀርብ ዐዋጅ ቁጥር 1332/2016 ታውጆ ፤ ለሕዝብ በይፋ ተገልጾ፤ በሥራ ላይ ከዋለ ሁለት ወር ካለፈው በኋላ ነው። ህ.ወ.ሓ.ትም ለሕዝብ ይፋ የሆነውን ዐዋጅ ዐላማና አፈጻጸም በግልጽ በማወቅና በመረዳት በዐዋጁ ላይ የተመለከቱትን ሠነዶች አያይዞ በማቅረብ በዐዋጁ የተጠየቀውን የምዝገባ ሥርዓት በመፈጸም " በልዩ ሁኔታ " ምዝገባው ተከናውኗል።
- ህ.ወ.ሓ.ት ሐምሌ 19 ቀን 2016 ዓ.ም. በጻፈው ደብዳቤ ላይ " የቀድሞው ሕጋዊ ሰውነት ይመለስልኝ " ብሎ ጠይቋል። ያቀረባቸው ሠነዶችና ጥያቄው የቀረበው የተሻሻለውን ዐዋጅ መውጣት ተከትሎ ነው። ቦርዱ ለህ.ወ.ሓ.ት ነሐሴ 3 ቀን 2016 ዓ.ም. " በልዩ ሁኔታ '' በመመዝገብ የሰጠው የሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ ሠርትፊኬት፣ ከሠርተፊኬቱም ጋር አብሮ በሰጠው ነሐሴ 3 ቀን 2016 ዓ.ም. ደብዳቤ ላይ የህ.ወ.ሓ.ት የቀድሞው ሕጋዊ ሰውነት እንደማይመለስለት በግልጽ ተመልክቶ ይገኛል።
- ህ.ወ.ሓ.ት የቀድሞው ሕጋዊ ሰውነት እንደማይመለስለት በግልጽ በደብድቤ ሰፍሯል። የፓርቲው ከፍተኛ አመራር በቦርዱ ዋና መ/ ቤት በመገኘት በልዩ ሁኔታ መመዝገቡን የሚገልጽ ሠርትፊኬት እና ደብዳቤውን በሚገባ አይተው፣ አንብበውና ተስማምተው በፈቃዳቸው ፈርመው ከወሰዱ በኋላ ይህ " በልዩ ሁኔታ " ተመዝግቦ የተሰጠን የሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ " አንቀበለውም " ማለት ተቀባይነት የለውም።
- ቦርዱ በሕግ የተጣለበትን ኃላፊነት ለመወጣትና ፓርቲው ያለበትን ኃላፊነትና ግዴታ እንዲወጣ ለማድረግ በተለያየ ወቅት በጽሑፍ ማሳሰቢያ ሲሰጥ ቆይቷል።
- ፓርቲው ግዴታውን እንዲወጣ ዕድል ለመስጠት ቦርዱ ፓርቲውን ለሦስት ወራት ከማንኛውም የፖለቲካ ፖርቲ እንቅስቃሴ በማገድ ፖርቲው የዕርምት ዕርምጃ በመውሰድ በሕጉ መሠረት ግዴታውን እንዲፈጽም ቦርዱ ጥረት ቢያደርግም ፓርቲው የተጣለበትን የሕግ ግዴታ ለመወጣት ፈቃደኛ አልሆነም።
- ቦርዱ የካቲት 5 ቀን 2017 ዓ.ም. በጻፈው ደብዳቤ ፓርቲው በሦስት ወር ዕግድ ጊዜ የዕርምት ዕርምጃ ሳይወስድ ቢቀር የፓርቲውን ምዝገባ እንደሚሰረዝ አሳውቋል።
- ህ.ወ.ሓ.ት ግን የዕርምት ዕርምጃ ባለመውሰዱ ቦርዱ ግንቦት 5/2017 ዓ.ም. ባደረገው ስብሰባ ፓርቲው ከግንቦት 5 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ ከፖለቲካ ፖርቲነት የተሠረዘ መሆኑን ወሥኗል።
- ውሣኔው ለህ.ወ.ሓ.ት፣ ለፍትሕ ሚኒስቴር በጽሑፍ እንዲደርስና ለሕዝብ ይፋ እንደረግና ተወስኗል።
- የፓርቲውን መሠረዝ ውጤትን በተመለከተ የዐዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀጽ 99 እንደ አግባብነቱ በህ.ወ.ሓ.ትና አመራሮቹ ላይ እንዲፈጸም ቦርዱ ወሥኗል።
#TPLF
@tikvahethiopia

👏432😡128❤112🤔33🕊26🙏17🥰10😢8😭5😱4