TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.62K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#እናትፓርቲ

እናት ፓርቲ የአዲስ አበባ ፋይናንስ ቢሮ ከሚያዝያ 2015 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ ያደረገው የጣሪያ ግድግዳ/ ንብረት ግብር መመርያ እንዲቆም የመሠረተው ክስ በፍርድ ቤት ተቀባይነት አግኝቶ መመሪያው "ተፈጻሚ ሊሆን አይገባም" ሲል ፍርድ ቤት ጥር 9 ቀን ብይን መስጡቱን ፓርቲው አስታውቋቃ።

ፓርቲው የወጣው መመርያ " ሕግን ባልተከተለ መንገድ እና የከተማ አስተዳደሩ ባልተሰጠው ሥልጣን የወጣ በመሆኑ " መመሪያው እንዲሻሻል ሲል በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አስተዳደር ችሎት ክስ መስሮቶ መቆየቱን ገልጿል።

ፍ/ቤቱ የአዲስ አበባ ፋይናንስ ቢሮ ያቀረባቸውን ሦስት መቃወምያዎች ውድቅ አድርጎ ወደ ፍሬ ነገር ክርክር ከገባ በኋላ ጉዳዩን መርምሮ መመሪያው " ተፈጻሚነት ሊኖረው አይገባም " የሚል ውሳኔ መስጠቱን፤ የውሳኔውን አፈጻጸም እንደሚከታተልም ፓርቲው አስታውቋል።

(ፓርቲው የላከው መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
2.64K👏1.3K🥰439🙏192🤔41🕊38😢25😭23😡20😱15
#እናትፓርቲ

" አማራ ክልል በተሟላ ጦርነት ውስጥ ነው። በየቀኑ ሰዎች በድሮን ጭምር ይጨፈጨፋሉኮሚሽኑና መንግስት ደግሞ ' የለም እየሞትክም ተመካከር' ' ይላሉ ! " - እናት ፓርቲ

እናት ፓርቲ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአማራ ክልል ባደረገው አጀንዳ የማሰባሰብ ሂደት ያልተሳተፈበትን ምክንያትና የኮሚሽኑን አካሄድ በተመለከተ የሰላ ትችት ሰንዝሯል።

Q.
በክልሉ አጀንዳ የማሰባሰብ ሂደት ያልተሳተፋችሁበት ምክንያት ምንድን ነው? ኮሚሽኑ ‘ይምጡ በራችን ክፍት ነው’ ይላል፤ እናንተ ደግሞ እየተሳተፋችሁ አይደለምና ልዩነቱ ምንድን ነው? መፍትሄውስ?

እናት ፓርቲ ፦

"
ግልጽ ነውኮ! ክልሉ በተሟላ ጦርነት ውስጥ ነው ያለው፡፡ በየቀኑ ሰዎች በድሮን ጭምር ይጨፈጨፋሉ፡፡ በአጠቃላይ ከባድ ውድመት እየደረሰ ነው፡፡

በክልሉ ለሚሊዮን የሚጠጉ ተፈናቃዮች፤ በብዙ ቦታዎች ከፍተኛ ድርቅና ሰው ሰራሽ ረሃብ አለ፡፡ ለሕዝቡ ጥቅም ሊሟገቱ የሚችሉ በርካታ ምሁራንና ፖለቲካኞች በእስር ናቸው ወይም ተሰደዋል።

በየሳምንቱ ዜጎች እየታገቱ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ይጠየቅባቸዋል፡፡ በክልሉ እንኳን ምክክር ሊያስደርግ የሚችል አውድ ገበያ ወጥቶ ቤት ለመግባት፣ ነብሰጡርን ሀኪም ቤት መውሰድ፣ ህፃናትን ትምህርት ቤት መሄድ፣ ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስም ብርቅ ሆኗል፡፡

ማህበረሰቡ 'የህልውና ችግር ገጥሞኛል በቅድሚያ እሱን ፍቱልኝ' (quick fix) እያለ ነው፡፡ ኮሚሽኑና መንግስት ደግሞ 'የለም እየሞትክም ተመካከር” ይላሉ።

በእነዚህ አበሳዎች ውስጥ ያለን ማህበረሰብ ነው ለፖለቲካ ትርፍ ሲባል 'ናና  አዲስ ማኅበራዊ ውል ለሚፈራረምበት ምክክር አጀንዳ አዋጣ'፣ ተመካከር' የሚባለው?

ኮሚሽኑ ከነችግሩ መጀመሪያ የነበረውን አቋም ወደመያዝ መመለስ አለበት፡፡ ኮሚሽኑ ለመንግስት የፕሮፓጋንዳ መሳሪያነት እየዋለ ነው። እንደዚያ መሆናቸውን ያቁት ይሆን አይሆን እርግጠኞች አይደለንም።

መፍትሄው፥ በአጠቃላይ ከምክክሩ በፊት ድርድር መቅደም፤ ተኩስ መቆም አለበት፡፡ ጦርነቱ ፖለቲካዊ መፍትሄ ያሻዋልል።

የኮሚሽኑ ሰዎች ያ እንዲሆን ባላቸው ተጽዕኖ በጎ አስተዋጽዖ ቢያሳራፉ ውለታም ጭምር ነው፤ ካልሆነ ግን ቢያንስ በሰው ቁስል እንጨት ከመስደድ ቢቆጠቡ እንመክራለን” ብሏል።

Q. በአማራ ክልል አጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት እንደማትሳተፉ ገልጻችሁ ለነበረው በተለይም "ቅድሚያ ጦርነት ይቁም" የሚለውን ሀሳባችሁን ኮሚሽኑ ምላሽ ሰጠበት ? 

እናት ፓርቲ ፦

" እንደማንሳተፍ የሚገልጸውን ደብዳቤ ለኮሚሽኑ ከላክንና ለህዝብ ይፋ ካደረግን በኋላ በሚዲያዎች በኩል በተወሰወነ ደረጃ መልስ የሚመስል ነገር ሰጥቷል።

ሀሳቡ የሚጣል እንዳልሆነና በጊዜ ሂደት (እስከዚያው) የተጠቀሱ ችግሮች ይፈታሉ ብለው እንደሚያምኑ የሚያወሱ ነበሩ፡፡ 

ከሦስት ሳምንታት በፊትም ከክልሉ ባለስልጣናት ጋር በባሕር ዳር ተገኝተው በተወያዩበት ወቅት እኛ ያነሳናቸውን፥ መንግስት በራሱ ተነሳሽነት ተኩስ አቁም እንዲያውጅ፣ እስረኞችን እንዲፈታ የሚሉትን ቅድመ ሁኔታዎች አንስተዋቸዋል።

ግን አጠንክረው አልዘለቁባቸውም፤ አይዘልቁባቸውም፡፡ "

Q. ኮሚሽኑ በአዲስ አበባ አጀንዳ ማሰባሰብ ሲጀምር ተሳትፋችሁ ነበር፤ ከዚያ በኋላስ በሌሎች ክልሎች (ለምሳሌ በኦሮሚያ) ተሳትፋችሁ ነበር ?

እናት ፓርቲ ፦

"አዎ ተሳትፈናል፡፡ በአጠቃላይ የፓርቲያችን እምነት በዋናው ምክክር ላይ ቅድመ ሁኔታዎች ቢኖሩንም በአንጻራዊነት ለመመካከር የምትሆን ክፍተት ከተገኘች ለዚህ አገር ከምክክር የተሻለ መፍትሄ ይኖራል ብለን አናምንም፤ ያንንም ከማንም በላይ ስናቀነቅን ቆይተናል፡፡ 

የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ መነሳትን ጨምሮ ሌሎች ቅድመ ሁኔታዎች እንዳሉ ሆነው የመነመነም አስቻይ ሁኔታ አለ ብለን ስላመንን አድርገነዋል፡፡"

Q. በአማራ ክልል በነበረው ሂደት ኮሚሽኑ ምን ክፍተቶችን ቢያስተካክል አሁንስ አጀንዳችሁን ታስረክባላችሁ ? ነው ወይስ ከዚህ በኋላ አጀንዳ የማስገባት እቅዱ የላችሁም? ከሌላችሁ ለምን ? 

እናት ፓርቲ

" የእኛ የቅድሚያ ቅድሚያ ጉዳይና ሆድ ቁርጠት የህዝብ ደህንነትና በሰላም ወጥቶ የመግባት ሁኔታ ነው።

የመሳሪያ ድምጽ በቅድሚያ ፀጥ ይበል፣ የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ፤ በአንድም በሌላም ከምክክሩ ራሳቸውን ያገለሉ ኃይሎች እንዲመለሱ ይደረግ። በተለይ አሁን አሁን ደግሞ የኮሚሽኑ ለመንግስት ያደላና ፖለቲካዊ ዝንባሌ ያለው አካሄድ ካልተስተካከለ አጀንዳ ማቀበሉንም አናደርገውም ከዋና ምክክሩም ለመግባት ይቸግረናል።

ኳሱ እነርሱ እግር ላይ ነው፡፡ እንዲያውም አሁን አሁን አንድ ሥጋት እየጫረብን የመጣ ጉዳይም አለ፡፡ ምን አልባት እንዲህ እያጓተቱ ምርጫ 2018’ን ለመጋፋት እንዲውል ሊያደርጉት ይሆን? የሚል። " 
 
Q. የምክክር ኮሚሽኑ በተለያዬ ክልሎች ያካሄዳቸውን አጀንዳዎች የማሰባሰብና የመረከብ ሂደቶች እንዴት ገመገማችኋቸው ? ምንስ መስተካከል አለበት? ምንስ ጥሩ ጎን አለው ?

እናት ፓርቲ ፦

" በአጠቃላይ በጣም ጥሩ ባይባልም መጥፎ የሚባል አልነበረም፡፡ እንዲነሱ የያዝናቸው አጀንዳዎች በተለያዩ አካባቢዎችና የማኅበረሰብ ክፍሎች ጉዳይ ሆነው ሲነሱ ታዝበናል፡፡ አብዛኛው ሰው አዲስ ማኅበራዊ ውል ሰርተን የተሻለች ሀገር እንድትኖረን የመናፈቅ ነገሩ ይታያል።

በአንጻሩ በርካታ ለብልጽግና ታማኝ የሆኑ ሰዎች እንዲሳተፉ የማድረግ፣ በአንዳንድ ቦታዎችም ጭሬ ላፍሰው ዓይነት አካሄዶችን ታዝበናል፡፡ ወደ ፊት የመራመድ ጥማት ሳይሆን ወደ ኋላ የመመለስና የብጥበጣ ዓይነት አዝማሚያም አስተውለናል፡፡

ኢትዮጵያን ከስሟ ጀምሮ ክዶ የመነሳትና ፖለቲካ ወለድ ጉምዠታና የኔ፣ የኔ ዓይነት ነገሮች ነበሩት፡፡ ኮሚሽኑን ደጋግመን እንዳሳሰብነው የማይታለፉ ቀይ መስመሮች ይኖሩታል ብለን እናምናለን።

ምክክር ያስፈለገው ከነበረው የተሻለ ለመጨመርና ጥሩ ለማድረግ እንጂ ጭራሽ ያለንንም ለማጣት እንዳልሆነ ማስታወስ አይከፋም" ብሏል።

(ፓርቲው በአማራ ክልል ጉዳይ ስላነሳው ሀሳብ በቀጣይ ይቀርባል)

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
👏581102😡52😭25🕊23🙏18🤔16😢8😱5🥰4
#እናትፓርቲ #ምርጫቦርድ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ " እናት ፓርቲ በአዋጅ እና በመመሪያ ከተደነገገው ውጭ የፋይናንስ አስተዳደሩን እየመራ እና እያስተዳደረ ይገኛል " በማለት በዚህ አመት የሚሰጠውን የመንግስት የፋይናንስ ድጋፍ ሊያገኝ አይገባውም ሲል ውሳኔ አሳልፏል።

ከዚህ በተጨማሪ የፖርቲውን የባንክ ሒሳብ ወጪ ሆኖ ከታለመለት አላማ ውጪ የመንግስት ድጋፍ ገንዘብ እንዲውል አድርገዋል ባላቸው ሒሳቡን በጣምራ የሚያንቀሳቅሱት የፓርቲው አመራሮች ፦
- ዶ/ር ሰይፈሥሰላሴ አያሌው የፓርቲው ፕሬዚደንት፤
- ወ/ሪት ሜሮን ታደለ የፓርቲው ዋና ፀሐፊ
- ወ/ሪት ኩሪ አሠፋ የፓርቲው የሂሳብ ክፍል ኃላፊ ላይ የፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ ተገቢውን ምርመራ እንዲያደርግ የወሰነ መሆኑን ቦርዱ አሳውቋል።

ቦርዱ ተገኙ ያላቸው የፋይናንስ ግኝቶች ምንድናቸው ?

እናት ፖርቲ ከመንግስት ስለአገኘው የ2016 የበጀት ድጋፍ ሂሳቡን በራሱ የውጭ ኦዲተር አሰርቶ ሪፖርት ለቦርዱ ማቅረቡን አመልክቷል።

በፖርቲው የተሰየመው የውጭ ኦዲተር በኦዲት ሪፖርቱ ላይ ፦

ፓርቲው ከአባላት ለሰበሰበው መዋጮ የገንዘብ መቀበያ ደረሰኝ ያለመስጠቱን በዚህ ምክንያት በሶስት ባንኮች ላይ የሚገኘውን 65,315ብር ትክክለኛነት ማረጋገጥ አለመቻሉን፤

ለቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ወጪ የሆኑ ገንዘቦች ህጋዊ በሆኑ የወጪ ደረሰኞች አለማስደገፉን ፤

ፓርቲው ለዕርዳታ በሚል ወጪ አድርጎ ብር 158,425 መክፈሉን ይገልጻል።

ቦርዱ ከላይ የተገለፁት ግኝቶች ከውጭ ኦዲተሩ ሲቀርብለት እንዲሁም የፓርቲው አባላት ጥቅምት 3/2017 ዓ/ም በተጻፈ አቤቱታ የፓርቲው ፋይናንስ አስተዳደር ችግር ላይመሆኑን ጠቅሰው ተገቢው ማጣራት በቦርዱ እንዲደረግ በመጠየቃቸው ጉዳዩን የፌደራል ዋና አዲተር መ/ቤት እንዲያየው ማድረጉን አስረድቷል።

የፓርቲው አባላት ያቀረቧቸውን ቅሬታዎች እና የፓርቲው የውጭ ኦዲተር የዘረዘሯቸውን ግኝቶች የያዘውን የኦዲት ሪፖርት ለፌደራል ዋና ኦዲተር በመላክ ፓርቲው ከመንግስት ያገኘውን ድጋፍ ለታለመለት ዓላማ መዋል /አለመዋሉን አጣርቶ እንዲገልጽ መጠየቁን አመልክቷል።

የፌደራል ዋና ኦዲተር መ/ቤትም የፓርቲውን የመንግስት በጀት ድጋፍ ኦዲት አድርጎ ውጤቱ እንዳሳወቀው ገልጿል።

በዋና ኦዲተር የኦዲት ሪፖርቱ ላይ የታዩት ግኝቶች በዋናነት ምንድናቸው ?

🔴 ፓርቲው በአዋጅ እና በመመሪያ ከመንግስት የተሰጠውን የበጀት ድጋፍ በተለየ የሒሳብ መዝገብ በየወጪ አርእስቱ ዘርዝሮ መያዝ እንዳለበት ቢደነግግም የሒሳብ መዝገብ እንደሌለው፤ የሒሳብ ማመዛዘኛ ሪፖርት እና የባንክ ሂሳብ ማስታረቂያ እንዳላዘጋጀ እንዲሁም ከቦርዱ የተሰጠውን ድጋፍ ወጪ ሲያደርግ በተለየ የሂሳብ መዝገብ በየወጪ አርእስቱ ዘርዝሮ ሳይዝ የተፈፀመ መሆኑን ይገልጻል።

🔴 ለማህበራዊ አገልግሎት በሚል ፖርቲው ከመንግስት ያገኘውን የበጀት ድጋፍን ከታለመለት ተግባር ውጪ አውሎ እንደተገኘ ይኸውም፦
• በጎፋ ዞን ለተከሰተው የመሬት መንሸራተት እርዳታ እንዲውል ሐምሌ 25/2016ዓ/ም በወጪ ማዘዣ 000098 ብር 20ሺ ማውጣቱን፤
• ለአቶ ዳዊት ብርሀኑ መሸኛ የሚውል መስከረም 18/2017ዓ/ም በወጪ ማዘዣ 000121 15 ሺ ወጪ ማድረጉን፤
• ለአቶ ተመስገን ሹመት የሐዘን በሚል ሐምሌ 25/2016ዓ/ም በወጪ ማዘዣ 000044 3,500ብር ወጪ ማድረጉን በድምሩ 38,500 ብር ከታለመለት አላማ እና ተግባር ውጪ ያወጣ መሆኑን ይገልጻል።

🔴 በተለያዩ ጊዜያት ለ13 ቅ/ጽ/ቤቶች በባንክ ቤት በኩል በዝውውር የላከው ብር 438,500ብር ለምን ተግባር እንደዋለ የወጪ ደጋፊ ሰነድ ተያይዞ ያልቀረበ መሆኑን ይህንንም ግኝት በተመለከተ የፖርቲው ፕሬዚደንት ሲጠየቁ የሰጡት መልስ አሳማኝ ያለመሆኑን ገልጿል።

በዚህም ምርጫ ቦርድ ፓርቲው ከመንግስት የተመደበለትን ድጋፍ ከታለመለት አላማ ውጭ እንዳዋለው መገንዘቡን አሳውቋል።

በዚሀ አመት የሚሰጠውን የመንግስት ድጋፍ ሊያገኝ አይገባውም ሲልም ወስኗል።

የፓርቲውን ባንክ ሒሳብ በጣምራ ሚያንቀሳቅሱት የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች ላይ የፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ ምርመራ እንዲያደርግ የወሰነ መሆኑን ይፋ አድርጓል።

(የእናት ፓርቲ ምላሽ በቀጣይ ይቀርባል)

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
😡393110🤔24👏19😭13🙏10🕊7😱6😢6🥰1
TIKVAH-ETHIOPIA
#እናትፓርቲ #ምርጫቦርድ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ " እናት ፓርቲ በአዋጅ እና በመመሪያ ከተደነገገው ውጭ የፋይናንስ አስተዳደሩን እየመራ እና እያስተዳደረ ይገኛል " በማለት በዚህ አመት የሚሰጠውን የመንግስት የፋይናንስ ድጋፍ ሊያገኝ አይገባውም ሲል ውሳኔ አሳልፏል። ከዚህ በተጨማሪ የፖርቲውን የባንክ ሒሳብ ወጪ ሆኖ ከታለመለት አላማ ውጪ የመንግስት ድጋፍ ገንዘብ እንዲውል አድርገዋል ባላቸው ሒሳቡን…
#እናትፓርቲ

" በጀት በመከልከልና በማስከልከል የሚደናቀፍ ትግል አይኖርም ! " - እናት ፓርቲ

እናት ፓርቲ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በፓርቲው ላይ ያሳለፈውን የበጀት ክልከላ " ፖለቲካዊ ውሳኔ " ሲል ጠርቶት አውግዟል።

" በጀት በመከልከልና በማስከልከል የሚደናቀፍ ትግል የለም "ም ብሏል።

እናት ፓርቲ ምን አለ ?

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለፌዴራል ዋና ኦዲተር በጻፈው እና ለፓርቲው ግልባጭ በተደረገ ደብዳቤ የፌዴራል ዋና ኦዲተር ለፓርቲው በ2016 ዓ.ም የተሰጠን ድጋፍ ብር 1,702,561.65 (አንድ ሚሊዮን ሰባት መቶ ኹለት ሺህ አምስት መቶ ስድሳ አንድ ከ65/100) ኦዲት ማድረጉን አመልክቷል።

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት በቀጥታ የኦዲት ሪፖርቱን ለኦዲት ተደራጊ እናት ፓርቲ እንዳላደረሰና ሪፖርቱ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በኩል ፓርቲው ጋር መምጣቱን ገልጿል።

የኦዲት ግኝት ተብሎ በዋነኛነት የቀረበውና ትልቅ ጥያቄ ያስነሳው ፓርቲያው ከተደረገለት ድጋፍ ፦

- በጎፋ ዞን ለተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር) መለገሱ ፤
- ለአንድ የፓርቲው ብሔራዊ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ስንብት ለማስታወሻ ብር 15,000.00 (አሥራ አምስት ሺህ ብር) ወጪ ማድረጉ፤
- የፓርቲያው የላዕላይ ምክር ቤት አባል ከዚኽ ዓለም በሞት በተለዩበት ወቅት ለባነር ማሠሪያ የወጣ ብር 3,500.00 (ሦስት ሺህ አምስት መቶ ብር) በድምሩ ፓርቲው ብር 38,500.00 (ሠላሳ ስምንት ሺህ አምስት መቶ ብር) " ከታለመለት ዓላማ እና ተግባር ውጭ ያወጣ መኾኑ" መመላከቱን አስረድቷል።

በዚህም ምክንያት ቦርዱ በዚህ ዓመት ፓርቲው የሚሰጠውን የመንግሥት ድጋፍ ሊያገኝ እንደማይገባ መወሰኑን ፤ የፓርቲውን ሂሳብ በጣምራ በሚያንቀሳቅሱት 3 አመራሮች ላይ ፌዴራል ፖሊስ ምርመራ እንዲያደርግ መወሰኑን በደብዳቤ እንደገለጸለት ጠቅሷል።

እናት ፓርቲ የቦርዱ ውሳኔ " አላግባብ ወጣ " ስለሚለው 38,500.00 ብር ሳይሆን ከጀርባው ሌላ ጉዳይ እንዳለው እገምታለሁ ብሏል።

" አላግባብ ወጣ " የተባለው ወጪ ፦

ብር 20,000 የመሬት መንሸራተት ለደረሰባቸው ወገኖች የወጣ እጅግ አነስተኛ ገንዘብ መሆኑና ይህም የነገ መራጮቹን ጎን ለሚጠይቀው የስብዕና ሞራል መቆም ከማስፈለጉ አኳያ ሊደረግ ከሚችል በጣም አነስተኛው ነገር እንደሆነ፤

ምንም ክፍያ ሳይከፈላቸው ለሀገራቸውና ሕዝባቸው ለመታገል ጊዜያቸውንና መላ እነሱነታቸውን ሰጥተው ለአደጋ ጭምር ራሳቸውን አጋልጠው የመጓጓዣ ወጪያቸው እንኳን ሳይሸፈን ለሀገር ከመቆም አኳያ በፓርቲው ከፍተኛ አመራርነት ያገለገሉ ከፓርቲው በሞት እንዲኹም በአካል ሲለዩ ወጣ የተባለው ወጪ እዚህ ግባ የማይባል መሆኑንና ከአግባብ ውጭ የወጣ ነው ብሎ እንደማያምን ገልጿል።

ከፓርቲው አመራር ቀብር ጋር ከተያያዘው ብር 3,500 ውጪ ሌሎቹ የተፈጸሙት ወጪዎች በፓርቲው ብሔራዊ ሥራ አስፈጻሚና መላ መዋቅሩ ውሳኔ መሠረት እንደሆነ ጠቁሟል።

ይህ ሆኖ ሳለ " አመራሮችን በተለየ መልኩ ተጠያቂ ለማድረግ የተኬደበት ርቀት ትናንት የፓርቲ አመራሮችና አባላት እሥርና አፈና ሲገጥማቸው ባሉበት ድረስ በመሄድ ያጽናና እና ለማስፈታት ግብ ግብ ይገጥም የነበረ ቦርድ በቅጽበት እንዲህ የመውጊያ ስለት አቀባይ ወደመሆን ያሽቆለቆለበት ቅጽበት ያስገርማል፣ ያሳዝናልም። የኢትዮጵያ ሕዝብም ይመዘግባል " ብሏል።

የተጠቀሰው ገንዘብ ፓርቲው በድጋፍ ከተሰጠው ገንዘብ ወጪ እንዲደረግ ያስገደደው ምክንያት በወቅቱ ፓርቲው ለማኅበራዊ አገልግሎት የሚጠቀምበትና ከአባላትና ደጋፊዎች የሚሰበሰብ ገንዘብ ከተቀመጠበት የባንክ ሒሳብ ማንቀሳቀስ ባለመቻሉና ገንዘቡ በወቅቱ ወጪ መደረግ የግድ ስለነበረ እንደሆነ አመልክቷል።

ነገር ግን የማኅበራዊ አገልግሎት የባንክ ሂሣቡን ማንቀሳቀስ በቻለበት በአሁኑ ሰዓት ግን የተጠቀሰውን በውንጀላ የተያዘበትን ገንዘብ ብር 38,500 አዛውሮ ዝግጁ ያደረገና ለመመለስም የሚችል መሆኑን ለፌዴራል ዋና ኦዲተር በፈረመው መተማመኛ ጽሑፍ መስጠቱን ገልጿል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ፓርቲው ጉዳዩን ቀለል አድርጎ ወደሥራው ባተኮረበት ወቅት ከዚህ ቀደም ' ፓርቲውን ከመፍረስ ለመታደግ በሚል ከፓርቲው የተቆረጠ ኃይል " ፓርቲውን በጀት አስከለከልኩ" ፣ " እነ እከሌንና እከሊትን ላሳስር ነው " እያለ ለተለያዩ ግለሰቦችና ሚዲያ አካላት ወሬ እየነዛ መመልከቱን በዚህም " በሬ ከአራጁ " ለማለት መገደዱን ገልጿል።

ይህን አካል ከነዝርዝር ማንነቱ በቅርቡ ለሕዝብ ይፋ እንደሚያደርግም ጠቁሟል።

ፓርቲው የመንግሥትን ሥልጣን በሕጋዊና ሰላማዊ መንገድ ለመጨበጥ እንደሚሰራ ገልጾ የገንዘብ አጠቃቀምን በተመለከተ እያንዳንዷ ሳንቲም ተጠያቂነት ባለው መልኩ ብቻ መውጣት እንዳለባት እንደሚያምን ለዚህም ተግቶ እንደሚሰራ ፤ ኦዲት መደረጉም እንደሚያስደስተው ገልጿል።

ነገር ግን የኦዲት ግኝት ተብሎ ነቀረበውና ቦርዱ ያሳለፈው ውሳኔ ከአስተዳደራዊ ውሳኔነቱ ይልቅ ፖለቲካዊ ግብ ያዘለ ነው ብሎ እንደሚያምን አመልክቷል።

" በቦርዱ ውሳኔ ላይ ዕለት ከዕለት የሚያስጨንቀንና ዘወትር የምንጮኽለት ወዲኽም ግራ ቀኝ ጥርስ ያስነከሰብን የሕዝባችን ስቃይ ከቀለለና ጊዜ ከተረፈን እንደአስፈላጊነቱ ሕጋዊ መንገድ ተከትለን ይግባኝ እንልበት ይሆናል " ብሏል።

ፓርቲው አለኝ ባለው መረጃ እንዳይሰጠው የታገደው የ2017 የበጀት ድጋፍ ብር 600 ሺህ ገደማ መሆኑን ጠቁሟል።

" በጀት በመከልከልና በማስከልከል የሚደናቀፍ ትግል አይኖርም " ሲልም አሳውቋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
542😡60👏53🙏31🕊17😭11🤔10😱1😢1