TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.9K photos
1.61K videos
216 files
4.37K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ዓለምአቀፍ

የሄይቲው ጠቅላይ ሚኒስትር በ6 ወራቸው ከስልጣናቸው ተባበሩ።

የሄይቲ ጠ/ሚ ጌሪ ኮኒል በ6 ወራቸው ከሥልጣን መባረራቸውን ሀገሪቱን የሚያስተዳድረው ም/ቤት አስታውቋል።

የምክር ቤቱ ዘጠኝ አባላት የፈረሙት ትዕዛዝ እንደሚያሳየው ከሥልጣን በተባረሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ምትክ ነጋዴ የሆኑትና የቀድሞ የሄይቲ ሕግ መወሰኛ ምክር ቤት አባል የነበሩት አሊክስ ዲዲዬን ሾሟል።

የቀድሞው የተባበሩት መንግሥታት ባልደረባ የነበሩት ኮኒል ወደ ሥልጣን የመጡት ሀገሪቱን ከታጠቁ ወሮበሎች እንዲታደጉ ነበር።

ሰውዬው በሄይቲ ምርጫ እስኪደረግ ድረስ ሥልጣን ላይ ይቆያሉ ተብሎ ቢጠበቅም በግማሽ ዓመት ከመንበራቸው ተባረዋል።

ሄይቲ ከአውሮፓውያኑ 2016 በኋላ ምርጫ አካሂዳ አታውቅም።

ሄይቲ በአሁኑ ወቅት ፕሬዝደንትም ሆነ ፓርላማ የላትም።

በሀገሪቱ ሕገ-መንግሥት መሠረት ጠቅላይ ሚኒስትሩን ከሥልጣን ማንሳት የሚችለው የሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ብቻ ነው።

ኮኒል ሥልጣን የያዙት ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር መጨረሻ ነበር።

እንደ ተመድ መረጃ ፤ በሄይቲ ካለፈው ጥር ጀምሮ በወሮበሎች አመፅ ምክንያት 3600 ሰዎች ሲገደሉ ግማሽ ሚሊዮን የሚሆኑት መኖሪያቸውን ጥለው ተሰደዋል።

በታጠቁ ወሮበሎች እየታመሰች ያለችው ሄይቲ በዓለማችን እጅግ ደሀ ከሚባሉ ሀገራት መካከል አንዷ ስትሆን እንደ ተመድ መረጃ ሁለት ሚሊዮን ዜጎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ከሀገሪቱ ሕዝብ ግማሽ ያክሉ በቂ ምግብ የለውም።

መረጃው የቢቢሲ ነው።

@tikvahethiopia
209👏54😭54🕊25😢18🙏14🤔13😱12🥰10
የትራምፕ የታሪፍ ጦርነት ወዴት ያመራ ይሁን ?

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሀገራት ላይ የሚጣል አዲስ ታሪፍ ይፋ ካደረጉ በኋላ በተለይም ከቻይና ጋር ተፋጠዋል።

ትራምፕ ከዚህ በፊት ሌሎች ሀገራት የአሜሪካ ምርቶች ላይ ከሚገባው በላይ ታሪፍ ጥለዋል ብለው እንደሚያምኑ እና ይህንን የሚስተካከል ታሪፍ እንደሚጥሉ ከተናገሩ በኋላ ነው አዲሱን ታሪፍ ያስተዋወቁት።

በመጀመሪያው ዙር ፕረዚዳንት ትራምፕ ከቻይና በሚገቡ ምርቶች ላይ 104 % ቀረጥ ጥለው የነበረ ሲሆን ቻይና በምላሿ (Reciprocal Tariff በተለምዶ አንድ ሃገር የሆነ ሃገር ላይ ታሪፍ ስትጥል በምላሹ ሌላኛዋ ሃገር የምትጥለው ታሪፍ) 84% ከአሜሪካ በሚገቡ እቃዎች ላይ ቀረጥ መጣሏን ገልጻለች።

አሜሪካ በቻይና ላይ የጣለችው ቀረጥ ዝርዝር ምን ይመስላል ?

➡️ 10% አዲስ ቤዝ ታሪፍ (ይህ በኢትዮጵያ እና በሌሎች ሀገራት ላይ የተጣለ ትንሹ ቀረጥ ነው)

➡️ 20% ነባር ታሪፍ

➡️ 34% ተመጣጣኝ / reciprocal ታሪፍ (በፊት ቻይና በአሜሪካ ላይ ጥላው የነበረችውን ታሪፍ መጠን ያክል)

➡️ 50% ለቻይና ያለፉት ድርጊቶች ቅጣት የተጣለ ታሪፍ ያካተተ ነው።

አሜሪካ ይህንን የታሪፍ ዝርዝር ይፋ ካደረገች በኋላ በርካታ ሀገራት ግብረ መልስ ቢሰጡም ዛሬ ከአሜሪካ በኩል የተሰማው መረጃ ተደራራቢ ታሪፍ የተጣለባቸው ሀገራት (ከ10 በመቶ በላይ) ከአሜሪካ መንግስት ጋር ለመነጋገር መጠየቃቸውን ይገልጻል።

በዚህም ምክንያት የአሜሪካ አስተዳደር ለ75 ሀገራት ከፍተኛ ሽኩቻ ውስጥ ገብታ የነበረችው ካናዳን ጨምሮ ሜክሲኮ፣ ጃፖን ፣ደቡብ ኮሪያ እና ለአውሮፖ አባል ሀገራት የ90 ቀን የታሪፍ እቀባ (አዲሱ ታሪፍ እንዳይፈጸም የተቀመጠ #የእፎይታ_ጊዜ) ሰጥቷል።

በዚህ ጊዜ ውስጥ እነዚህ 75 ሀገራት ከአሜሪካ መንግስት ጋር ድርድር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

በተቃራኒው ግን የቻይና መንግስት ለአሜሪካ አዲስ ታሪፍ ተመጣጣኝ ያለውን የ84 በመቶ ታሪፍ መጣሉን ባስታወቀ በሰዓታት ውስጥ አሜሪካ በቻይና ላይ የጣለችውን የታሪፍ መጠን ወደ 125 ከፍ አድርገዋለች።

ቻይና ከዚህ በተጨማሪ 18 የአሜሪካ ተቋማትን በተለይም ከወታደራዊ ምርት ጋር የተያያዙ ተቋማትን ዝርዝር በማውጣት እገዳ ጥላለች።

እንደ አማራጭም የቻይና የመገበያያ ገንዘብ የሆነው ይዋን (yuan) የመግዛት አቅምን ከዶላር አንጻር በማዳከም ምርቶቿ ይበልጥ በገቢያው ተወዳዳሪ እንዲሆኑም እየሰራች ነው።

ለምሳሌ ፦ አሜሪካ በቻይና ላይ የምትጥለው ታሪፍ የቻይናን ምርቶች የሚያስወድዱት ከሆነ የይዋን መዳከም ምርቶቹን ርካሽ ያደርጋቸዋል።

የዓለም ንግድ ድርጅት ይህ በዚህ ከቀጠለ የአሜሪካ-ቻይናን ንግድ እስከ 80% ሊቀንስ እንደሚችል አስጠንቅቋል።

#ቲክቫህኢትዮጵያ #ዓለምአቀፍ
@tikvahethiopia
700🤔191😭81🕊80🙏48👏39💔29🥰28😢20😡13😱5
TIKVAH-ETHIOPIA
#USA #China ቻይና በአሜሪካ ላይ አፀፋዊ የሆነ ተጨማሪ ታሪፍ ጥላለች። ቻይና ከዚህ በፊት ከአሜሪካ በሚገቡ ምርቶች ላይ የ84% ታሪፍ ጥላ የነበረ ሲሆን ዛሬ ሌላ ተጨማሪ ታሪፍ ጥላለች። የቻይና የፋይናንስ ሚኒስትር ከአሜሪካ በሚገቡ ዕቃዎች ላይ የተጣለው ታሪፍ ከ84% ወደ 125% ከፍ መደረጉን አስታውቀዋል። የትራምፕ አስተዳደር  በቻይና ላይ የተጣለው አጠቃላይ ታሪፍ 145% መሆኑን የገለፀ…
#USA #CHINA

የአሜሪካ እና የቻይና የታሪፍ ጦርነት !

ወደ አሜሪካ የሚገቡ የኤሌክትሮኒክስ ምርቶች ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቅርቡ ከጣሏቸው የአፀፋ ታሪፎች ነፃ መሆናቸውን የአሜሪካ የጉምሩክ ጉዳዮች ቢሮ አስታውቋል።

➡️ ስማርት ስልኮች፣
➡️ ኮምፒዩተሮች
➡️ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ክፍሎች ትራምፕ ከጣሉት ታሪፍ ነፃ መደረጋቸውም ተዘግቧል።

ውሳኔው የመጣው የፕሬዚዳንት ትራምፕ አስተዳደር በቻይና ላይ የ145% አጠቃላይ ታሪፍ መጣሉን ካስታወቀ በኋላ ሲሆን የታሪፉ መጣል እንደ አፕል ላሉ ግዙፍ የኤሌክትሮኒክ ምርት አምራቾች ስጋትን ፈጥሮም ነበር።

አፕል 90% የሚሆነውን የአይፎን ስልክ የሚያመርተው እና የሚገጣጥመው በቻይና ሲሆን ካውንተር ፖይንት የተሰኘው የጥናት ተቋም አፕል በአሜሪካ ያለው ክምችት ለ6 ሳምንታት ብቻ የሚሆን እንደሆነና እሱ ካለቀ የምርቱ ዋጋ መጨመር እንደሚጀምር ገልጾ ነበር።

አፕል ከአይፎን በተጨማሪ 80% የሚሆነውን አይፓድ እና ከ50% በላይ የሚሆነውን የማክ ኮምፒዩተር ምርቶቹን በቻይና እንደሚያመርት ተገልጿል።

አፕል ከግማሽ በመቶ በላይ የሚሆነውን የአይፎን ምርት የሚሸጠው በአሜሪካ እንደሆነ ሲነገር በቻይና ላይ ታሪፍ መጣሉን ተከትሎ አብዛኛውን ምርቱን በህንድ ማምረት ለመጀመር ማሰቡም ተነግሮ ነበር።

አፕል ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአፀፋ ታሪፍ በሃገራት ላይ መጣል ከጀመሩ በኋላ የገበያ ዋጋው በ640 ቢሊየን ዶላር መቀነሱ የተዘገበ ሲሆን ከ600 ቶን በላይ ክብደት ያላቸው 1.5 ሚሊየን የአይፎን ስልኮችንም ከህንድ ወደ አሜሪካ በአውሮፕላን አጓጉዞ ማስገባቱ መዘገቡ ይታወሳል።

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትናንትና አንዳንድ ምርቶች በሚታወቁ ምክንያቶች እሳቸው ከጣሉት ታሪፍ ነፃ ሊሆኑ እንደሚችሉ ተናግረው ነበር።

ትራምፕ በጣሉት ታሪፍ የተነሳ የአይፎን ስልክ ዋጋ በሶስት እጥፍ ሊጨምር እንደሚችል ስጋቶች የነበሩ ቢሆንም አሁን ላይ የኤሌክትሮኒክስ ምርቶቹ ከአፀፋዊ ታሪፉ ነፃ መሆን ትልቅ ዕድል እንደሚሆን ተዘግቧል።

በውሳኔው መሰረትም #ሳምሰንግን ጨምሮ ሌሎች አለም አቀፍ የኤሌክትሮኒክስ አምራቾች ወደ አሜሪካ ምርታቸውን ሲልኩ ይጠብቃቸው ከነበረው የ10% መሰረታዊ ታሪፍም ነፃ መሆናቸው ተነግሯል።

ከታሪፉ ነፃ የሆኑ 20 የምርት ዘርፎች የተቀመጡ ሲሆን ለሴሚ ኮንዳክተር መሳሪያነት የሚያገለግሉ ማሽኖችም ከታሪፉ ነፃ መሆናቸው ታውቋል።

ኋይት ሃውስ፣ የአሜሪካ የአለም አቀፍ ንግዶች ኮሚሽን እና የአሜሪካ የንግድ ቢሮ በጉዳዩ ላይ እስካሁን አስተያየት አልሰጡም።

#ዓለምአቀፍ #የታሪፍጦርነት #ቻይና #አሜሪካ

@tikvahethiopia
304🤔76🙏24👏21💔16🕊14😭13🥰10😡10😢4😱2