TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.9K photos
1.61K videos
216 files
4.37K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የትራምፕ የታሪፍ ጦርነት ወዴት ያመራ ይሁን ?

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሀገራት ላይ የሚጣል አዲስ ታሪፍ ይፋ ካደረጉ በኋላ በተለይም ከቻይና ጋር ተፋጠዋል።

ትራምፕ ከዚህ በፊት ሌሎች ሀገራት የአሜሪካ ምርቶች ላይ ከሚገባው በላይ ታሪፍ ጥለዋል ብለው እንደሚያምኑ እና ይህንን የሚስተካከል ታሪፍ እንደሚጥሉ ከተናገሩ በኋላ ነው አዲሱን ታሪፍ ያስተዋወቁት።

በመጀመሪያው ዙር ፕረዚዳንት ትራምፕ ከቻይና በሚገቡ ምርቶች ላይ 104 % ቀረጥ ጥለው የነበረ ሲሆን ቻይና በምላሿ (Reciprocal Tariff በተለምዶ አንድ ሃገር የሆነ ሃገር ላይ ታሪፍ ስትጥል በምላሹ ሌላኛዋ ሃገር የምትጥለው ታሪፍ) 84% ከአሜሪካ በሚገቡ እቃዎች ላይ ቀረጥ መጣሏን ገልጻለች።

አሜሪካ በቻይና ላይ የጣለችው ቀረጥ ዝርዝር ምን ይመስላል ?

➡️ 10% አዲስ ቤዝ ታሪፍ (ይህ በኢትዮጵያ እና በሌሎች ሀገራት ላይ የተጣለ ትንሹ ቀረጥ ነው)

➡️ 20% ነባር ታሪፍ

➡️ 34% ተመጣጣኝ / reciprocal ታሪፍ (በፊት ቻይና በአሜሪካ ላይ ጥላው የነበረችውን ታሪፍ መጠን ያክል)

➡️ 50% ለቻይና ያለፉት ድርጊቶች ቅጣት የተጣለ ታሪፍ ያካተተ ነው።

አሜሪካ ይህንን የታሪፍ ዝርዝር ይፋ ካደረገች በኋላ በርካታ ሀገራት ግብረ መልስ ቢሰጡም ዛሬ ከአሜሪካ በኩል የተሰማው መረጃ ተደራራቢ ታሪፍ የተጣለባቸው ሀገራት (ከ10 በመቶ በላይ) ከአሜሪካ መንግስት ጋር ለመነጋገር መጠየቃቸውን ይገልጻል።

በዚህም ምክንያት የአሜሪካ አስተዳደር ለ75 ሀገራት ከፍተኛ ሽኩቻ ውስጥ ገብታ የነበረችው ካናዳን ጨምሮ ሜክሲኮ፣ ጃፖን ፣ደቡብ ኮሪያ እና ለአውሮፖ አባል ሀገራት የ90 ቀን የታሪፍ እቀባ (አዲሱ ታሪፍ እንዳይፈጸም የተቀመጠ #የእፎይታ_ጊዜ) ሰጥቷል።

በዚህ ጊዜ ውስጥ እነዚህ 75 ሀገራት ከአሜሪካ መንግስት ጋር ድርድር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

በተቃራኒው ግን የቻይና መንግስት ለአሜሪካ አዲስ ታሪፍ ተመጣጣኝ ያለውን የ84 በመቶ ታሪፍ መጣሉን ባስታወቀ በሰዓታት ውስጥ አሜሪካ በቻይና ላይ የጣለችውን የታሪፍ መጠን ወደ 125 ከፍ አድርገዋለች።

ቻይና ከዚህ በተጨማሪ 18 የአሜሪካ ተቋማትን በተለይም ከወታደራዊ ምርት ጋር የተያያዙ ተቋማትን ዝርዝር በማውጣት እገዳ ጥላለች።

እንደ አማራጭም የቻይና የመገበያያ ገንዘብ የሆነው ይዋን (yuan) የመግዛት አቅምን ከዶላር አንጻር በማዳከም ምርቶቿ ይበልጥ በገቢያው ተወዳዳሪ እንዲሆኑም እየሰራች ነው።

ለምሳሌ ፦ አሜሪካ በቻይና ላይ የምትጥለው ታሪፍ የቻይናን ምርቶች የሚያስወድዱት ከሆነ የይዋን መዳከም ምርቶቹን ርካሽ ያደርጋቸዋል።

የዓለም ንግድ ድርጅት ይህ በዚህ ከቀጠለ የአሜሪካ-ቻይናን ንግድ እስከ 80% ሊቀንስ እንደሚችል አስጠንቅቋል።

#ቲክቫህኢትዮጵያ #ዓለምአቀፍ
@tikvahethiopia
700🤔191😭81🕊80🙏48👏39💔29🥰28😢20😡13😱5