TIKVAH-ETHIOPIA
#USA #China ቻይና በአሜሪካ ላይ አፀፋዊ የሆነ ተጨማሪ ታሪፍ ጥላለች። ቻይና ከዚህ በፊት ከአሜሪካ በሚገቡ ምርቶች ላይ የ84% ታሪፍ ጥላ የነበረ ሲሆን ዛሬ ሌላ ተጨማሪ ታሪፍ ጥላለች። የቻይና የፋይናንስ ሚኒስትር ከአሜሪካ በሚገቡ ዕቃዎች ላይ የተጣለው ታሪፍ ከ84% ወደ 125% ከፍ መደረጉን አስታውቀዋል። የትራምፕ አስተዳደር በቻይና ላይ የተጣለው አጠቃላይ ታሪፍ 145% መሆኑን የገለፀ…
#USA #CHINA
የአሜሪካ እና የቻይና የታሪፍ ጦርነት !
ወደ አሜሪካ የሚገቡ የኤሌክትሮኒክስ ምርቶች ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቅርቡ ከጣሏቸው የአፀፋ ታሪፎች ነፃ መሆናቸውን የአሜሪካ የጉምሩክ ጉዳዮች ቢሮ አስታውቋል።
➡️ ስማርት ስልኮች፣
➡️ ኮምፒዩተሮች
➡️ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ክፍሎች ትራምፕ ከጣሉት ታሪፍ ነፃ መደረጋቸውም ተዘግቧል።
ውሳኔው የመጣው የፕሬዚዳንት ትራምፕ አስተዳደር በቻይና ላይ የ145% አጠቃላይ ታሪፍ መጣሉን ካስታወቀ በኋላ ሲሆን የታሪፉ መጣል እንደ አፕል ላሉ ግዙፍ የኤሌክትሮኒክ ምርት አምራቾች ስጋትን ፈጥሮም ነበር።
አፕል 90% የሚሆነውን የአይፎን ስልክ የሚያመርተው እና የሚገጣጥመው በቻይና ሲሆን ካውንተር ፖይንት የተሰኘው የጥናት ተቋም አፕል በአሜሪካ ያለው ክምችት ለ6 ሳምንታት ብቻ የሚሆን እንደሆነና እሱ ካለቀ የምርቱ ዋጋ መጨመር እንደሚጀምር ገልጾ ነበር።
አፕል ከአይፎን በተጨማሪ 80% የሚሆነውን አይፓድ እና ከ50% በላይ የሚሆነውን የማክ ኮምፒዩተር ምርቶቹን በቻይና እንደሚያመርት ተገልጿል።
አፕል ከግማሽ በመቶ በላይ የሚሆነውን የአይፎን ምርት የሚሸጠው በአሜሪካ እንደሆነ ሲነገር በቻይና ላይ ታሪፍ መጣሉን ተከትሎ አብዛኛውን ምርቱን በህንድ ማምረት ለመጀመር ማሰቡም ተነግሮ ነበር።
አፕል ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአፀፋ ታሪፍ በሃገራት ላይ መጣል ከጀመሩ በኋላ የገበያ ዋጋው በ640 ቢሊየን ዶላር መቀነሱ የተዘገበ ሲሆን ከ600 ቶን በላይ ክብደት ያላቸው 1.5 ሚሊየን የአይፎን ስልኮችንም ከህንድ ወደ አሜሪካ በአውሮፕላን አጓጉዞ ማስገባቱ መዘገቡ ይታወሳል።
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትናንትና አንዳንድ ምርቶች በሚታወቁ ምክንያቶች እሳቸው ከጣሉት ታሪፍ ነፃ ሊሆኑ እንደሚችሉ ተናግረው ነበር።
ትራምፕ በጣሉት ታሪፍ የተነሳ የአይፎን ስልክ ዋጋ በሶስት እጥፍ ሊጨምር እንደሚችል ስጋቶች የነበሩ ቢሆንም አሁን ላይ የኤሌክትሮኒክስ ምርቶቹ ከአፀፋዊ ታሪፉ ነፃ መሆን ትልቅ ዕድል እንደሚሆን ተዘግቧል።
በውሳኔው መሰረትም #ሳምሰንግን ጨምሮ ሌሎች አለም አቀፍ የኤሌክትሮኒክስ አምራቾች ወደ አሜሪካ ምርታቸውን ሲልኩ ይጠብቃቸው ከነበረው የ10% መሰረታዊ ታሪፍም ነፃ መሆናቸው ተነግሯል።
ከታሪፉ ነፃ የሆኑ 20 የምርት ዘርፎች የተቀመጡ ሲሆን ለሴሚ ኮንዳክተር መሳሪያነት የሚያገለግሉ ማሽኖችም ከታሪፉ ነፃ መሆናቸው ታውቋል።
ኋይት ሃውስ፣ የአሜሪካ የአለም አቀፍ ንግዶች ኮሚሽን እና የአሜሪካ የንግድ ቢሮ በጉዳዩ ላይ እስካሁን አስተያየት አልሰጡም።
#ዓለምአቀፍ #የታሪፍጦርነት #ቻይና #አሜሪካ
@tikvahethiopia

❤304🤔76🙏24👏21💔16🕊14😭13🥰10😡10😢4😱2