TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update
" ዛሬ ወሬ የለም " - ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ
የሃይማኖት አባቶች ልዑክ በመቐለ !
ከአዲስ አበባ ተነስቶ በጥዋቱ ትግራይ ክልል መቐለ አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፍያ የደረሰው የሃይማኖት አባቶች ልዑክ ከሁሉም የሃይማኖት ተቋማት የተወጣጣ ሲሆን አጠቃላይ ልዑኩ ከ20 በላይ አባላት አሉት።
የሰላም ልኡኩ ከአውሮፕላን ማረፍያ በቀጥታ ወደ መቐለ ፕላኔት ሆቴል አዳራሽ በማመራት በፕሬዜዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀነራል) ከሚመራው የጊዚያዊ አስተዳደሩ የካቢኔ አባላት ጋር #በዝግ ተወያይቷል።
ፕሬዜዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጄነራል) ከሰላም ልኡካኑ ጋር የነበራቸውን ቆይታ አጠቃልለው ሲወጡ የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ የሚገኙባቸው የጋዜጠኞች ቡድን መረጃ ፍለጋ ተጠግተው ነበር።
ፕሬዝዳንቱ በሳቅ ታጅበው " ዛሬ ወሬ የለም " በማለት ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል።
የሰላም ልኡኩ በሆቴሉ ጥቂት ደቂቃዎች እረፍት ወስዶ መልሶ በተመሳሳይ አዳራሽ ከትግራይ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ ተወካዮች ጋር ተወያይቷል።
በዚሁ ወቅት በቦታው ላይ የነበሩ ጋዜጠኞች ውይይቱን ለመከታተል ጥያቄ ቢያቀርቡም መከታተል ይቅርና አዳራሹ ውስጥ እንዳይዘልቁና ፎቶም እንዳያነሱ ተከልክለዋል።
ከሰዓት በኃላ ከውይይቱ ተሳታፊዎች በተገኘው መረጃ የሰላም ልኡካኑ በመጠለያ ጣቢያዎች የሚገኙ ተፈናቃዮች ጎብኝተው የማወያየት ፕሮግራም የነበራቸው ቢሆንም ባልታወቀ ምክንያት ይሄ ፕሮግራም ሳይካሄድ ቀርቷል።
የሰላም ልኡኩ ቀጥሎ ከህወሓት ከፍተኛ አመራሮች ነው የተወያየው። ውይይቱ እንደ ጠዋቱ #በዝግ መካሄዱን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተረድቷል።
የድርጅቱ / የህወሓት ልሳን የሆነው የወይን ጋዜጣ ጋዜጠኞችም ጭምር ወደ ስብሰባው አዳራሽ እንዳይገቡ ተከልክለው ነው ውይይቱ የተካሄደው።
ከአዲስ አበባ የተጓዘው የሰላም ልኡክ ያካሄዳቸው የውይይቱ ርእሰ ጉዳዮች አልታወቁም። ከግምት ባሻገር የተሰጠ ይፋዊ መረጃ የለም።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ መቐለ የሰላም ልኡኩ ቀኑን ሙሉ ከተለያዩ አካላት ጋር ያካሄደውን ውይይት በማስመልከት የሚሰጥ ጋዜጣዊ መግለጫ ይኖር እንደሆነ ለጊዚያዊ አስተዳደሩ የሚድያ ዴስክ ጠይቆ ያገኘው አመርቂ መልስ የለም።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
ፎቶ፦ ትግራይ ቴሌቪዥን
@tikvahethiopia

❤877🕊179🤔51😡31😢22🙏17👏14🥰9😭6