TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.3K photos
1.62K videos
218 files
4.4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#REFERENDUM

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርዱ አስቀድሞ ባወጣው የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ አፈጻጸም መርሀ ግብር መሰረት የተለያየ ሀላፊነት ያላቸው የህግ አስፈጻሚ እና የጸጥታ አካላት እና የቦርዱ የስራ አመራር አባላት የህዝበ ውሳኔውን አፈጻጸም ሰላማዊነት ማረጋገጥ አስመልክቶ መስከረም 07/2012 ዓ.ም ውይይት አካሂደዋል፡፡

በውይይቱም የፌደራል ፓሊስ ተወካዮች ፣ የደቡብ ብ/ብ/ህ ክልል ፓሊስ ኮሚሽን ተወካዮች፣ በክልሉ የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት ሀላፊ፣ የሃዋሳ ከተማ ፓሊስ አዛዥ፣ የሲዳማ ዞን ፓሊስ ሀላፊ, የክልሉ የአስተዳደር እና ጸጥታ ቢሮ ጽ/ቤት ሃላፊ ተገኝተው ሰፊ ውይይት ተደርጓል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-19-4
#REFERENDUM

በሀዋሳ ከተማ በ166 የምርጫ ጣቢያዎች እድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ከ190000 (ከመቶ ዘጠና ሺህ) በላይ ሰው ድምፅ ይሰጣል ተብሎ ዕቅድ ተይዟል!

በሲዳማ ብሔር የክልልነት ጥያቄ ማስፈፀሚያ ዕቅድ እና አተገባበር ዙሪያ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ገለፃ አደረገ
በሀገር ደረጃ ለአስተዳደራዊ ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ለመጀመሪያ ጊዜ የሲዳማ ብሔር የክልልነት ጥያቄ ህዝበ ውሳኔ ህዳር 3 ቀን 2012 ዓ.ም እንደሚካሄድ ይታውቋል፡፡

በዚህ መነሻ በተደረገው ገለፃ በከተማ አስተዳደሩ በሁሉም እርከን የሚገኘው አመራር የተሳተፈ ሲሆን የሲዳማ ብሔር ክልል የመሆን ጥያቄ ህዝበ ውሳኔ መላውን ህዝብ ያሳተፈ፣ ፍፁም ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የከተማ አመራሩ እንደሚሰራ ተገልጿል፡፡

የሲዳማን የክልልነት ጥያቄ ህዝበ ውሳኔ ለማካሄድ ከተቋቋሙ 19 የድምፅ መስጫ ክልልሎች አንዷ በሆነችው ሀዋሳ ከተማ በ166 የምርጫ ጣቢያዎች እድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ከ190000 (ከመቶ ዘጠና ሺህ) በላይ ሰው ድምፅ ይሰጣል ተብሎ ዕቅድ ተይዟል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-25-8

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Referendum ነዋሪዎች ከለሊት ጀምሮ በመሰለፍ በተለያዩ ድምፅ መስጫ ጣቢዎች ሰላማዊ በሆነ መንገድ ድምፅ በመስጠት ላይ ይገኛሉ። ቲክቫህ ኢትዮጵያ በአጠቃላይ በሁሉም ምርጫ ጣቢያዎች ያለውን እንቅስቃሴ እየተከታተለ የሚያሳውቃችሁ ይሆናል።

PHOTO : TIKVAH FAMILY

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia