TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.2K photos
1.62K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ፎቶ📸ትላንት ለሊት የእሳት አደጋ የደረሰበት የአዲስ አበባ አቃቂ ገበያ ስፍራ አሁን ያለበት ሁኔታ ከላይ በፎቶው የምትመለከቱትን ይመስላል። #Amir/TIKVAH-ETH/

@tsegabwolde @tikvahethiopia
🌼🌼እንኳን ለአዲሱ ዐመት በሰለም አደረሳችሁ🌼🌼
ዘ-ስፕሪንት የቴክኖሎጂ ማሰልጠኛ ተቋም
የምንሰጣቸው ስልጠናዎች (በከፊል)
√የሞባይል ጥገና ስልጠና
√የቢሮ ማሽኖች ጥገና ስልጠና
√የኤሌክሮኒክስ ዕቃዎች ጥገና ስልጠና
√የኮምፒውተርና ላፕቶፕ ጥገና ስልጠና
√የዲሽ ኢንስታሌሽን ስልጠና
√ቢውልዲንግ ኤሌክትሪካል ኢንስታሌሽን ስልጠና
√የደህንነት ካሜራ (CCTV) ገጠማ ስልጠና የቋንቋ እና ኮምፒውተር ስልጠና - አሁኑኑ ይመዝገቡ! የምዝገባ ቦታ፦
#1. ጆሞ አንድ፤ ሳባ ህንፃ 2ኛ ፎቅ 202
#2. መካኒሳ፤ ማይ ፒክ ህንጻ 3ኛ ፎቅ
#3. መገናኛ፤ ገነት ኮመርሻል ሴንተር 6ኛ ፎቅ
👇📱መገናኛ 0982808080፣ ጀሞ 0912880149 እና መካኒሳ 0940414243 ደውለው ይመዝገቡ! ሙሉ ዕውቅና ያለው 💯
@zsprint ላይ ቻናላችንን ይቀላቀሉ በ @zsprintcomputer ላይ እኛን ያገኙናል! ይመዝገቡ!
🌼🌼እንኳን ለአዲሱ ዐመት በሰለም አደረሳችሁ🌼🌼
1
በሲዳማ ዞን ሸበዲኖ ወረዳ 1ሚሊዮን 500ሺህ ብር ግምት ያለው የኮንትሮባንድ እቃ ተያዘ። በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሀዋሳ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የህግ ተገዥነት ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ዴሳ ለማ ዛሬ እንደገለጹት ልባሽ ጨርቅ የሆነው የኮንትሮባንድ እቃው ከህዝብ በደረሰ ጠቆማ መሰረት ትናንት ሌሊት ሊይዝ ችሏል። የተገኘውም ከኬንያ በሀገረ ሰላም በኩል ወደ ሀዋሳ ለማስገባት በሸበዲኖ ወረዳ በሶስት ቤቶች ውስጥ ተከማችቶ እንደሆነ አመልክተው አሮጌ የሆነው ይሄው ልባሽ ጨርቅ ወደ ሀገር እንዳይገባ በመንግስት እገዳ የተጣለበት እንደሆነ ተናግረዋል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በምዕራብ ጉጂ ዞን ቡሌ ሆራ ከተማ 335 ለሚሆኑ ወላጅ አልባ እና ችግርተኛ ለሆኑ ተማሪዎች የመማርያ ቁሣቁሦችን መሥጠቱን የቡሌ ሆራ ከተማ ማዛጋጃ ቤት እና የከተማው ሴቶች እና ህፃናት ቢሮ በቅንጅት እየሠራ መሆኑን ገልጿል።

Via Gemede Tamiru/ Bule Hora/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#New

የአዲስ አበባ  ዩኒቨርሲቲ ነባር የመደበኛ ተማሪዎች በሙሉ!

TIKVAH ETH MAGAZINE የዩኒቨርሲቲ ጥሪዎችን ብቻ በዚህ ተከታተሉ👇
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAEcez-UrldBjOpa-qQ

#ቲክቫህ_ዩኒቨርስቲ
@tikvahethmagazine
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርት መስከረም 8 ይጀምራል!

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የቅድመ  ምረቃ ነባር ተማሪዎች ምዝገባ መስከረም 5 እና መስከረም 6  2012 ዓ.ም ለመሆን ሆኑን ገልጿል።  ነባር የድህረምረቃ ተማሪዎች ምዝገባ ድግሞ መስከረም 7 ቀን 2012 ዓ.ም መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ትምህርት የሚጀመረዉ ሐሙስ መስከረም 8 ቀን 2012 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

http://www.aau.edu.et/blog/registration-of-year-2nd-and-above-undergraduate-and-graduate-regular-students/

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ
ሬጅስትራር

TIKVAH ETH MAGAZINE የዩኒቨርሲቲ ጥሪዎችን ብቻ በዚህ ተከታተሉ👇
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAEcez-UrldBjOpa-qQ

@tikvahethmagazine
👍1
ፎቶ📸ውጭ ጉዳይ ምኒስትሩ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው "ከሩሲያው አቻቸው ሰርጌ ላቭሮቭ በቀረበላቸው ግብዣ መሰረት" ለሥራ ጉብኝት ሞስኮ ገብተዋል። የመከላከያ ምኒስትሩ አቶ ለማ መገርሳ አብረው ተጉዘዋል። ሁለት ወታደራዊ መኮንኖች ከልዑካን ቡድኑ መካከል ይታያሉ።

Via #EsheteBekele
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ በአማራ ክልል ለ4 ሺህ 329 ታራሚዎች #ይቅርታ ተደርጓል።

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ደቡብ ክልል አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ለ2 ሺህ 366 ታራሚዎች ይቅርታ አድርጓል። የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ርስቱ ይረዳው ዛሬ ከሰዓት በሰጡት መግለጫ፥ ክልሉ አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ለ2 ሺህ 366 ታራሚዎች ይቅርታ ማድረጉን አስታውቀዋል።

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Breaking ጋዜጠኛ በሪሁን ከእስር ተፈቷል!

ላለፉት ሦስት ወራት በእስር ላይ የቆየው የአሥራት ሚዲያ መስራች አባል ጋዜጠኛ በሪሁን አዳነ ዛሬ ከእስር ተፈቷል።

Via #AsratTV
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የድርጊት መርሃ ግብር .pdf
203.4 KB
የሲዳማ ዞን የክልልነት ጥያቄን አስመልክቶ/ሪፈረንደም/የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያዘጋጀው የድርጊት መርሃግብር!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
1 ሺህ 87 ታራሚዎች በይቅርታ ይለቀቃሉ!

አዲሱን አመት ምክንያት በማድረግ 1 ሺህ 87 የፌደራል ታራሚዎች በይቅርታ ይለቀቃሉ። የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ እንደገለፁት፥ በአዲሱ አመት 2012 ከሁሉም የፌደራል ማረሚያ ቤቶች በድምሩ 1 ሺህ 87 ታራሚዎች በነገው እለት በይቅርታ ይወጣሉ። ከዚህ ውስጥ 367 ከቃሊቲ፣ 28 ከዝዋይ እና 439ኙ ደግሞ ከሸዋሮቢት ማረሚያ ቤቶች መሆናቸውን ተናግረዋል። አዲሱን አመት ምክንያት በማድረግ በይቅርታ የሚለቀቁ ታራሚዎች በህግ ይቅርታ የማይጠየቅባቸው ወንጀሎችን ፈፅመዋል ተብለው በማረሚያ ቤት የቆዩ ናቸው።

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በድንገተኛ ፍተሻ 7.6 ሚሊዮን በላይ ብር፤ 53 ሺሕ ዶላር እና የተለያዩ ሃገራት ገንዘቦች በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ መያዙን ፖሊስ አስታውቋል። የአዲስ አበባ ፖሊስ እንዳለው በሕገ-ወጥ የውጭ ምንዛሪ ግብይት የተጠረጠሩ 10 ሰዎች ተይዘዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሳዛኝ ዜና!

በምዕራብ ሸዋ ዞን የጊቤ ወንዝን #በመሻገር ላይ የነበሩ አምስት ሰዎች በውሃው ተወስደው ህይወታቸው ማለፉን የዞኑ ኮሙዩኔኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አስታወቀ። አደጋው የደረሰው ሰሞኑን  እየጣለ ያለው ከባድ ዝናብ ተከትሎ ወንዙ ሞልቶ በመፍሰሱ ነው፡፡ የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ #ጉታ_ባልቻ እንደገለጹት ህይወታቸው ያለፈው ባለፈው ቅዳሜ ዳኖ ወረዳ ውስጥ ሰዮ ከተማ ገበያ ውለው ወደ ቤታቸው በመመለስ ላይ ከነበሩ 12 ሰዎች መካከል ነው። በወንዙ ላይ የጓዙበት የነበረው ባህላዊ ጀልባ በመገልበጡ አምስት ሰዎች በውሃው ተወስደው  ህይወታቸው ሊልፍ ችሏል፡፡ “ከሟቾቹ መካከል የሶስት ሰዎች አስክሬን ተገኝቷል፤ የቀሪዎቹ እስከዛሬም አልተገኘም” ብለዋል፡፡ አስክሬናቸው የተገኘው ቤተሰቦቻቸው እንዲረከቡ መደረጉን አመልክተዋል። የጊቤ ወንዝ ወደ ጅማና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን የሚያልፍና ወንዙ ድልድይ ስለሌለው የአካባቢውን ህብረተሰብ እየጎዳ መሆኑን አቶ ጉታ ጠቁመዋል፡፡

Via ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ADDISABEBA

ደህንነታቸው፣ ፈዋሽነታቸው፣ ጥራታቸው ያልተረጋገጡ መድኃኒቶች በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በኩል ሊገቡ ሲል ተያዙ።፡ የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን በቦሌ ዓለም ቀፍ አሮፕላን ማረፊያ በሃገር ውስጥ በረራ የመግቢያ መውጫ ኬላ ከገቢዎችና ጉምሩክ ጋር ባደረገው ቁጥጥር መድኃኒቶቹን መያዙን አስታውቋል። መድኃኒቶቹ በሁለት የውጭ ሀገር ዜጎች ለመግባት ሲሞክሩ የተያዙ ሲሆን፥ በህገወጥ መልኩ ከጎዴ ወደ አዲስ አበባ ሲገቡ የተያዙ ናቸው።

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
😢1
#JIMMA---በጅማ ከተማ ከቀን ጀምሮ በአንዳንድ አከባቢዎች አለመረጋጋት እና ውጥረት እንዳለ እንዲሁም የሚመለከታቸው አካላትም ትኩረት እንዲሰጡ በርካታ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት እየጠቆሙ ይገኛሉ።

በዛሬው ዕለት በጅማ ከተማ ምንተፈጥሮ ነበር?
የተጣራና ዝርዝር መረጃ ከከተማይቱ ነዋሪዎች እንዲሁም ከከተማው የፀጥታ ኃላፊዎች ጠይቀን የምናቀርብ ይሆል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የዋጋ ጭማሪ መቆሚያው የት ይሆን?

በጤፍ ላይ በኩንታል ከ400 እስከ 800 ብር፤ በስንዴ ላይ በኩንታል ከ300 እስከ 600 ብር፤ እንዲሁም በአትክልትና ሽንኩርት ላይ በኪሎ ከ10 እስከ 18 ብር ጭማሪ መደረጉ ከታህሳስ 2011 ጀምሮ የታየ ችግር ሆኗል።

ከዓመት ዓመት መባሉ ቀርቶ ከዕለት ዕለት ከፍ ሲል እንጂ ባለበት እንኳን መርጋት የተሳነው የሸቀጦች ዋጋ ሰፊውን በተለይም ዝቅተኛ ገቢ ያለውን አብዛኛውን የህብረተሰብ ክፍል እጅጉን ፈትኖታል። ለከፋ ምሬትና እሮሮም ዳርጎታል።

ይህ የዋጋ ማሻቀብ ሂደትም የዘርፉ ባለሙያዎች እንደሚሉት ከአንድ አሃዝ አልፎ ሁለት አሃዝ የደረሰ፤ ከ15 በመቶ የተሻገረ ነው። ይህ ሂደት ደግሞ በወጉ ተለይቶና ታቅዶ እንደየባህሪው ሊሰራበትና ሊፈታ ካልቻለ፤ የደላሎችና ሕገወጦችን ኪስ የሚያደልብ፤ የድሆችን ረሃብ በማጽናት ለብሶት የሚዳርግና የሰፊውን ህዝብ ትዕግስት አስጨርሶ ለአመፅ የሚያነሳሳ፤ ሕገወጦች የሰበሰቡትን ሃብት ቁጭ ብለው የሚበሉበትን ስፍራም የሚያሳጣ እንደሆነ ያስገነዝባሉ።

ተጨማሪ👇
https://telegra.ph/ETH-09-09-3
#ET302

ከኢትዮጵያ ወደ ኬኒያ ሲያመራ በተከሰከሰው ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን አደጋ ሕይወታቸው ያለፈው ሰዎችን ማንነት የመለየት ስራ ተጠናቀቀ፡፡ ከስድስት ወር በፊት ከኢትዮጵያ ወደ ኬኒያ ሲያመራ የነበረውና በኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ቁጥር ኢቲ 302 የሆነው ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን ተከስክሶ በውስጡ የነበሩ መንገደኞች መሞታቸው ይታወሳል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-09-4
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የመን አላርም ትሁነን!

•ከ70 ሺህ በላይ ንፁሃን ህይወታቸውን አጥተዋል!
•ከ11 ሺህ በላይ ዜጎች አካላቸው ጎድሏል!
•24 ሚሊዮን ዜጎች አስቸኳይ ሰብዓዊ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል!
•ባለፉት 3 ዓመታት ውስጥ ብቻ 85 ሺህ እድሜያቸው ከ5 ዐመት በታች የሆኑ ህፃናት በምግብ እጥረት ሞተዋል!
•በርካታ ሚሊዮን ዜጎች ቤታቸውን ንብረታቸውን ጥለው ተሰደዋል!

ብልቂሳ አብደላ ከ20 ዓመታት በላይ በየመን ነዋሪ ናት ይህንን ብላለች፦ "ወላሂ! የጦርነት ጥሩ ነገር የለም፤ የመንን ያየ... ሰላም የሆነውን ሀገር ባያደፈርሱ ጥሩ ነው። ...ኢትዮጵያ ችግር አለ ሲባል የመንን፣ ሶሪያን፣ ኢራቅን አላዩም ወይ...የመን እንኳን አንድ ቋንቋ፤ አንድ ሃይማኖት ነው፤ ይሄ ደግሞ የተለያየ ስላለ ከጀመረ የሚያቆም አይመስለኝም"

የመን ለምን እንዲሆነች??
•አለመደማመጥ
•ምክንያታዊ ሆኖ አለማሰብ

#የመናውያን መነጋገርና መደራደር የሚለውን #አማራጭ ባለመተግበራቸው ለዚህ ችግር ተጋልጠዋል። ጦርነት ሩቅ አይደለም፤ በፖለቲካና በሃይማኖት መካረሩ መዳረሻው ግልፅ ነው👉ጦ ር ነ ት!

#TIKVAH_ETHIOPIA

Via #SRTA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#JIMMA ጅማ ከተማ ቤተክርስቲያን #ተቃጠለ፤ አገልጋዮችም እየታረዱና እየተገደሉ ነው፤ በሚል በፌስቡክ የሚሰራጨው መረጃ ፍፁም ከእውነት የራቀ መሆኑን የጅማ ዞን ኮሚኒኬሽን አሳውቋል። ይህን ስራ እየሰሩ ያሉት ምንም ኃላፊነት የማይሰማቸው አካላት ናቸው ያለው የጅማ ዞን ኮሚኒኬሽን በከተማይቱ ውስጥ ንብረት አልወደመም ሰዎች ላይም ጉዳት አልደረሰም፤ እየተናፈሰ ያለውም በሬ ወለደ ፕሮፖጋንዳ በመልቀቅ ህዝቡን ማደናበር ነው ብሏል። በመሆኑም ሁሉም አካላት የጉዳዩን ጥንስስ አላማን በመረዳት ዋስትና ለሆነዉ ሰላምና አንድነት ተግቶ በመስራት ጅማን #ወደቀድሞ ሰላሟ ለመመለስ እየተደረገ ላለዉ ርብርብ የድርሻውን እንዲወጣ ዞኑ ጥሪ አስተላልፏል።

የጅማ ዞን ኮሚኒኬሽን⬆️
_______________________________________

ከጅማ ከተማ ጋር በተያያዘ ተጨማሪ ዝርዝር እና የተጣሩ መረጃዎችን ይዘን እንመለሳለን፦

•ዛሬ በከተማይቱ አንዳንድ አካባቢዎች ለተፈጠረው ውጥረት ምክንያቱ ምንድነው?
•በእርግጥ በከተማው በአሁን ሰዓት በፌስቡክ ላይ እየተወራ እንዳለው የከፋ እና አስጊ ችግር አለ?

📑የከተማይቱን ነዋሪዎች፣ በስፍራው የነበሩ የአይን እማኞች እንዲሁም የከተማው የፀጥታ ኃላፊዎች ስለተፈጠረው ሁኔታ ምን ይላሉ? የሚለውን እንዳዘጋጀንና እንደጨረስን ተጨማሪ መረጃ እናቀርባል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
1