#NEW
በ2011 ዓ.ም የመሰናዶ ት/ታችሁን አጠናቅቃችሁ የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና ላለፋችሁ ተማሪዎች በሙሉ!
ጅማ ዩኒቨርሲቲ የ2012 ዓ.ም አዲስ ገቢ ተማሪዎችን የሚቀበለው ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በተላከለት ትዕዛዝ መሰረት በትምህርት ሚኒስቴር ወደ ጅማ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ ተማሪዎችን ብቻ መሆኑን እና ዩኒቨርሲቲው በራሱ የሚመድበው ተማሪ እንደሌለ አውቃችሁ ራሳችሁን ከተሳሳተ መረጃ እና ከአታላዮች እንድትጠብቁ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡
ከሰላምታ ጋር
የጅማ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር ጽ/ቤት
Via #JimmaUniversity
@tsegabwolde @tikvahethiopia

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የገቢዎች ሚኒስቴር ለእኛ ለኛ 30 ሚሊዮን ብር የሚገመት የአልባሳት ድጋፍ ሰጠ!
የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን በጋራ በመሆን በትምህርት ሚኒስቴር ስር ለሚመራው ''የእኛ ለእኛ'' የኢትዮጵያውያን በጎ ፍቃደኞች መርሃ ግብር ግምታቸው 30 ሚሊዮን የሚሆኑ 100 ሺህ ኪሎ ግራም አልባሳትን በትላንትናው አለት በገቢዎች ሚኒስቴር ዋና መስሪያ ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ በተዘጋጀው የአዲስ አመት ስጦታ ዝግጅት ላይ ለተገኙት የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስቴር ዴኤታ ወ/ሮ ፅዮን ተክሉ ከገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እና ከጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ደበሌ ቃበታ በስጦታ ተበርክቶላቸዋል:: ሚኒስትር ዴኤታዋም በርክክቡ ወቅት እነዚህ ከፍተኛ ገንዘብ ሊያወጡ የሚችሉትን አልባሳት በተለያዮ የአገራችን ክፍሎች በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ አደጋ ምክንያት ትምህርታቸውን በአግባቡ ላልተከታተሉና ላቋረጡ ተማሪዎች እንደሚሰጥ ቃል ገብተዋል።

ባቱ⬆️
ዛሬ በባቱ ከተማ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ እና የክረምት በጎ አድራጎት ማጠቃለያ ፕሮግራም እየተካሄደ ይገኛል።

"ኢትዮጵያ ለጎረቤት ሃገራት የሚተርፍ መከላከያ ሠራዊት ገንብታለች" ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ
.
.
ኢትዮጵያ የውስጥ ሠላምን አስጠብቆ ለጎረቤት ሃገራት የሚተርፍ መከላከያ ሠራዊት ገንብታለች ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ ገለጹ፡፡
የሀገር መከላከያ ሠራዊት የምስራቅ እዝ በሀረር ከተማ አዲሱን ዓመት ከተለያየ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር አክብሯል፡፡ በመድረኩም ትናንት ከሰዓት የቀድሞና የአሁን ከፍተኛ የሰራዊቱ አዛዦች በተገኙበት የቀጠናው ሁኔታና የአገሪቷ የመከላከያ ሠራዊት ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ያተኮረ ውይይት ተደርጓል፡፡
የውይይት መነሻ ሃሳብ ያቀረቡት ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦሩ እንደተናገሩት ኢትዮጵያ ሰፊና አስቸጋሪ የቀጠናው ሁኔታ ውስጥ ያለች ሀገር መሆኗን ጠቁመዋል፡፡ በዚህ ቀጠና ውስጥ የሽብር እንቅስቃሴዎች የሀገራት የውስጥ ግጭቶች በሰፊው የሚስተዋሉበት መሆኑንም እንዲሁ ተናግረዋል፡፡
Via #ENA

"ማንም ረግጦ የወጣ አባት የለም!"
የኦሮሚያ ቤተ ክህነት ፅ/ቤትን ለማቋቋም እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ከነበሩ አካላት ጋር በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ውይይት ይካሄድ በነበረበት ወቅት ማንም ረግጦ የወጣ አባት እንዳልነበረ የስብከተ ወንጌልና የሃዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያ ኃላፊ አስታውቀዋል። ረግጠው ወጥተዋል ከተባሉት የቅዱስ ሲኖዶስ አባል አንዱ የሆኑት ብፁህ አቡነ ዲዎስቆሮስም ለVOA በሰጡት ቃል የተባለው እውነት አይደለም በሲኖዶስ ስብሰባ ተረግጦ አይወጣም ብለዋል።
ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መካንን👇
"...ስምምነት ላይ ደርሰን ነበር፤ ነገር ግን የወጣው መግለጫ እኛ ያልጠበቅነውና ከተነጋገርነው ውጪ ነው። አሁንም በዚህ ጉዳይ ላይ ከአባቶች ጋር #እየተነጋገርን ስለሆነ ምንም ልል አልችልም።"
NB. ከላይ ያለው ፅሁፍ ከቀናት በፊት በፌስቡክ እና በቴሌግራም ሲሰራጭ የነበረ ነው!

#update ‹‹የዓቃቤ ህግ መተዳደሪያ ደንብ በሚኒስትሮች ምክር ቤት የፀደቀ በመሆኑ ዓቃቤያን ህግ የየትኛውም የፖለቲካ ፓርቲ አባል መሆን አይችሉም›› ሲሉ የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ ገለፁ። በአሁኑ ወቅት ምንም አይነት የጨለማ እስር ቤቶች አለመኖራቸውንም አስታውቀዋል። ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ ‹‹እኔ ለህግ ተገዢ ነኝ›› በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ የሚከበረውን የፍትህ ቀንን አስመልክተው ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደተናሩት፤ ከዚህ በፊት ዓቃቤ ህግ የየትኛውም የፖለቲካ ፓርቲ አባል መሆን ይችል ነበር። ነገር ግን አሁን በሚኒስትሮች ምክር ቤት በፀደቀው አዲስ የዓቃቤ ህግ መተዳደሪያ ደንብ መሰረት ዓቃቤያን ህግ የየትኛውም የፖለቲካ ፓርቲ አባል መሆን አይችሉም። ‹‹ፖሊስና ፍርድ ቤቶች ድሮውንም ቢሆን በፓርቲ አባልነት ውስጥ መግባት ስለማይችሉ ጉዳዩ አይመለከታቸውም›› ያሉት አቶ ብርሃኑ፣ ዓቃቤያን ህጉ ግን ምንም እንኳ ቀደም ሲል በየትኛውም ፓርቲ አባል የመሆን እድሉ ነበራቸው ብለዋል።
Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
🤔ለሽያጭ ገበያ ወጥቶ 1 ነጥብ 75 ግራም የጆሮ ጌጥ ወርቅ የዋጠው ዶሮ!
ለሽያጭ ገበያ የወጣው ዶሮ 1 ነጥብ 75 ግራም የሚመዝን የጆሮ ጌጥ ወርቅ ይውጣል። ነገሩ የተከሰተው ጳጉሜ 03 ቀን 2011 ዓ.ም በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ወሊሶ ከተማ ነው፡፡ ባለቤትነቱ የአቶ ደነቀ ሸለመ የሆነው ዶሮ ለሽያጭ ገበያ ወጥቶ ገዢዎችን በመጠባበቅ ላይ እንዳለ የወይዘሮ ሃጫልቱ በድሩን 1 ነጥብ 75 ግራም የሚመዝን የጆሮ ጌጥ ላይ አነጣጥሮ ከጆሮዋ ላይ በጥሶ ይውጣል።
ነገሩ ከተከሰተ በኋላ የዶሮው ባለቤትና የወርቋ ባለቤት ሰጣ ገባ ውስጥ ይገባሉ፡፡ የወርቋ ባለቤት ወይዘሮ ሃጫልቱ ዶሮው ወዲያው ታርዶ ወርቃቸው እንዲሰጣቸው ቢሹም የዶሮው ባለቤት ደግሞ በጉዳዩ አልተስማሙም።
ነገሩ መክረሩን ያዩት ገቢያተኞች ጉዳዩ ወደ ፖሊስ ጣቢያ እንዲሄድ በማድረግ በአቅራቢያቸው ወደ ሚገኝ የወሊሶ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ያመራሉ፡፡ ጉዳዩ እንግዳ የሆነበት የወሊሶ ከተማ አስተዳዳር ፖሊስ ጣቢያም ጉዳያቸውን በመስማማት እንዲፈቱ ትዕዛዝ ይሰጣቸዋል።
የዶሮው ባላቤትም ወይዘሮ ሃጫልቱ ዶሮው የሚያወጣውን ዋጋ ከፍለው ዶሮውን ይረከቡኝ ሲሉ ይስማማሉ። አቶ ደነቅም የወርቁ ባለቤት 250 ብር እንዲሰጧቸው ቢጠይቁም ባለ ወርቋ የተጠየቀውን ብር የለኝም በማለታቸው 150 ብር ሰጥተዋቸው ጉዳዩ በሰላማዊ መንገድ መፈታቱን ነው የወሊሶ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የኮሙዩኒኬሽን ዲቪዥን ሃላፊ ኮማንደር ከበደ በዳዳ የተናገሩት።

❤1👍1
አሳዛኝ ዜና!
በምስራቅ ጎጃም ዞን ጎዛመን ወረዳ በደረሰ የተሽከርካሪ አደጋ የአንዲት ወጣት ህይወት ሲያልፍ በ15 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን ፖሊስ አስታወቀ። አደጋው የደረሰው ከአዲስ አበባ ጎንደር ሰዎችን አሳፍሮ ይጓዝ የነበረ ሚኒባስ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ድልድይ ጥሶ 14 ሜትር ጥልቀት ያለው ወንዝ ውስጥ ትናንት ሌሊት አስር ሰዓት አካባቢ በመግባቱ ነው፡፡
የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኢንስፔክተር ጎበዜ ይርሳው እንደገለጹት በጎዛመን ወረዳ ወይንማ ግራሞ ቀበሌ ተሽከርካሪው ድልድይ ጥሶ 14 ሜትር ጥልቀት ወርዶ “ቁልች” በተባለው ወንዝ ውስጥ በመግባቱ አደጋው ሊደርስ ችሏል። አደጋውን ያደረሰውም የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3-62442 ኦሮ ሚኒባስ ከአዲስ አበባ ተነስቶ በጨለማ በህገ ወጥ መንገድ ጎንደር ሲጓዝ በነበረበት ወቅት ነው።
በዚህም የአንዲት ወጣት ሴት ህይወቷ ወዲያው ማለፉን የተናገሩት ኢንስፔክተሩ 11 ሰዎች በከባድና አራት ደግሞ ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል። የሟቿ አስክሬን ለቤተሰብ ለማስረክብ ፖሊስ በመጠባበቅ ላይ እንደሆነ ኢንስፔክተር ጎበዜ ጠቅሰው፤ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በደብረ ማርቆስ ሪፈራል ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ አስታውቀዋል። የአደጋው መንስኤ በመጣራት ላይ ነው።
አሽከርካሪው አደጋውን ከደረሰ በኋላ ቢሰወረም ፖሊስ ለመያዝ በክትትል እንደሚገኝ አመልክተው የአካባቢው ማህበረሰብ ተጎጂዎቹን ለመታደግ ላደረገው ርብርብ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

5 ኢትዮጵያዊያን ላይ የቅጣት ውሳኔ ተላለፈ!
ከኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ 285 ኪሎ ሜትር ርቀት በስተሰሜን የምትገኘው የአይሲኦሎ ግዛት ፍርድ ቤት ያለ ፈቃድ በኬንያ ግዛት ውስጥ ሲንቀሳቀሱ አግኝቻቸዋለሁ ያላቸውን አምስት ኢትዮጵያዊያን ላይ የእስር ቅጣት አስተላልፏል። ጥፋተኛ ናቸው የተባሉት ኢትዮጵያዊያን የተከሰሱበትን ጉዳይ ያመኑ ሲሆን ከቤተሰብ ጋር ለመኖር ወደ ኬንያ እንደገቡ እና ያለ ፈቃድ መግባት ይህን ያህል ከባድ አገራዊ ጉዳይ መሆኑን እንደማያውቁ ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል።
ኢትዮጵያ እና ኬንያ በሚዋሰኑበት የማርሳቤት ግዛት ተነስተው ወደ ዋና ከተማዋ ናይሮቢ በመኪና ሲጓዙ አይሲኦሎ ግዛት ውስጥ በቁጥጥር ስር የዋሉት ኢትዮጵያዊያን በፍርድ ቤቱ ውሳኔ መሰረት ኹለት ወራትን በእስር ቤት የሚቆዩ ሲሆን የእስር ጊዜያቸውን ሲያጠናቅቁም ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ ተወስኗል።
ነፃ የሰዎችን ዝውውር በሚመለከት የኬንያው ፕሬዘዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ከወራት በፊት ‹‹ማንኛውም ምስራቅ አፍሪካዊ ኬንያዊ ነው ፤ በሚኖርበት አገር መታወቂያ ፓስፖርት ሳያስፈልገው ወደ ኬንያ መግባትና መውጣት ይችላል›› ሲሉ በይፋ መናገራቸው የሚታወስ ነው።
Via AddisMaleda

በሃዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ በሃያ ሁለት ኩባንዎች የተያዙ ሃምሳ ሁለት የማምረቻ ሼዶች በቀጣዩ ዓመት አጋማሽ ላይ ሙሉ በሙሉ ወደስራ እንደሚገቡ ተጠቆመ። ፓርኩ የፈጠረውን 27 ሺ የስራ እድልም ወደ 60 ሺ እንደሚያሳድገው ይጠበቃል።
Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
👍1
ፎቶ⬆️አንኮበር ወረዳ በረዶ የቀላቀለ ከባድ ዝናብ ዘንቦ ነበር። አካባቢውን ከላይ ባሉት በፎቶዎች ተመልከቱ።
ፎቶ📸Haile/TIKVAH-ETH/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ📸Haile/TIKVAH-ETH/
@tsegabwolde @tikvahethiopia