TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.2K photos
1.62K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አሳዛኝ ዜና!

በምዕራብ ሸዋ ዞን የጊቤ ወንዝን #በመሻገር ላይ የነበሩ አምስት ሰዎች በውሃው ተወስደው ህይወታቸው ማለፉን የዞኑ ኮሙዩኔኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አስታወቀ። አደጋው የደረሰው ሰሞኑን  እየጣለ ያለው ከባድ ዝናብ ተከትሎ ወንዙ ሞልቶ በመፍሰሱ ነው፡፡ የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ #ጉታ_ባልቻ እንደገለጹት ህይወታቸው ያለፈው ባለፈው ቅዳሜ ዳኖ ወረዳ ውስጥ ሰዮ ከተማ ገበያ ውለው ወደ ቤታቸው በመመለስ ላይ ከነበሩ 12 ሰዎች መካከል ነው። በወንዙ ላይ የጓዙበት የነበረው ባህላዊ ጀልባ በመገልበጡ አምስት ሰዎች በውሃው ተወስደው  ህይወታቸው ሊልፍ ችሏል፡፡ “ከሟቾቹ መካከል የሶስት ሰዎች አስክሬን ተገኝቷል፤ የቀሪዎቹ እስከዛሬም አልተገኘም” ብለዋል፡፡ አስክሬናቸው የተገኘው ቤተሰቦቻቸው እንዲረከቡ መደረጉን አመልክተዋል። የጊቤ ወንዝ ወደ ጅማና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን የሚያልፍና ወንዙ ድልድይ ስለሌለው የአካባቢውን ህብረተሰብ እየጎዳ መሆኑን አቶ ጉታ ጠቁመዋል፡፡

Via ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia