TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.62K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ኢትዮጵያ #ጌዴኦ

በሳውዲ አረቢያ ፤ ሪያድ 45ኛው የዩኔስኮ የዓለም ቅርስ ኮሚቴ ስብሰባ እየተካሄደ የሚገኝ ሲሆን በዚህም ስብሰባው ፤ በኢትዮጵያ የቀረበው የጌድኦ ባህላዊ መልክአ-ምድር ፋይል በኮንቬሽኑ መሰረት መርምሮ #በዓለም_ቅርስነት  እንዲመዘገብ በሙሉ ድምጽ ማፅደቁን የቱሪዝም ሚኒስቴር አሳውቋል።

ይህም በኢትዮጵያ የተመዘገቡት የባህልና ተፈጥሮ ቅርሶች ወደ 10 እንዲያድጉ አድርጓል ፤ ለአፍሪካ ደግሞ 100ኛ ሆኖ ተመዝግቧል።

የጌድኦ ባህላዊ መልክአ-ምድር ፋይል ምዝገባ ከኮንሶ ከተመዘገበ ከ12 አመት ( እ.ኤ.አ ከ2011) በኃላ በዓለም ቅርስነት የተመዘበ ነው።

#ቱሪዝም_ሚኒስቴር

@tikvahethiopia
👍1.74K248🙏63👎53🕊30😢25🥰14😱14😡1
ሐይቻ ጅብቾ ቦራሚ !

የጌዴኦ ብሔር ታሪክ ውስጥ በቀዳሚነት ከምጠቀሱ ታሪካዊ አባቶች አንዱ የወንጌል አርበኛ ሐይቻ ጅብቾ ቦራሚ በ112 ዓመታቸው ማረፋቸውንና ስርዓተ ቀብራቸውም መፈጸሙን የጌዴኦ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ የባህል ጉዳዮች መረጃ ዘርፍ አስተባባሪ አቶ ዳንኤል ከተማ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

አቶ ዳንኤል " ሐይቻ ጅብቾ ቦራሚ ለብሔጉ ነጻነት እና እኩልነት የታገሉ ጀግና ነበሩ " ብለዋል።

" በህይወት ዘመናቸውም ለብሔርና ብሔረሰቦች አንድነት ሰላምና መቻቻል አበክሮ የተጉ ፣ አንድነትን ያሰፈኑ፣ ሰለምን ያረጋገጡ የህዝብ አባት ነበሩ " ሲሉ ገልጸዋል።

በ1905 የተወለዱት ሐይቻ ጅብቾ ቦራሚ የወጣትነት ጊዜያቸውን በነጻነት ትግልና በተለይም የጭሰኛና ባላባት ስርዓትን በመቃወም ያሳለፉ መሆኑን አካባቢውንም በአውራጃነት ማስተዳደራቸውን ገልጸዋል።

" ሀይቻ ጅብቾ ታሪክ ከማይዘነጋዉና ከትዉልድ ወደ ትዉልድ እየተላለፈ ከሚነገርላቸዉ አኩሪ ስራቸዉ ዉስጥ በወቅቱ ብሔሩ በተሳሳተ መንገድ ይጠራ የነበረበትን ' ዴራሳ ' የሚል የወል ስያሜ በመቃወም በ1938
#ጌዴኦ ተብሎ እንዲጠራ አስደርገዋል " ሲሉም አክለዋል።

ሐይቻ ጅብቾ ለህዝብ ፣ ለመንግሥት ብቻ ሳይሆን ለወንጌል አገልግሎት ትልቅ መስዋእትነትን የከፈሉ አባት እንደነበሩ ተገልጿል።

‎ውልደታቸው በጌዴኦ ዞን ዲላ ዙሪያ የሆኑት ሐይቻና የወንጌል አርበኛ አቶ ጅብቾ ቦራሚ በተወለዱ በ112 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩ ሲሆን ‎የቀብር ስነስርዓታቸው መኖሪያቸውን አድርገው በነበሩበት በአባያ ወረዳ ቡናታ ቀበሌ በቡናታ ቃለህይወት መቃብር ተፈጽሟል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
😭327190🙏63🕊50🤔34👏12😢9😱3😡3🥰2