TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63K photos
1.61K videos
217 files
4.38K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ይህ የ18 ቢልዮን ዶላር ባለሀብቱ አል ዋሊድ ቢን ታላል ሪያድ ባለው ሪትዝ ካርልተን ሆቴል ውስጥ መሬት ላይ ባለ ቀጭን ፍራሽ ላይ ጋደም ብለው የሚያሳይ ፎቶ ነው። በትዊተር እና ሲቲ ባንክ ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ ያላቸው አል ዋሊድ ከቀናት በፊት በሳውዲ መንግስት መታሰራቸው ይታወሳል።

@tikvahethiopia
አረርቲ መረጋጋት ርቋታል ተባለ፡፡ ለሁለት ሳምንት የመብራት አገልግሎት በመቋረጡ ምክንያት አደባባይ የወጡ ነዋሪዎች እስካሁንም በጨለማ የተዋጡ ምሽቶችን እየገፉ እደሆነ ነው የተሰማው፡፡ መንግስትም ችግሩን ለመፍታት ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል።

ምንጭ፦ ዶቼ ቨለ

@tsegabwolde @tikavhethiopia
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አዋዳ ካምፓስ ተማሪዎች የወጪ መጋራት ክፍያ(Cost) በአግባቡ አልተከፈለንም አሉ።

የተላከልኝ መረጃ እንደሚጦቅመው በሌሎቹ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ካምፓሶች ማለትም በዋናው ካምፓስ፣በቴክኖ ካምፓስ፣በሪፈራል ካምፓስ(ጤና ግቢ)፣በአግሪ ካምፓስ እንዲሁም በወንዶገነቱ ካምፓስ የሚማሩ ተማሪዎች ከገቡበት ቀን አንስቶ ማለትም ከመስከረም 19 ጀምሮ እንስከ ጥቅምት ወር ያለው ክፍያ ሲከፈላቸው የአዋዳ ካምፓስ ተማሪዎች ግን ሌላው ተቀንሶ የተከፈላቸው የህዳር ወር ብቻ ነው።

ተማሪዎች ከሌሎቹ ጋር እኩል ገብተው በክፍያው ላይ ይህን መሰሉ መከፍፈል እንዴት እንደመጣ ግራ እንዳጋባቸው በመግለፅ የሚመለከተው አካል አፍጣኝ መፍትሄ እምዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

ምንጭ ፦ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የአዋዳ(የማህበራዊ ሳይንስ) ተማሪዎች

@tsegabwolde @tikvahethiopia
1
ክብር ለሚገባው ክብር እንስጥ !

አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ለጀግናው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በቤቱ የምሳ ግብዣ አደረገለት።

ኢትዮጵያዊነት ረቂቅ ነው !

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰናይ ተግባር ! የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች "ደማችንን ለወገናችን"

ኢትዮጵያ ቡና

#ነገን_እናፍቃለው ነገ ህዳር ሦስት በቢጫ እና በቡኒው አርማ ተውበው በድንቅ ዝማሬቸው ታጅበው ገና በማለዳ ስቴድዮም አጠገብ ቤሔራዊ ደም ባንክ አካባቢ የቡናን ደጋፊ በብዛት ካየህ
አይገረምህ ፤ልንገርህ አይደል ስለነዚህ ድንቅ ደጋፊዎች...ጅሮህ ከሰማው ከፉ ወሬ ይልቅ ዓይነህ ያየው መልካም ምግባር እና ሳባዊነት የነሱ ትክክለኛ መገለጫ ነው። ይህን እመን ምክንያቱም ኢትዮጵያ ቡናን ለሰባዊነት የሚቀድመው የለም፡፡ የነገን ማለዳ እናፍቃለው ፤ አዎ የዛሬን መሽቶ፣ መንገት በጉጉት እጠብቃለው ፤
በቃላቸው ከሚታመኑት እጅግ ከምወዳቸው እና ከምናፍቃቸው የቡና ደጋፊዎች ጋር ለሰባዊነት ተግባር ነገ (ህዳር 3) ቀጠሮ አለብኝ እና፡፡

"ደማችንን ለወገናችን"

ምንጭ ☞ ከቡና ሰማይ ስር

@BUNA_GEBEYA

12 የሆነው በምክንያት ነው

@tsegabwolde @tikvahethiopia
1😢1
ዛሬ በመቱ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እርስ በእርሳቸው ተጋጩ። ፓሊስም ወደግቢው በመግባት አስለቃሽ ጭስ በመጠቀም ሁኔታውን ለማረጋጋት ችሏል።

የግጭቱ ምክንያት ዛሬ በግቢው በተደረገ ስብሰባ ላይ ተማሪዎች የሰነዘሩት ቃል አለመግባባትን እና ቁጣን በመፍጠሩ ነው።

ስብሰባው በግቢው እየተስተጓጎለ የሚገኘውን የትምህርት ስርዓትን በሚመለከት ከተማሪዎች ጋር ወይይት ለማድረግ የታቀደ ነበር።

በተፈጠረው ግጭት የተጎዱ ተማሪዎች እንዳሉ እና ብሄርን መሰረት ተደርጎም አንዳንድ ግለሰቦች በሰዎች ላይ ድብደባ መፈፀማቸውን ከአይን እማኞች ባገኘሁት መረጃ ለመረዳት ችያለሁ።

በዩኒቨርሲቲው አቅራቢያም የትራስፖርት አገልግሎት ተስተጓጉሎ አምሽቷል።

በሁኔታው የተደናገጡ ተማሪዎች አዳራቸውን በእምነት ተቋማት እና በተለያዩ ቦታዎች ለማድረግ መገደዳቸውንም ገልፀዋል። በግቢው የሚገኙ ተማሪዎችም ሁኔታው እጅግ እንደሚያሰጋቸው ተናግረዋል። የሚመለከተው አካል ይህን ችግር እንዲፈታላቸውም ተማፅነዋል።

በተጨማሪ ፦

በዩኒቨርሲቲው የሚማሩ የጋምቤላ ክልል ተማሪዎች ግቢው እንዲለቃቸው መጠየቃቸው ተሰምቷል። ነገር ግን ጥያቄያቸው ወድቅ መደረጉን እና የዩኒቨርሲቲው አስተዳደሮችም ሁኔታዎች ወደ ቀደመው መልኩ እንደሚመለሱ አስረድተዋቸዋል ተብሏል።

በአሁን ሰዓት ግቢው ሰላማዊ ነው።

ምንጭ ፦ የመቱ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢትዮጵያ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ የምታደርገውን ጥረት በተለያዩ ዘርፎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ ለግንባታ የሚውሉ የኬሚካል ውጤቶችን የሚያመርት ፋብሪካ በአለም ገና ተመርቋል፡፡

ምንጭ ፦ ኢብኮ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አርባምንጭ ከተማ ለምተገኙ የሁሉም ካምፓስ ተማሪዎች እና መምህራን፡፡ የተወሰኑ ህገወጥ ግለሰቦች በከተማው ለዘረፋ ተሰማርተው የከተማዋን ስምና መልካም ገፅታ እያበላሹ ነው። በተለይ በኩልፎ ካመፓስ ከመምህራን ኮሌጅ አንሰቶ እስከ ካምፓስ በር፣ በሜን ካምፓስ ከገበያው እሰከ ዋናው በር እና በጫሞ ካምፓስ ደግሞ ወሰጥ ለውስጥ ባሉ መንገዶች ተማሪዎች እየተዘረፉ ነው። እንዲሁም የባጃጅ ትራንስፖርት የሚሰጡ መስለው በወሰጡ ዘራፊዎችን በመያዝ በጉዞ ላይ እነዳሉ መንገድ በመቀየር ወንጀል ይፈጽማሉ።ተማሪዎች እራሳችሁንም ንብረታችሁንም ጠብቁ።

ይህን መልዕክት ያደረሰው የአርባምንጭ ከተማ ነዋሪ ነው።

@tikvahethiopia @tsegabwolde
ደሜን ለወገኔ ያሉት የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች ዛሬ ደም በመለገስ ላይ ይገኛሉ።ከለጋሾች ብዛት የተነሳም የብሄራዊ ደም ባንክ ሰውን ማስተናገድ ከአቅሙ በላይ ሆኖበታል። በርካታ የቡና ደጋፊዎች በሰልፍ ብዛት እየተመለሱ ነው። በቦታው ተጨማሪ የሰዉ ሀይል እንደሚያስፈልግ ደጋፊዎች ገልፀዋል።

@BUNA_GEBEYA
ሌላኛው የደጋፊዎች የደም ልገሳ በሀላባ ከተማ። ዛሬ የሸገር ስፖርት ደጋፊዎች ደም ሲለግሱ ውለዋል።
የሸገር ስፖርት ክለብ የ2009 የማጠቃለያ የምክክር መድረክ አዘጋጀ ።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ዛሬ እሁድ ህዳር 3/2010 በሀላባ ከተማ ቴክኒክና ሙያ ተቋም አዳራሽ ውስጥ በተለያዩ ፕሮግራሞችና ከኢትዮጵያ ቡና በመቀጠል "# የደም_ልገሳ ያደረገ ብቸኛው ስፖርት ክለብ መሆኑን በማስመስከር በደማቅ ሁኔታ አክብሯል።

በፕሮግራሙ ላይ የክለቡ ሰብሳቢ አቶ መሀመድ አብድረህማን የ2009 የክለቡን የስራ አፈፃፀም ሪፖርት አቅርበዋል።

በቀረበው ሪፖርት ላይ የክለቡ ደጋፊዎችና ታዳሚዎች ሰፋ ያለ ውይይት አድርገዋል በውይይቱ ለሸገር ስፖርት ብቻ ሳይሆን ለታላቁ ክለባችን ሀላባ ከነማ
ግብዓት ሊሆኑ የሚችሉ ሀሳቦች ተነስተዋል።

ፕሮግራሙን ሰሞኑን ከሱዳኑ ኮንሰርት ለዚህ ፕሮግራም ስትል ስትበር በመጣችው ድምፃዊት ዙልፋ ከማል ደመቅመቅ ብሎ ቀጥሏል።

በ2009 የክረምት ውድድር ላይ ከሸገር ስፖርት የኮከቡ ተጫዋችና ጎል አግቢ ፀጋው ደርቤ መለያ ለጫረታ ቀርቦ አብዲ ሳዳት በ3000 ብር አሸንፎ ወስዶታል።

ኬኩን በ6500ብር ባህረዲን ሸሱሌ ሲያሸንፍ በአሸናፊ ዮሀንስ የተዘጋጀው የሸገሩን አርማ አብዲሻ ሁሴን በ5000ብር አሸንፎ ወስዷል።

ፕሮግራሙ ይህ ፅሁፍ አስከተለቀቀበት ሰዓት ድረስ ቀጥሏል።

ምንጭ ፦ ማሞ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የዝዋይ ከተማ ነዋሪዎች አደባባይ ወጡ። ነዋሪዎቹ በመንግስት ላይ ያላቸውን ቅሬታ አሰምተዋል። ከአንድ የህዝብ ማመላለሻ መኪና ውስጥ ተቀርፆ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የተላከውን ቪድዮ ይመልከቱ።

ምንጭ ፦ ፍ....

@tikvahethiopia
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ እስኪጠናቀቅ ድረስ የሚያደርገውን ድጋፍ እንደሚቀጥል የሃዋሳ ዩኒቨርስቲ አስታወቀ፡፡

የዩኒቨርስቲው ማህበረሰብም ለህዳሴው ግድብ ዋንጫ አቀባበል ባደረጉበት ወቅት የ3ዐ ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርገዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ከቦንድ ግዥ በተጨማሪ በምርምር ስራ አስፈላጊውን ሙያዊ ድጋፍ ለማድረግ መዘጋጀቱንም ገልጿል።

ምንጭ ፦ ኢብኮ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዛሬ ዝዋይ በነበረው ሁኔታ ወጣቶች መንገድ በመዝጋት "ሰላም ባስን" አናሳልፋም በማለት መልሰዋል። ሌሎች ተሽከርካሪዎችን ደግሞ ተሳፋሪዎች በእጃቸው የ"X" ምልክት እያደረጉ እዲያልፉ ማድረጋቸውን ከአይን እማኝ የተገኘው መረጃ ይጠቁማል።

ምንጭ ፦ ፍ....

@tikvahethiopia
ቢጂአይ ኢትዮጵያ ራያ ቢራን በ2.5 ቢልዮን ብር ለመጠቅለል ጥያቄ እንዳቀረበ ተነገረ። ቢጂአይ የራያ ቢራ 42 ፐርሰንት ባለቤት ሲሆን የተጠቀሰውን የገንዘብ መጠን ያቀረበው በትግራይ ክልል የሚገኘውን ፋብሪካ ሙሉ ለሙሉ ለመጠቅለል ነው ሲል ሪፖርተር ዘግቧል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አስቸኳይ ማስታወቂያ ለሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች።

@tikvahethiopia
የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ባወጣው አስቸኳይ ማስታወቂያ ከነገ ሰኞ ህዳር 4/2010 ዓ.ም ቀን ጀምሮ የተቋረጠው ትምህርት እንዲቀጥል እና ተማሪዎችም ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ በጥብቅ አሳውቋል።

በተማሪዎች የተጠየቁ ጥያቄዎች በመንግስት ምላሽ የተሰጣቸው በመሆኑና አሁም እየተጠየቁ ያሉ ጥያቄዎች በሂደት መልስ እንደሚያገኙ በመግለፅ ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ አሳስቧል።

ማንኛውም ተማሪ ከነገ ጀምሮ በትምህርት ገበታው ላይ ባይገኝ በዩኒቨርሲቲው ህግ እና ደንብ መሰረት ተጠያቂ እንደሚሆን ተገልጿል። በተጨማሪም ሌሎች ተማሪዎች ትምህርታቸውን እንዳይከታተሉ ተፅእኖ ማድረግ ተቀባይነት የሌለው ድርጊት በመሆኑ በዚህ ድርጊት ተሳታፊ የሚሆን ተማሪ ተጠያቂ እንደሚሆንም ዩኒቨርሲቲው አስታውቋል።

ዩኒቨርሲቲው እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው የዩኒቨርሲቲው መማክርት ጉባኤ በዩኒቨርሲቲው ያለውን አሳሳቢ ሁኔታ በመገንዘብ ህዳር 1 ቀን ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ ነው።

@tikvahethiopia @tsegabwolde
አላሙዲን ከሳዉዲ እስር ቤት ተፈቱ እየተባለ ነው። በአዲሱ የሳኡዲ አልጋወራሽ ልኡል በተቀጣጣለው የሳኡዲ ንጉሳዊ ቤተሰብ ስልጣን ሽኩቻ ቀውስ ሰለባ በመሆን ላለፉት ቀናት ሪያድ በሚገኘው ባለ 5 ኮከቡ ሪትዝ ካርልተን ሆቴል እንዲቆዩ የተደረጉት ሼክ መሐመድ አሊ አል-አሙዲ ዛሬ ቆይታቸውን ያጠናቀቁ ሲሆን ነገ ወደ ኢትዮጵያ ይመለሳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ይህን መረጃ ያወጡት ለቢልየነሩ ቅርብ የሆኑ ሰዎች ናቸው።

@tsegabwolde @tilvahethiopia
ከወጣት እስከ አዛውንት የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊ ደሙን ለወገኑ ሲለግስ ውሏል። ደጋፊዎቹ ለህፃናት መልካምነትን እንዲማሩ ለወገን ደራሽ ወገን መሆኑን እንዲያውቁትም አድርገዋል።