መኀደረ ጤና
2.6K subscribers
36 photos
13 videos
6 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩╩═╝
ስለ ጤናዎ ወሳኝ መረጃዎች💊 ሁሉም ሰው ሊያውቃቸው የሚገባ የጤና መረጃዎችን ከፈለጉ ይህን ቻናል ይቀላቀሉ ይማሩበታል ያስተምሩበታል መልካም ጤና ለሁላችን..


መልካም ጤና ለሁላችን..
Download Telegram
#የማህፀን #አንገት #ካንሰር

የማህፀን አንገት ካንሰር ከማህፀን አንገት ሴሎች የሚነሳ
የካንሰር አይነት ነዉ፡፡ ለብዙዎቹ የማህፀን አንገት ካንሰር
መከሰት ከፍተኛዉን ሚና የሚጫወተው ሂዩማን ፓፒሎማ
ቫይረስ/ human papillomavirus /የሚባለዉና
በግብረስጋ ግንኙነት አማካይነት የሚተላለፈዉ የቫይረስ
አይነት ነዉ፡፡
የህመሙ ምልክቶች
ህመሙ በሚጀምርበት የመጀመሪያ ጊዜያቶች ምንም
አይነት የሚታይ የህመም ምልክት ላይኖር ይችላል፡፡
ህመሙ እየቀጠለ ሲመጣ ግን የሚከተሉት የህመም
ምልክቶች ሊታዩ ይችላሉ፡፡
የግብረስጋ ግንኙነት ካደረጉ በኃላ፣ በወር አበባ ዑደት
መካከል ወይም ካረጡ በኃላ ከብልት ደም መታየት
ዉሃማ፣ ደምነትና ሽታ ያለዉ ፈሳሽ መጠነኛ ወይም ከፍተኛ
በሆነ መጠን ከብልት መፍሰስ
የዳሌ ዉስጥ ህመም፣ በግብረስጋ ግንኙነት ወቅት ህመም
መኖር የመሳሰሉት ናቸዉ፡፡
የህመሙ መንስኤ
የማህፀን አንገት ካንሰር የሚከሰተዉ የማህፀን አንገት
ሴሎች ጤነኛ ወዳልሆኑ ሌሎች ሴሎች በሚለወጡበት
ወቅት( genetic change (mutation)) የሚመጣ
ነዉ፡፡
የማህፀን አንገት ካንሰር መንስኤዎች በትክክል ምን
እንደሆኑ ባይታወቅም ሂዩማን ፓፒሎማ ቫይረስ ትልቁን
ሚና እንደሚጫወት ይታመናል፡፡ሂዩማን ፓፒሎማ ቫይረስ
ብዙ ሴቶች ላይ የሚከሰት ቢሆንም በዚህ ቫይረስ የተያዙ
ሁሉም ሴቶች የማህፀን አንገት ካንሰር ይያዛሉ ማለት ግን
አይደለም፡፡ ስለሆነም ሌሎች እንደ አካባቢያዊና የአኗኗር
ዘይቤ ለችግሩ መፈጠር ሚና ሊኖራቸዉ ይችላሉ፡፡
ለህመሙ የሚያጋልጡ ነገሮች
ከአንድ በላይ የወንድ ጓደኛ ያላቸዉ ሴቶች፡- ከብዙ
ወንዶች ጋር የግብረስጋ ግንኙነት የሚያደርጉ ሴቶች ወይም
ከብዙ ሴቶች ጋር ግንኑነት ካለዉ ወንድ ጋር ጥንቃቄ
የጎደለዉ የግብረ ስጋ ግንኙነት የሚያደርጉ ሴቶች በሂዩማን
ፓፒሎማ ቫይረስ የመያዝ እድላቸዉ ከፍተኛ ነዉ፡፡
በለጋነት እድሜ የግብረስጋ ግንኙነት መጀመር፡-
እድሜያቸዉ ከ18 አሜታት በታች እያሉ የግብረ ስጋ
ግንኑነት የሚጀምሩ በቫይረሱ የመጠቃት እድሉ
ይጨምራል፡፡
በሌሎች የአባለዘር ህመሞች መያዝ፡- እንደ ጨብጥ፣
ከርክርና ሌሎች አባለዘር ህመሞች መያዝ በሂዩማን
ፓፒሎማ ቫይረስ የመያዝ እድሉን ይጨምራል፡፡
የበሽታ መከላከል አቅም ደካማ/ የቀነሰ ከሆነ፡- የሂዩማን
ፓፒሎማ ቫይረስ ኢንፌክሽን ካለና የበሽታ መከላከል
አቅም የደከማ አሆነ በማህፀን አንገት ካንሰር የመያዝ
እድሉ ከፍ ያለ ነዉ፡፡
ሲጋራ ማጨስ፡- ሲጋራ ማጨስ ለማህፀን አንገት ካንሰር
ያጋልጣል፡፡
ሊደረጉ የሚችሉ ህክምናዎች
ለማህፀን አንገት ካንሰር የሚደረጉ ህክምናዎች እንደ
ካንሰሩ የህመም ደረጃ፣እንዳለዎት ሎሎች የህመም
አይነቶችና የህክምና ምርጫዎ ሊለያይ ይችላል፡፡ስለሆነም
ሊሰጡ ከሚችሉ የህክምና ዘዴዎች ዉስጥ ቀዶ
ጥገና፣የጨረር ህክምና፣ኬሞቴራፒና ከሶስቱ ዉስጥ
አንዱን ከአንዱ ጋር በማዳበል ሊሆን ይችላል፡፡