#ቋቁቻ
ቋቁቻ በብዛት ሊከሰት የሚችል ከሰዉ ወደ ሰዉ የማይተላለፍ በፈንገስ ምክንት የሚመጣ የቆዳ ላይ ችግር ነው። ፈንገሱ የቆዳ ተፈጥሮዊ መልክን በማሳጣት ትናንሽ፣ ነጣ ወይም ጠቆር ያሉ መልካቸዉን የለወጡ ነገሮች በቆዳ ላይ እንዲወጡ ያደርጋል፡፡ ቐቁቻ በብዛት የሚከሰትዉ #በአንገት፣#ትከሻ #ደረትና #ጀርባ ላይ ነዉ።
👉የህመሙ ምልክቶች
#በጀረባ ፣ #ደረት ፣ #አንገት #እጅ #ላይ ከክርን በላይ ከፍ ብሎ ባለዉ የቆዳ ከለር መለወጥ።
👉 መጠነኛ ማሳከክ
😁የቆዳ መቀረፍ የመሳሰሉት ናቸው።
👉የህመሙ መንስኔዎች
ቐቁቻን ሊያመጡ የሚችሉ ፈንገሶች በጤናማ ቆዳ ላይ ሊገኙ ይችላሉ፡፡ ይህ ችግር በብዛት በለጋነትና በወጣትነት እድሜ ክልል ይከሰታል፡፡ ቐቁቻ ህመም የለዉም፤ ከሰዉ ወደ ሰዉ አይተላለፍም፡፡ ነገር ግን ሊያስጨንቅ ወይም የሀፍረት
ስሜት እንዲሰማን ሊያደርግ ይችላል፡፡ ይህ የሚሆነም ፈንገሱ ከመጠን በላይ ሲያድግ ነዉ፡፡
ቐቁቻ እንዲመጣ የሚያደርጉ/እንዲባባስ የሚያደርጉ ነገሮች፦
• ሞቃታማና እችጥበታማ የአየር ፀባይ
• ወዛማ ቆዳ ካለዎት
• የሆርሞን መለዋወጥ
• የበሽታ መከላከል መዳከም ናቸው።
የህክምና ባለሙያዎን መመከር የሚገባዎ መቼ ነው?
• ለቆዳዎ እያደረጉት ያለዉ ጥንቃቄ ለዉጥ ካላመጣ
• ህመሙ ከጠፋ በኃላ ተመልሶ ከመጣ
• ህመሙ ብዙ የቆዳ ክፍልን ከሸፈነ።
ሊደረጉ የሚችሉ ህክምናዎች
ቐቁቻ በፈንገስ ምክንት የሚመጣ የቆዳ ችግር ስለሆነ የሚከተሉት መድሃኒቶች ሊታዘዙ ይችላሉ፡፡ የተወሰኑት መድሃኒቶች በቆዳ ላይ ሊቀቡ የሚችሉ ሲሆን ቀሪዎቹ የሚዋጡ ናቸዉ፡፡
• የፍሉኮናዞል እንክብል ወይም ፈሳሽ መድሃኒት
• ኢትራኮናዞል (እንክብል ፣ ወይም ካፕሲዩል ፈሳሽ)
• ኬቶኮናዞል (ክሬም ጄል ፣ ወይም ሻንፖ) ናቸው።
ምንም እንኳ ህክምናዉን በደንብ ቢከታተሉትና ህመሙ ቢሻሎትም ለሳምንታት ወይም ለወራት የቆዳዎ ቀለምዎ ሳይለወጥና እንደሻከረ ሊቀጥል ይችላል።
እንዳንዴ ደግሞ ህመሙ ተመልሶ ሊመጣ ይችላል( በተለይ በሞቃታማና እርጥበታማ የአየር ፀባይ ወቅት)፡፡ ስለሆነም ኢንፌክሽኑ ተመልሶ እንዳይመጣ መድሃኒት በወር አንዴ ወይም ሁለቴ መዉሰድ ሊስፈልግ ይችላል።
መልካም ጤንነት!!