መኀደረ ጤና
2.6K subscribers
36 photos
13 videos
6 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩╩═╝
ስለ ጤናዎ ወሳኝ መረጃዎች💊 ሁሉም ሰው ሊያውቃቸው የሚገባ የጤና መረጃዎችን ከፈለጉ ይህን ቻናል ይቀላቀሉ ይማሩበታል ያስተምሩበታል መልካም ጤና ለሁላችን..


መልካም ጤና ለሁላችን..
Download Telegram
#ምች

ምች ትናንሽ ዉሃ የቋጠሩ በከንፈርና በከንፈር ዙሪያ የሚወጡ ቁስለቶች ናቸዉ። #ምች በመሳሳምና በሌሎች ከሰዎች ጋር ባለን የቀረበ ግንኙነት አማካኝንት ከአንድ ሰዉ ወደ ሌላዉ ሰዉ በቀላሉ የሚተላለፉ የህመም አይነቶች ናቸዉ።
👉ምች ሀርፐስ ሲምፕሌክስ
ታይፕ 1/ herpes simplex virus (HSV-1) በሚባል የቫይረስ አይነት የሚከሰት ነዉ፡፡ የምች ቫይረስን ሙሉ በሙሉ በህክምና ማዳን/ማጥፋት አይቻልም፡፡ ስለሆነም ጭንቀት ሲኖር ወይም የበሽታ
መከላከያ ዘዴዎች ሲቀንሱ ህመሙ በተደጋጋሚ ሊከሰት ይችላል፡፡ ለቫይረሱ የሚሰጡት መድሃኒቶች ህመሙ ቶሎ እንዲሻሻልና በተደጋጋሚ እንዳይከሰት ለማድረግ ይረዳል፡፡
👉 #የህመሙ #ምልክቶች
ብዙዎቹ በሀርፐስ ቫይረስ የተያዙ ሰዎች የህመም ምልክቶችን አያሳዩም፡፡ ነገር ግን ምንም ቁስለት ባይኖራቸዉም ቫይረሱን ወደ ሌላ ሰዉ ሊያስተላልፉ ግን
ይችላሉ፡፡ በቫይረሱ ከተያዙ በኃላ የህመሙ ምልክት የሚያሳዩ ሰዎች ላይ ህመሙ የተለያዩ ደረጃዎችን ያሳያል፡፡
👉የመጠቅጠቅና የማሳከክ ስሜት፡- ብዙ ሰዎች ዉሃ የቋጠሩ ቁስለቶች ከመዉጣታቸዉ በፊት ለአንድ ወይም ሁለት ቀናት በከናፍሮቻቸዉ ዙሪያ የማሳከክ፣ የማቃጠል ወይም የመጠቅጠቅ ስሜት ያሳያሉ፡፡
👉ዉሃ የቋጠሩ ቁስለቶች፡- ትናንሽ ዉሃ እየቋጠሩ የሚፈነዱ ቁስለቶች ይከሰታሉ፡፡ የማዠትና የመድረቅ ደረጃ፡- ዉሃ የቋጠሩ ቁስለቶች አንዱ ከሌለኛዉ ጋር እየተወሃዱና እየፈነዱ ተለቅ ያለ ክፍተት ያለዉ ቁስል ይፈጥራሉ፡፡ ቁስሉ ፈሳሽ
ነገር እየያዘና እየደረቀ ይመጣል፡፡
የተለያዩ የህመም ምልክቶች የሚከሰቱ ሲሆን በተለይ ህመሙ ለመጀመሪያ ጊዜ ከሆነ የተከሰተዉ የሚከተሉት ምልክቶች ይታያል፦
💦ትኩሳት
💦የጉሮሮ መከርከር/ህመም
💦የራስ ምታት
💦የጡንቻ ላይ ህመም
💦ትናንሽ ያባበጡ እጢዎች መከሰት ናቸዉ፡፡
የሀርፐስ ቫይረስ የመመገቢያ ዕቃዎችን አብሮ በመጠቀም፣ በምላጭ፣ በፎጣ እንዲሁም በመሳሳም ከአንዱ ወደ ሌላ ሰዉ ይተላለፋል፡፡ ምንም እንኳ ህመሙ ፈሳሽ ባለዉ/ በሚያዥበት ወቅት በጣም ተላላፊ ቢሆንም ዉሃ የቋጠሩ
ቁስለቶችም በሌሉበት ወቅትም ሊተላለፍ ይችላል፡፡
አንድ ሰዉ በምች አንዴ ተይዞ ከዳነ በኃላ ቫይረሱ በቆዳዉ ዉስጥ ባሉ የነርቭ ሴሎች ዉስጥ ተደብቆ ስለሚቆይ ሌላ ጊዜ እንደአዲስ በበፊቱ ቦታ ወይም በአቅራቢያዉ በመዉጣት እንደገና ህመም እንዲመጣ ያደርጋል።
ምች እንደገና/በተደጋጋሚ እንዲመጣ/እንዲባባስ ከሚያደርጉ ነገሮች ዉስጥ፡-
💦ትኩሳት
💦 የወር አበባ ዑደት
💦 ጭንቀት
💦ድካም
💦ለፀሃይ ብርሃን መጋለጥ
👉ለምች ተጋላጭነትዎን የሚጨምሩ ነገሮች
90 በመቶ የሚሆኑ የአለማችን አዋቂ ሰዎች ምንም እንኳ ከዚህ በፊት ከምች ጋር ተያያዥነት ያላቸዉ ህመም ታመዉ ባያዉቁም ምችን የሚያመጣዉ ቫይረስ በሰዉነታቸዉ ዉስጥ እንዳላ ጥናቶች ያረጋግጣሉ፡፡
የበሽታ መከላከያ ዘዴዎቻቸዉ
የተዳከመ ሰዎች ከሌሎቹ ይልቅ በቫይረሱ ምክንያት ጉዳት ሊደርስ ይችላል፡፡
በሃርፐስ ቫይረስ ምክንት የሚመጣዉን ህመም እንዲወሳሰብ የሚያደርጉ ነገሮች
💦ኤች አይቪ ኤድስ
💦ኤክዜማ
💦ቃጠሎ
💦የካንሰር ህክምና
#ለምች #ሊደረግ #የሚችል #ህክምና
👉ምች/ የአፍ ዙሪያ ቁስለት ያለምንም ህክምና በራሱ ጊዜ ከሁለት እስከ አራት ሳምንታት በራሱ ጊዜ የሚጠፋ ሲሆን የመዳኑን ሂደት ለማፋጠን አንደ አሳይክሎቪር፣ ቫልሳይክሎቪርና ፋምክሎቪር ያሉ መድሃኒቶች ሊታዘዝልዎ
ይችላል፡፡
#የህክምና #ባለሙያ #ማማከር #የሚገባዎ #መቼ #ነዉ?
በአጠቃላይ ሲታይ ምች/የአፍ ዙሪያ ቁስለት ያለምንም ህክምና በራሱ ጊዜ ሊጠፋ ይችላል፡፡ ነገር ግን የሚከተሉት ነገሮች ካሉ የህክምና ባለሙያዎን ያማክሩ
💦 የበሽታ መከላከል ብቃትዎ የቀነሰ/የተዳከመ ከሆነ
💦ቁስሉ በሁለት ሳምንት ጊዜ ዉስጥ ካልዳነ
💦 የህመሙ ምልክቶች ከፍተኛ ከሆኑ
💦 ህመሙ በተደጋጋሚ እየተከሰተ ካስቸገረዎ
💦 በአይንዎ ላይ የመቆጥቆጥ ስሜት ከተሰማዎ/ካጋጠመዎ
#ምችን #እንዴት #ልንከላከል #እንችላለን?
የሀርፐስን ቫይረስ ወደ ሌላ ሰዉ/ወደ ሌላ የሰዉነትዎ ክፍል እንዳይዛመት ለመከላከል
💦 ዉሃ የቋጠረ ቁስል ባለበት ወቅት የቆዳ ለቆዳ ንክኪ እንዳይኖር መከላከል
💦ቫይረሱ በከፍተኛ ሁኔታ የሚዛመተዉ በሚያዥበት/ዉሃ በሚቋጥርበት ጊዜ ሌላዉን የሰዉነት ክፍልዎን እንዳይነኩ መጠንቀቅ:- በተለይ አይንዎንና የብልት አካብቢ ለቫይረሱ በጣም ተጋላጭ ስለሆኑ ላለመንካት መጠንቀቅ
የመገልገያ ዕቃዎችን በጋራ ያለመጠቀም፡- እንደ ፎጣ፣ መመገቢያ ዕቃዎችንና የመሳሰሉትን
💦 የእጅዎን ንፅህና መጠበቅ፡- ሌላ ሰዉ ከመንካትዎ በፊት እጅዎን በደንብ መታጠብ

መልካም ጤና