መኀደረ ጤና
2.59K subscribers
36 photos
13 videos
6 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩╩═╝
ስለ ጤናዎ ወሳኝ መረጃዎች💊 ሁሉም ሰው ሊያውቃቸው የሚገባ የጤና መረጃዎችን ከፈለጉ ይህን ቻናል ይቀላቀሉ ይማሩበታል ያስተምሩበታል መልካም ጤና ለሁላችን..


መልካም ጤና ለሁላችን..
Download Telegram
#የሆድ #ጥገኛ #ትላትሎች

የሆድ ጥገኛ ትላትሎች ህፃናትንና አዋቂዎችን የሚያጠቁ ቢሆኑም በአብዛኛዉ
በህፃናት ላይ ይከሰታሉ/ይበዛሉ፡፡ በጣም የተለያዩ የሆድ ጥገኛ ትላትሎች ያሉ
ሲሆን የተለመዱትና በብዛት ከሚገኙት ዉስጥ 👉ወስፋት፣
👉የመንጠቆ ትል፣
👉ጊኒ ወርም፣
👉ስተሮንግሎይድስ፣
👉የኮሶ ትል፣
👉ጃርድያና
👉አሜባ ይገኛሉ፡፡
የሆድ ጥገኛ ትላትሎች ወደ ሰዉነታችን የሚገቡት በቆዳ፣ በአፍንጫና በተበከለ ዉሃና ምግብ
ሲሆን ወደ ሰዉነታችን ከገቡ በኃላ በአንጀታችን ላይ በመራባት ጥሩ ስሜት
የሌላቸዉ የህመም ስሜቶች እንዲከሰቱ ያደርጋሉ፡፡
የህመም ምልክቶቹ
የአንጀት ስርዓት ለዉጥ መኖር፡- የሆድ ጥገኛ ትላትሎች የአንጀት ስርዓት ለዉጥ
እንዲኖር ያደርጋሉ፡፡ ይህም እንደ ጥገኛ ትላትሉ አይነት ሊለያይ የሚችል ሲሆን
ከነዚህም ዉስጥ #የሆድ #ድርቀት#ተቅማጥ ወይም #ልል #ሰገራ እንዲከሰት ያደርጋሉ፡፡
የምግብ ፍላጎት መለወጥ፡- የሆድ ጥገኛ ትላትሎች የሚመገቡትን ምግብዎን
ስለሚሻሙ በብዛት የሚከሰተዉ የምግብ ፍላጎት መጨመር ነዉ፡፡ እንድያዉም
አንዳንድ ሰዎች የምግብ ፍላጎታቸዉ እንደጨመረ እያለና ምግብ በደንብ
እየተመገቡ ሳለ ምንም ክብደት ያለመጨመር ሁኔታ ይታያል፡፡ በተቃራኒዉ ደግሞ
አንዳንድ ሰዎች ላይ የምግብ ፍላጎታቸዉ እንዲቀንስ ያደርጋሉ፡፡
ከምግብ ፍላጎት መቀነስ ጋር ተያይዞ ሰዉነታችን ፓራሳይቱን ለማስወገድ በሚያደርገዉ ጥረት
ዉስጥ ማቅለሽለሽና ማስታወክ በተጨማሪ ሊኖር ይችላል፡፡
ህመም፡- የሆድ ጥገኛ ትላትሎች አንጀት እንዲቆጣ ስሊሚያደርጉ የሆድ ህመም
እንዲከሰት ያደርጋሉ፡፡ የሆድ ጥገኛ ትላትሉ ለረጅም ጊዜ በአንጀት ዉስጥ
ከነበሩና ከአንጀት ዉጪ ወደ ሌሎች ቦታዎች ከተሰ0ራጩ ህመሙ ከአንጀት ዉጪ
በየትኛዉም የሰዉነት ክፍል እንዲኖር/እንዲከሰት ያደርጋሉ፡፡
ተጨማሪ የህመም ምልክቶች፡- ጉንፋን መሰል የህመም ምልክቶች፣ የሆድ መነፋትና ጋዝ መብዛት፣ በሰገራ ላይ የሆድ ጥገኛ ትላትሎችን
መታየት፣በፊንጢጣ ወይም በሴቶች ብልት ዙሪያ ማሳከክና የመሳሰሉት ናቸዉ፡፡
ለሆድ ጥገኛ ትላትሎች መከሰት ምክንያቶች
የሆድ ጥገኛ ትላትሎች በየትኛዉም የአለማችን ክፍል የሚገኙ ቢሆንም ከሰሃራ
በታችና በከፊል ሰሃራማ አካባቢዎች በብዛት ይገኛሉ፡፡ ለሆድ ጥገኛ ትላትሎች
መከሰት ምክንያት ከሆኑት ዉስጥ የሚከተሉት ይጠቀሳሉ፡- #በንፅህና #ያልተዘጋጁ #ምግቦችን #መመገብ #የተበከለ #ዉሃ
#ቆሻሻ #የእጅ #ጣቶች
በደንብ ያልበሰለ ያልተቀቀሉ ስጋ( ለብ ለብ የተደረገ)
ጤናማ ያልሆነ የአመጋገብ ባህሪይ መኖር
በባዶ እግር መሄድ፡- እንደ መንጠቆ ትል ያሉ የሆድ ጥገኛ
ትላትሎች በባዶ እግር
የምንሄድ ከሆነ ትሉ የእግር ቆዳን በስቶ ወደ ሰዉነታችን ይገባል፡፡
ጥገኛ ተዋሲያን በብዛት ወደሚገኙበት ስፍራ መሄድ፡- ለምሳሌ የንፅህና አጠባበቃቸዉ ጥሩ ወደያልሆኑበት ቦታዎች መሄድ የግል ንፅህና አጠባበቅ አነስተኛ/ጥሩ ያለመሆን
የበሽታ መከላከል አቅም ደካማ መሆን/ መቀነስ
የኤች አይቪ ቫይረስ በደምዎ መኖር
በጥገኛ ትላትሎች የተያዙ የቤት እንስሳ ጋር መኖር
ለሆድ ጥገኛ ትላትሎች ሊደረጉ የሚችሉ ህክምናዎች
ለሆድ ጥገኛ ትላትሎች የሚደረገዉ ህክምና እንደጥገኛ ትላትሉ አይነት የሚለያይ
ሲሆን የህክምና ባለሙያዎን በማማከር አስፈላጊዉን ህክምና ማግኘት ይገባል፡፡
እንደ ጥገኛ ትላትሉ የህክምናዉ እርዝማኔ የሚለያይ ስለሆነ ከቀናት እስከ
ሳምንታት ሊዘልቅ ይችላል፡፡
የሆድ ጥገኛ ትላትሎችን #እንዴት #መከላከል #ይቻላል
👉የእጅ ጥፍርዎን ማሳጠር
ይህ ቆሻሻ በጥፍርዎ ስር
እንዳይጠራቀም በማድረግ
ብክለትን ይከላከላል፡፡
👉ሁሉንም አትክልትና ፍራፍሬዎች ከመመገብዎ በፊት በደንብ ማጠብ
👉ከመመገብዎ በፊት ምግብዎን በደንብ ማብሰል ፓራሳይቶችን ለመግደል ይረዳል፡፡
በተለይ ዝናባማ ወራትን ጨምሮ በሌሎች ጊዜያትም ቢሆን መጠጣት ያለብዎ
ፈልቶ የቀዘቀዘ አልያም የተጣራ ዉሃ መሆን አለበት፡፡
👉የግል ንፅህናዎን በደንብ/ በአግባቡ መጠበቅ
ምግብ ከመመገብዎ በፊት፣
👉ምግብ በሚያበስሉበት ወቅትና ከመፀዳጃ ቤት መልስ እጅዎን በዉሃና ሳሙና
መታጠብ
👉 እንዲሁም የቤት እንስሳዎችን ከነኩ/ካጫወቱ በኃላ እጅዎን በደንብ መታጠብ
👉የቤት እንስሳቶችን መደበኛ በሆነ መልኩ ከሆድ ጥገኛ ትላትሎች እንዲፀዱ
ማድረግ ከቤተሰብዎ መሃል አንድ ሰዉ የሆድ ጥገኛ ተዋህሲያን እንዳለበት ከታወቀ
ሌሎች የቤተሰቡ አባላትም መድሃኒት እንዲወስዱ በማድረግ ከሆድ ጥገኛ ትላትሎች እንዲፀዱ ማድረግ።
መልካም ጤና.
#እርግዝናን #የመከላከያ #መንገዶችና #እውነታቸው

ያልተፈለገ እርግዝናን ለመከላከልና ራስዎን ከአባላዘር በሽታዎች ለመጠበቅ ሲባል የተለያዩ መንገዶችን ይጠቀሙ ይሆናል፡፡ ነገር ግን የእነዚህን መከላከያዎች እውነታዎች አውቆና ተረድቶ ጥቅም ላይ ማዋል እጅግ ጠቀሜታ ይኖረዋል
#በወር #አበባ #ጊዜ #የግብረ #ሥጋ #ግንኙነት #ቢደረግ #እርግዝና (ይከሰት #ይሆን ?
👉የወር አበባን በምታይ ጊዜ የግብረ ሥጋ ግንኙነት የምታደርግ ሴት የማርገዝ ዕድሏ የቀነሰ ቢሆንም ሙሉ በሙሉ ግን አይከሰትም ለማለት አይቻልም፡፡ ይህም የሚሆንበት ምክንያት የወር አበባ ከማለቁ በፊት እንቁላል ሊፈጠር ስለሚችልና ወይንም ደግሞ የወንድ ዘር በማኅፀን ውስጥ እስከ 3 ቀን ወይንም ከዚያ በላይ የሚቆይበት አጋጣሚ ስለሚኖር ነው፡፡
#ጡት #ማጥባት #እርግዝናን #ይከላከላል ?
👉ጡት ማጥባት የእንቁላል መፈጠርን የሚከላከል ቢሆንም የሚቆይበት ጊዜ ግን ለጥቂት ወራት ብቻ ስለሆነ ሰውነት ወደቀድሞ ሁኔታው በሚመለስ ጊዜ የማርገዝ ዕድልም አብሮ ስለሚመለስ ጡት ማጥባት እርግዝናን የሚከላከልብት ጊዜ ውስን መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡
#የመጀመሪያ #ጊዜ #የግብረ #ሥጋ #ግንኙነት #ማድረግ #ላልተፈለገ #እርግዝና #ያጋልጣል ?
👉አዎን! ለመጀመሪያ ጊዜ የሚደረግ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ላልተፈለገ እርግዝና ላያጋላጥ ይችላል ብለው የሚያስቡ አንዳንዶች ያሉ ቢሆንም ይህ ከእውነት የራቀ ነው፡፡ በመጀመሪያ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ወቅት ሕመምና ደም መፍሰስ ሊያጋጥም የሚችል ቢሆንም እርግዝናን ከመከላከል ጋር ግን ምንም ዓይነት ግንኙነት የሌለው መሆኑን ተገንዝቦ ተገቢውን ጥንቀቄ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
#የወሊድ #መቆጣጠሪያዎች #ምን #ያህል #እርግዝናን #ይከላከላሉ ?
👉የወሊድ መቆጣጠሪያዎች በትክክለኛው መንገድ ከተተገበሩ ከ90% በላይ የሚሆን የመከላከያ አቅም ያላቸው ሲሆን ተአቅቦ ግን ጥርጥር የሌለው አማራጭ ነው፡፡ የወሊድ መቆጣጣሪያ ለመጠቀም በሚታሰብ ጊዜ የትኛውን ዓይነት እንደምንመርጥና አጠቃቀሙን በተመለከተ ሐኪምዎን ማማከር ተገቢ ነው፡፡
#በግብረ #ሥጋ #ግንኙነት #ጊዜ #ሁለት #ኮንዶሞች #ደርቦ #መጠቀም #በእርግጥ #እርግዝናን #የበለጠ #ይከላከላል ?
👉አብዛኛውን ጊዜ ሰዎች ሁለት ኮንዶምን ደርቦ በመጠቀም የበለጠ ጠቀሜታ እንዳለው ያስባሉ ይህ ግን እጅግ የተሳሳተ እና ከእውነት የራቀ ሲሆን ይባስ ብሎ በሚፈጠረው ፍጭት (Friction) ምክንያት የኮንዶም መቀደድ በማስከተል ላልተፈለገ እርግዝና ለአባላዘር በሽታ የመጋለጥን ዕድል በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራል፡፡ ስለዚህ ሁለት ኮንዶሞችን ደርቦ መጠቅም አይመከርም፡፡
#የወሊድ #መቆጣጠሪያ #እንክብሎችን #መውሰድ #ወዲያውኑ #እርግዝናን #ይከላከላል?
👉የወሊድ መቆጣጠሪያ እንክብሎች አጠቃቀም እና የሚወሰዱበትን ጊዜ በሚገባ ማወቅ እርግዝናን ለመከላከል ጠቃሚ ነው፡፡ የወሊድ መቆጣጠሪያ እንክብሎችን የወር አበባ በመጣ ከመጀመሪያው ቀን እስከ አምስተኛው ቀን ውስጥ መጀመር ወዲውኑ ከአልተፈለገ እርግዝና የሚከላከል ሲሆን፣ ከዚያ ጊዜ ውጭ ከመጀመሩ ግን ወዲያውኑ የመከላከል አቅም ስለማይኖረው ኮንዶምን መጠቀም አስፈላጊ ይሆናል፡፡
#ሁሉም #የወሊድ #መቆጣጠሪያዎች #ከአባለዘር #በሽታዎች #ይከላከሉ #ይሆን ?
👉ከወሊድ መቆጣጠሪያዎች ውስጥ ኮንዶምን መጠቀም ብቻ ከአባላዘር በሽታ ራስን መከላከል የሚቻልበት ዋነኛው መንገድ ነው፡፡
#የወሊድ #መቆጣጠሪያ #እንክብሎች #የሰውነት #ክብደት #ይጨምራሉ ?
👉አንዳንድ ሴቶች የሰውነት ክብደት መጨመርን እንዳስከተለባቸው የሚናገሩ ሲሆን ምክንያቱም የምግብ ፍላጎትን መጨመርን ማስከተሉና ፈሳሽ በሰውነታችን እንዲቀመጥ ማድረጉ መሆኑን ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ ስለዚህም የወሊድ መቆጣጠሪያ እንክብሎች መጠነኛ የሚባል የሰውነት ክብደት መጨመርን ያስከትላሉ፡፡
#የወሊድ #መቆጣጠሪያን #መጠቀም #መሃንነትን #ያስከትላል?
👉አያስከትልም! ሆርሞኖችን በውስጣቸው የያዙ የወሊድ መቆጣጠሪያዎች ለረጅም ጊዜ ከተወሰዱ መሃንነትን ያስከትላሉ ተብሎ የሚታሰብ ቢሆንም እነዚህን የወሊድ መቆጣጠሪያዎች መካንነትን እንደማያስከትሉ ሊያውቁት የሚገባ እውነታ ነው፡፡
#ኮንዶምን #በሌሎች #ቁሳቁሶች #መተካት #ይቻላል?
👉በፍፁም አይቻልም! በግብረ ሥጋ ግንኙነት ጊዜ ኮንዶምን በሌሎች እንደ ላስቲክ፣ ፈኛ፣እና የመሳሰሉ ቁሳቁሶች ተክቶ መጠቀም በፍፁም ተገቢ ያልሆነ ድርጊት እና ከአልተፈለገ እርግዝናም ሆነ ከአባላዘር በሽታም በጭራሽ እንደማይከላከል ሊያውቁት ይገባል

#መልካም #ጤና
#የሳንባ #ምች (Pneumonia)

የሳንባ ምች የምንለው በሳንባ ላይ ሚከሰትን ኢንፌክሽን ነው፡፡
#የሳንባ #ምች #እንዴት #ይከሰታል?
👉በባክቴሪያ
👉በቫይረስ
በሽታን የመከላከል አቅማቸው የደከመ ሰዎች ላይ ደግሞ #በፈንገስ ምክንያትም ይከሰታል
አንድ ሰው አየር በሚያስገባ ጊዜ እነዚህን በሽታ አምጪ ተህዋሲያን ወደ ውስጥ ያስገባል ይህም ወደ ሳንባ በመሄድ ኢንፌክሽን ይፈጥራል
#ለሣንባ #ምች #ተጋላጭነት #የሚዳርጉ #ሁኔታዎች
👉ዕድሜ፦ዕድሜያቸው ከ1 ዓመት በታች የሆኑ እና ከ65 ዓመት ዕድሜ በላይ የሆኑ ሰዎች
👉በሽታን የመከላከል አቅማቸው የተዳከመ ሰዎች
👉በጉንፋን የተጠቁ ሰዎች
👉የአስም ሕመም ተጠቂ የሆኑ ሰዎች
👉ሲጋራን ማጤስ
👉የአልኮል መጠጥን እጅግ ማዘውተር
#የሳንባ #ምች #ሕመም #ምልክቶች
👉አክታ የተቀላቀለ ሳል
👉ትኩሳት
👉ትንፋሽ ማጠር
👉የራስ ምታት
👉ብርድ ብርድ ማለት
👉የደረት ውጋት በሳል ጊዜ የሚብስ የልብ ትርታ መጨመር
👉ላብ ላብ ማለት
👉የሰውነት ድካም
👉የምግብ ፍላጎት መቀነስ
👉ማቅለሽለሽ እና ማስመለስ

#የሳንባ #ምችን #እንዴት #መከላከል #ይቻላል?
👉ሲጋራ ማጤስን ማቆም
👉እጅን በሚገባ መታጠብ
የሳንባ ምችን ሕመምተኞች በቤት ውስጥ ሊያደርጓቸው የሚችላቸው ሕክምናዎች፤
👉ፈሳሽ በብዛት መውሰድ
👉ዕረፍት ማድርግ
ትኩሳትን ማስታገሻ በመውሰድ መቆጣጠር
በቫይረስ የሚከሰት የሳንባ ምች በአብዛኛውን ጊዜ በጉንፋን ምልክቶች የሚጀምር ሲሆን #ትኩሳት #ደረቅ ሳል #ራስ ምታት#ቁርጥማት እና #የድካም #ስሜትን ያስከትላል ትንፋሽ ማጠር እና አክታ ከአንድ ቀን በኋላ ሊከሰቱ ይችላሉ፡፡
በባክቴሪያ የሚከሰት የሳንባ ምች ከፍተኛ #ትኩሳት #አክታን #የቀላቀለ #ሳል ከፍተኛ #የሰውነት #ማላብ #የልብ ምት መጨመር እና በፍጥነት የሚጨምር የአተነፋፈስ ስርዓት ይኖራቸዋል፡፡
የሣንባ ምች ሕክምና ህመሙን እንዳስከተለው ተህዋስያን ዓይነት፤ እንደ ሕመሙ ክብደት እና ተጨማሪ ሕመም መኖር ሁኔታ ይለያያል፡፡
በሕመሙ የተጠቁ ሰዎች ወደ ሕክምና ቦታ በመሄድ ሐኪምን በማማከር ሕክምናውን በመውሰድና በሚገባ በመከታተል ከበሽታው መዳን ይቻላል

#መልካም #ጤና
#ኪንታሮት - (Hemorrhoids)

#ኪንታሮት በፊንጢጣ ውስጥ እና በታችኛው ትልቁ አንጀት አካባቢ በህብረት
የሚገኙ የደም መልስ የደም ቧንቧዎች/ ስሮች ሲያብጡና ሲቆጡ የሚፈጠር
እብጠት ነው።
---
ለዚህ እብጠት(ኪንታሮት) መፈጠር መንስኤ ከሚሆኑት ውስጥ:-
👉ሠገራን በምናስወግድበት ወቅት አብዝተን ወይም ለረጅም ግዜ ማማጥ።
👉 ለረጅም ግዜ የቆየ ሳል።
👉ከመጠን በላይ የሆነ ውፍረት።
👉 ለረጅም ግዜ የቆየ የሆድ ድርቀት ወይም ተቅማጥ።
👉 እንዲሁም ሌሎች ሆድ ውስጥ ያለ ግፊት እንዲጨምር የሚያድርጉ ፣
(ለምሳሌ ለሆድ እብጠት የሚጋልጡ የጉበት በሽታዎች)።
👉በተጨማሪ በእርግዝና ግዜና እድሜያቸው ከ40 አመት በላይ የሆኑ ጎልማሶች ለይ በስፋት ይታያል።
#የኪንታሮት #ምልክቶችና #ሊያስከትላቸው #የሚችላቸው #ተዛማጅ #ችግሮች:-
👉 በፊንጣጣ ላይና ከፊንጢጣ ውስጥ የሚታይ እብጠት።
ኪንታሮት የውጪ/ውጫዊ ኪንታሮት (External Hemorrhoid)
እና የውስጥ ውስጣዊ ኪንታሮት(Internal Hemorrhoid) በመባል በሁለት ይከፈላል ። #የውስጥ#ውስጣዊ
👉የሚባለው ኪንታሮት(Internal Hemorrhoid) አራት ደረጃዎች ያሉት ሆኖ፣
የመጀመሪያ ደረጃ የሚባለው ላይ እብጠቱ ወደ ውጪ ወጥቶ አይታይም።
እንዲሁም ሁለተኛ ደረጃ ላይም ሰገራ በሚወገድበት ወቅት ላይ ብቻ ነው
እብጠቱ ሊታይ የሚችለው።
👉 ሰገራ በምናስወገድበት ሰዓት ህመም መሰማት፣ ማሳከክ ወይ አለመመቸት።
👉ህመም ሳይኖር በሰገራ ላይ ወይንም በምናፀዳበት ወረቀት ላይ ደም መኖር።
👉አንዳንዴ ደግሞ ያለቁጥጥራችን የሰገራ መውጣት።
👉አልፎ አልፎ ደግሞ በደንብ ሊደማ ስለሚችል ወይም ቀስ በቀስ የሚደማው
ደም ለደም ማነስ ሊያጋልጠን ይችላል።
👉አንዳንዴ እብጠቱ በመታጠፍ ወይም እብጠቱ ውስጥ ያሉ ደም ስሮች በረጋ
ደም በመዘጋት ከፍተኛ ህመም ሊሰማን ይችላል። ይህኔ ፈጥነን በአቅራቢያችን
ሚገኝ ሆስፒታል መሄድ ይኖርብናል።
---
---
#ከታች #የተዘረዘሩትን #ዘዴዎች #በመጠቀም #የኪንታሮት #ህመም #ስሜት #እና #መጠኑ
#እንዲቀንስ #ማድረግ #ይቻላል:-
👉ለብ ባለ ውሃ ውስጥ ሁለት/ሶስት ማንኪያ ጨው በመጨመር ከ15-20 ደቂቃ
በቀን ሁለት/ሶስት ግዜ በመቀመጫ/በፊንጣጣ መዘፍዘፍ።
👉 የሎሚ ጭማቂ መቀባት።
👉 በፋይበር የበለፀጉ አትክልትና ፍራፍሬዎችን መመገብ።
👉እብጠቱ ላይ በረዶን መያዝ ፣ በቀን ብዙ ግዜ እንደዚያ ማድረግ እብጠቱ
እንዲቀንስ ያደርጋል።
👉በቂ ውሃ መጠጣት።
👉ሰገራ በመጣ ግዜ ማስገወድ። አብዝተን አለማማጥ።
👉እንዲሁም ሀኪም ቤት በመሄድ የሚሰጠውን ምክርና የህክምና አገልግሎት በአግባቡ መከታተል።

#መልካም #ጤና
#የጥርስ #መቦርቦር

#የጥርስ #መቦርቦር የሚከሰተው በአፋችን ውስጥ የሚገኙ ጀርሞች (ባክቴሪያ) ጥርሳችንን የሚያበሰብሱ አሲዶችን በሚያመነጩበት ጊዜ ነው ይህም በጥርሳችን ላይ የተቦረቦሩ ቀዳዳዎችን እንዲፈጠሩ ያደርጋል የተቦረቦሩ ጥርሶች ህመም ከማስከተል ባለፈ ለኢንፌክሽን ያጋልጣሉ።

#የጥርስ #መቦርቦር #እንዴት #ይከሰታል?

👉በጥርስ ላይ ተለጥፈው የሚቀሩ ምግቦች ካልተፀዱ ይከማቹና የባክቴሪያዎች መራቢያ እና ምግብ ይሆናሉ #ባክቴሪያዎች በሚመገቡ ጊዜ ከውስጣቸው አሲድን ይረጫሉ፣ ይህም ጥርሳችን እንዲቦረቦርና እንዲበሰብስ ያደርጋል

#ለጥርስ #መቦርቦር #የሚያጋልጡ #ሁኔታዎች

👉ጥርስን በሚገባና በመደበኛ ሁኔታ አለማፅዳት
👉ጣፋጭነት የበዛባቸው ምግቦች ማዘውተር
👉የፍሎራይድ እጥረት መኖር
👉የስኳር ህመም ተጠቂ መሆን
👉በህመም ወይንም በተለያዩ መድሀኒቶች ምክንያት የአፍ ድርቀት ሲኖር
👉ሲጋራን ማጤስ ናቸው

#የጥርስ #መቦርቦር #የሚያስከትላቸው #ምልክቶች

👉የጥርስ ህመም ስሜት
👉 በተጎዳው ጥርስ አካባቢ የድድ ማበጥ
👉 መጥፎ የሆነ የአፍ ጠረን መኖር
👉በጥርስ ላይ ነጭ ግራጫ ቡኒ ወይንም ጥቁር ቀለማት የያዙ የተቦረቦሩ ቦታዎች መኖር ናቸው

#የጥርስ #መቦርቦርን #እንዴት #መከላከል #ይቻላል ?

👉ጥርስዎን በቀን ውስጥ ቢያንስ ሁለት ጊዜ (ከቁርስ በኃላ እና ከመተኛትዎ በፊት) የፍሎራይድ ኬሚካል ባለው የጥርስ ሳሙና መታጠብ
👉በማንኛው ግዜ ምግብ ከተመገቡ በኃላ አፍዎን በንፁህ ውሀ በሚገባ መጉመጥመጥ
👉ከእንቅልፍ በፊት ጥርስዎን ከታጠቡ በኃላ ምንም አይነት ምግብ አለመመገብ
👉ጣፋጭ የበዛባቸው ምግቦችን ከምግብ ፕሮግራም ውስጥ ማስወገድ
👉 ልጆች ለጥርስ መቦርቦር ተጋላጭነታቸው ከፍተኛ ስለሆነ ሁሌም ስለ ጥርስ ፅዳት አጠባበቅ ማስተማር
👉 የጥርስ ሀኪምዎ ጋር በዓመት አንድ ጊዜ በመሄድ ጥርስዎን በባለሞያ ማሳጠብና ማስመርመር

#ማሳስቢያ❗️❗️

የጥርስ ህመም ሲሰማዎ ጊዜ ሳይሰጡ ወደ ሀኪም መሄድን አይዘንጉ ምክንያቱም የህመም ስሜቱ ከጥቂት ጊዜ በኃላ በራሱ ሊጠፋ ቢችልም የጥርስ መቦርቦር ግን ያለ ህመም ሊቀጥል ይችላል። በአፋጣኝ ህክምና ካልተደረገ ጥርስዎን እስከማጣት ሊያደርስዎ ይችላል

መረጃዉ ከተመቸዎት ይቺን 👍 አይንፈጉን

#መልካም #ጤና
#ግላውኮማ(Glaucoma)

#ግላውኮማ የምንለው የአይን ህመም በአይናችን ነርቭ ላይ ችግር የሚያስከትል ሲሆን በአይናችን ውስጥ የሚገኘው ግፊት መጨመር ምክንያት የሚከሰት ነው። የዚህ ግፊት መጨመር በአይናችን የምናያቸውን ምስሎች ወደ አንጎል የሚውስደውን የአይናችንን ነርቭ ይጎዳል ይህም በቀጣይነት ቋሚ ለሆነ የአይን ብርሃንን እጦት ይዳርጋል።

#የግላኮማ #ዓይነቶች #ምንድ #ናቸው?

🔘ሁለት ዋነኛ ዓይነቶች አሉ

👉Open-angle glaucoma በጣም የተለመደ ዓይነት ነው በዓይናችን ውስጥ ያለውን የውኃ ማስተላለፊያ አካል trabecular meshwork ተብሎ የሚጠራዉ ጤናማ ይመስላል, ግን ፈሳሹ እንደ ልብ አይንቀሳቀስም
👉Angle-closure glaucoma. በምዕራቡ ዓለም በእስያ እንጂ በስፋት የተለመደ አይደለም በአይንዎ መካከል ያለው ፍሰት በጣም ጠባብ ስለሚሆን ዓይንዎ በትክክል አይሰራም. ይህ በአይኑ ውስጥ ድንገተኛ መጨናነቅ ሊያስከትል ይችላል. በተጨማሪም በአይንዎ ውስጥ ያለውን ሌንስ ጭጋግ መሰል ነገር ያለብሰዋል

👉ግላውኮማ በሚጀምርበት ጊዜ የሚያሳየው ቀዳሚ ምልክት ወይንም የህመም ስሜት ስለሌለ ማንኛውም ሰው መደበኛ የሆነ የአይን ህክምና ማድረግ አስፈላጊ ነው ይህም አይናችን ለከፋ ጉዳት ከመጋለጡ በፊት ህክምና እንድናደርግለት ይረዳናል። ከ40 አመት እድሜ በላይ ያሉ ሰዎች በአመት አንድ ጊዜ ወደ ሃኪም በመሄድ ምርመራን ማድረግ አለባቸው።

#የአይናችን #ውስጥ #ግፊት #ለምን #ይጨምራል?

🔘ግላውኮማ የሚከሰተው በአይናችን ውስጥ የሚገኘው ግፊት ሲጨምር ነው ያልን ሲሆን ይህደግሞ
👉በኢንፌክሽን
👉በአይን በቀዶ ጥገና ምክንያት በፊተኛው የአይናችን ውስጥ የሚገኘው ፈሳሽ በጤናማ ሁኔታ መንሸራሸር ሲያዳግተው ነው።
ግላውኮማ በአብዛኛው ሁለቱንም አይነቶች የሚያጠቃ ሲሁን የህመሙ ክብደት ግን ሊለያይ ይችላል።
#በግላውኮማ #የሚጠቁ #እነማን #ናቸው?

👉ከአርባ አመት እድሜ በላይ የሆኑ
👉በግላውኮማ የተጠቃ ቤተሰብ ያላቸው
👉የስኳር ህመምተኞች
👉የአይን ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች

#የግላውኮማ #ህመም #ምልክቶች #ምንድን #ናቸው?

🔘በአብዛኛው ግላውኮማ በቅድሚያ የህመም ምልክት ላያሳይ ቢችልም ከጊዜ በሗላ ግን የመጀመሪያ ምልክት የሚሆነው
በጥግ በኩል የሚጀምር የአይን ብርሃን ችግር ነው።
#ከምልክቶቹ #ውስጥ
👉ድንገተኛ የሆነ የአይን ህመም
👉ከፍተኛ የራስ ምታት
👉የአይን ብዥታ
👉ጥርት ያለ እይታ አለመኖር
👉የአይን መቅላት
👉የአይን ብርሃን ማጣት
👉የአይን እይታ ጥበት ናቸው
እነዚህ ሁኔታዎች ሲያጋጥምዎ በአፋጣኝ ወደ አይን ሀኪም መሄድ ይጠበቅቦታል።

#ግላውኮማን #መከላከል #ይቻላል?

🔘ግላውኮማ እንዳይከሰት መከላከል የማንችል ሲሆን ነገር ግን በቶሎ የህመሙ መኖር ከታወቀ ለመቆጣጠርና እንዳይባባስ ማድረግ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው።
በግላውኮማ ምክንያት የተከሰተ የአይን ብርሃን ጉዳት ተመልሶ ሊስተካከል የማይችል ሲሆን የነበረው ጉዳት እየተባባሰ እንዳይሄድ ግን የአይን ግፊት መጠኑን መቀነስ ይቻላል። ህክምናቸውን በሚገባ የሚከታተሉ ታካሚዎች የአይን ብርሃናቸውን ማዳን ይችላሉ።

#መልካም #ጤና
#የጥፍር #ፈንገስ #ኢንፌክሽን

#የጥፍር #ፈንገስ #ኢንፌክሽን የምንለው በፈንገስ ምክንያት የሚከሰት ህማምን ሲሆን ከአንድ በላይ ጥፍሮችንም ሊያጠቃ ይችላል።
የጥፍር ፈንገስ ጥፍራችን እንዲወፍርና የህመም ስሜት እንዲሰማን ያደርጋል። የጥፍር ፈንገስ ኢንፌክሽኑ በጣቶችዎ መካከል ሊዛመትም ይችላል።

#የጥፍር #ፈንገስ #ምልክቶች #ምንድን #ናቸው

👉የጥፍር መወፈር
👉የጥፍር ቀለም ወደ ቢጫነት መለወጥ
👉የጥፍር ቅርጽ መለወጥ
👉መጥፎ ጠረን ማምጣት ናቸው።
የጥፍር ፈንገስ በአብዛኛው በእግር ጥፍሮች ላይ የሚከሰት ሲሆን አልፎ አልፎ በእጅ ጣት ጥፍሮች ላይም ይከሰታል።

#ለጥፍር #ፈንገስ #ተጋላጭነትን #የሚጨምሩ #ሁኔታዎች #ምንድን #ናቸው?

👉 እድሜ መጨመር
👉ከፍተኛ ላቦት መኖር
👉በባዶ እግር ውሀ ዋና ቦታ፣ በጂም እና የገላ መታጠቢያ ቦታዎች መራመድ
👉ስኳር ወይም በሽታ የመከላከል አቅምን የሚያዳካሙ ህመሞች መኖር ናችው።

#የጥፍር #ፈንገስ #እንዴት #መከላከል #ይቻላል

👉እጅዎን እና እግርዎን በሚገባ መታጠብ እና ማድረቅ
👉በፈንገስ ያልተበከለ የጥፍር መቁረጫን መጠቀም ወይንም በሚገባ አጽድተን መጠቀም
👉ላቦትን የሚመጡ ካልሲዎችን መጠቀም
👉በየትኛውም ቦታ ጫማ ተጫምተው መንቀሳቀስ
👉የአየር ዝውውርን የሚፈቅዱ ጫማዎችን መጠቀም
👉ጥፍርዎን ለማስዋብ የሚጠቀሟቸው እቃዎች በሚገባ የጸዱ መሆናቸው ማረጋገጥ
👉የጥፍር ማስዋቢያ እቃዎችን ከሌሎች ሰዎች ጋር አለመጋራት ናቸው።

#ህክምናው

👉የጥፍር ፈንገስን ለመከላከል ዋናውና ቀላሉ መንገድ ጥፍሮቻችንን አጭርና ንፁህ አድርጎ መያዝ ነዉ በበሽታዉ ከተጠቃን በኋላ ግን በሀኪም ትዛዝ የሚሰጡ መድሀኒቶች አሉ ከነዚህም ውስጥም
በአፍ የሚወሰዱ የፈንገስ መድሀኒቶች
በቅባት መልክ የተዘጋጁ መድሀኒቶች ናቸው

#ሀኪምዎን #ማማከር #የሚገባው #መቼ #ነው

የጥፍር ፈንግስ ኢንፌክሽን በከፍተኛ ሁኔታ ከአንድ ጥፍር ወደ ሌላው ሊዛመት ስለሚችልና ተገቢው ጥንቃቄ ካልተወሰደ ደግሞ ሌሎች የቤተሰብ አባሎችንም ሊያጠቃ ስለሚችል ወደሀኪም በመሄድ ተገቢውን መድሀኒት በታዘዘው መሰረት በሚገባ በመጠቀም እንዲለቅ ማድረግ ይቻላል

ጠቃሚ መረጃ ነውና ለወዳጆችዎ ያከፍሉ አብሮነታችሁን በዚ 👍 አሳዩን


#መልካም #ጤና