Forwarded from እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net
YouTube
የእስላማዊ ባንክ አሉታዊ ገፅታዎች
• እስላማዊ ፋይናንስ ምንድነው?
• የእስላማዊ ፋይናንስ ችግሮች
1. ወለድን መከልከል ዘመናዊ የአክራሪዎች የቁርአን ትርጓሜ ነው
2. በእስላማዊ ፋይናንስ ወለድ የለም የሚለው አባባል አታላይ ነው
3. እስላማዊ ፋይናንስ በፅንፈኛ እስላማውያን የሚቀነቀንና ከእነርሱ ጋር የተቆራኘ ሥርዓት ነው
4. እስላማዊ ፋይናንስ የተለየና ተፎካካሪ የፋይናንስ ሥርዓትን ለመዘርጋት ያለመ ነው
5. እስላማዊ ፋይናንስ ኢ…
• የእስላማዊ ፋይናንስ ችግሮች
1. ወለድን መከልከል ዘመናዊ የአክራሪዎች የቁርአን ትርጓሜ ነው
2. በእስላማዊ ፋይናንስ ወለድ የለም የሚለው አባባል አታላይ ነው
3. እስላማዊ ፋይናንስ በፅንፈኛ እስላማውያን የሚቀነቀንና ከእነርሱ ጋር የተቆራኘ ሥርዓት ነው
4. እስላማዊ ፋይናንስ የተለየና ተፎካካሪ የፋይናንስ ሥርዓትን ለመዘርጋት ያለመ ነው
5. እስላማዊ ፋይናንስ ኢ…
Forwarded from እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net
ስሙት መንፈስን የሚያድስ ውብ ዝማሬ https://www.youtube.com/watch?v=_pEE_x44_48
Forwarded from እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net
ግራኝ አሕመድን የሚያወድሱ ቲ-ሸርቶች በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ እየተቸበቸቡ ነው፡፡ የኦቶማን ቱርኮችና የአረብ ማምሉኮች ቅጥረኛ የነበረው ግራኝ የፈፀመው ጭፍጨፋ የጎዳው ክርስቲያኑን ብቻ ሳይሆን ሙስሊሙንም ጭምር ነው፡፡ ይህንን የማያውቅ ታሪክ ያንብብ!
Forwarded from እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net
መሐመድ ለመስቀል የነበረው ጥላቻ 👇👇👇
http://www.ewnetlehulu.org/am/muhammad/mo_vs_cross/
http://www.ewnetlehulu.org/am/muhammad/mo_vs_cross/
Forwarded from እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net
የሃይማኖት ጦርነት ለመቀስቀስ የታለሙ የአሕመድ ግራኝ ቲ-ሸርቶችን ለብሰው የታዩት ሙስሊም አሸባሪዎች መታሰራቸው ተሰማ። ሙስሊም አክቲቪስቶች እያለቃቀሱ ነው። ይህንን ወንጀል የፈፀሙትን በመደገፍ እየተንጫጩ የሚገኙት ሁሉ እንደሚታሰሩ ተስፋ እናደርጋለን። የቢላል ሚድያ ሙሾ የሚከተለውን ይመስላል:-
-------------
ምን እየተካሄደ ነው
የኢማም አህመድ ስም ያረፈበትን ቲሸርት ለብሳችኋል በሚል የታሰሩት ወንድሞቻችን ፍርድ ቤት ቀርበው የዋስትና መብታቸው ተነፈገ።
በሳሪስ አዲስ ሰፈር በሚገኘው በሒክማ መስጂድ ሲያስተምሩ የነበሩት ሦስቱ ወንድሞቻችንን አዲስ ሙሉጌታ(ቢላል)፣ ጧሂርና ሙሀመድ ከሚያስተምሩበት መስጊድ በፖሊስ ተይዘው የታሰሩት ከአራት ቀናት በፊት ቢሆንም ዛሬ (ከአራት ቀናት ቡኃላ ) በንፋስ ስልክ ላፍቶ ችሎት ምድብ ቀርበው ነበር።
--------------

❤1
Forwarded from እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net
መነበብ ያለበት አዲስ መጣጥፍ
ሙሐመድ አብድ ወረሱል አል-ሸይጧን! ሙሐመድና አጋንንታዊ ልምምዶቹ 👇👇👇
http://www.ewnetlehulu.org/am/mo-rasul-alshaytan/
ሙሐመድ አብድ ወረሱል አል-ሸይጧን! ሙሐመድና አጋንንታዊ ልምምዶቹ 👇👇👇
http://www.ewnetlehulu.org/am/mo-rasul-alshaytan/
❤1
Forwarded from እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net
ሰሞኑን የተወሰኑ ሙስሊሞች “የመጽሐፍ ቅዱስ ግጭት” ብለው በማሕበራዊ ሚድያዎች ላይ እየተቀባበሉት ለሚገኙት አንድ ሙግት ምላሽ እንሰጣለን፡፡ ሙግቱ እንዲህ የሚል ነው፡-
~~~~~~~~~~
መቼም ዳንኤልና ኤርሚያስ በቁርአን ባይጠቀሱም የእስራኤል ነቢያት ሆነው የተናገሩት ትንቢት እንደተፈፀመ እናያለን፤ ነገር ግን የዳንኤና የኤርሚያስ መፅሃፍ ታሪክ የገባበት መፅሃፍ መሆኑን ቅቡል ነው፤ ከዚህ ጭማሬ ጋር ተያይዞ እርስ በእርሱ ይጋጫል፤ ይህም ግጭት፦
1. አንዱ ናቡከደነፆር ኢየሩሳሌምን የከበባት ኢዮአቄም በነገሰ በሶስተኛው አመት ነው ሲለን፦
ዳን1:1፤ የይሁዳ ንጉሥ "ኢዮአቄም" በነገሠ "በሦስተኛው ዓመት" የባቢሎን ንጉሥ "ናቡከደነፆር" ወደ "ኢየሩሳሌም መጥቶ ከበባት"።
2. ሌላው ደግሞ የኢያቄም ንግስና አራተኛው አመት ላይ የናቡከደነጾር የመጀመሪያው አመት ነው ይለናል፤በዚህ ጊዜ ገና ኢየሩሳሌም እንደሚከብ ትንቢት ተነገረ፦
ኤር.25:1 በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ "በኢዮአቄም በአራተኛው ዓመት"፥ በባቢሎን ንጉሥ "በናቡከደነፆር በመጀመሪያው ዓመት"፥ ስለ ይሁዳ ሕዝብ ሁሉ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው።
ኤር 25:9 ልኬ የሰሜንን ወገኖች ሁሉ ባሪያዬንም የባቢሎንን ንጉሥ ናብከደነዖርን እወስዳለሁ፥ "በዚህችም ምድር በሚቀመጡባትም ሰዎች በዙሪያዋም ባሉ በእነዚህ አሕዛብ ሁሉ ላይ አመጣቸዋለሁ"፤ ፈጽሜም አጠፋቸዋለሁ፥ ለመደነቂያና ለማፍዋጫም ለዘላለምም ባድማ አደርጋቸዋለሁ።
የቱ ነው ትክክል? ናቡከደነጾር ኢየሩሳሌም የከበበው በኢያቄም ንግስና በሶስተኛ አመት ወይስ ከኢያቄም ንግስና አራተኛው አመት በኃላ?
~~~~~~~~~~~~~
መልስ
ሁለቱም ትክክል ናቸው፡፡
በባቢሎናውያን አቆጣጠር መሠረት አንድ ንጉሥ ከነገሠ በኋላ የመጀመርያው የንግሥና ዓመት የማይቆጠር ሲሆን አዲስ ዓመት ከገባ በኋላ አንድ ተብሎ ይጀመራል፡፡ ነገር ግን በአይሁድ አቆጣጠር መሠረት ንጉሡ ዙፋን ላይ የወጣበት ዓመት የመጀመርያው ዓመት ተብሎ ይቆጠርለታል፡፡ ስለዚህ በባቢሎን ምድር ይኖር የነበረው ነቢዩ ዳንኤል የባቢሎናውያንን የንግሥና ዘመን አቆጣጠር በመጠቀም ስለቆጠረ የናቡ ከደነፆር ወረራ ኢዮአቄም በነገሠ በሦስተኛው ዓመት እንደሆነ የጻፈ ሲሆን ነቢዩ ኤርምያስ ግን በይሁዳ ምድር ስለነበረ በአይሁድ አቆጣጠር መሠረት የመጀመርያውን የንግሥና ዓመት ጨምሮ በመቁጠር ኢዮአቄም በነገሠ በአራተኛው ዓመት ናቡ ከደነፆር በነገሠ በመጀመርያው ዓመት እንደሆነ ጽፏል፡፡ ንጉሥ ኢዮአቄም የነገሠው በ668 ዓ.ዓ. ስለነበር ነቢዩ ኤርምያስ በተጠቀመው የአይሁድ አቆጣጠር መሠረት አራተኛው የንግሥና ዓመቱ 665 ዓ.ዓ. ነው፡፡ ዳንኤል በተጠቀመው የባቢሎናውያን አቆጣጠር መሠረት የመጀመርያው የንግሥና ዓመቱ 667 ዓ.ዓ ሲሆን ሦስተኛው የንግሥና ዓመቱ በተመሳሳይ 665 ዓ.ዓ. ነው፡፡ ስለዚህ በሁለቱ መካከል ግጭት የለም፡፡ (ለበለጠ መረጃ አ.መ.ት. ማጥኛ ገፅ 1297 እንዲሁም Gleason L. Archer; Encyclopedia of Bible Difficulties, p. 288)

ጮሌው ኡስታዝ ወሒድ ዳንኤል 7፡13-14 ላይ የሚገኘውን ስለ ክርስቶስ አምላክነት የሚናገረውን ጥቅስ በተመለከተ ለጻፈው በስህተት የተሞላ ጽሑፍ የሰጠነውን ምላሽ ካነበበ በኋላ የመጀመርያውን ጽሑፍ ኤዲት አድርጎ መልሶ ለጥፎታል፡፡ በጥቅሱ ትርጓሜ ዙርያ የአይሁድ ሊቃውንት ያላቸውን አቋም በተመለከተ የፈፀመውን አሳፋሪ ቅጥፈት በመሰረዝ ለማስተካከል ሞክሯል፡፡ በመጀመርያው ጽሑፉ ውስጥ እንዲህ ብሎ ነበር፡- “የአይሁድ ኮሜንቴርይ አንዳቸውም “የሰው ልጅ የሚመስል” የተባለው ዐውዱ ላይ መሲሁ ነው ብሎ የሰጡበት ማብራሪያ የለም።”
ይህ አባባሉ ቅጥፈት መሆኑን ማስረጃዎችን በማጣቀስ ስላጋለጥነው በሁለተኛው ጽሑፉ ውስጥ ይህንን ሐሳብ በመሰረዝ እንዲህ ሲል ጽፏል፡-
“የአይሁድ ኮሜንተርይ፡- “የሰው ልጅ የሚመስል” የተባለው ዐውዱ ላይ የእስራኤል ሕዝብ ነው” ብለው የፈሰሩት፡፡”
ከአጻጻፉ እንደሚስተዋለው ወሒድ ሆዬ ጽሑፋችንን ሲያነብና አሸማቃቂ ስህተቱን ሲያስተውል ተርበትብቶ ኖሮ ኤዲት ሲያደርግ ግራመሩን እንኳ አስተካክሎ መጻፍ አልቻለም፡፡ በቀደመው ጽሑፉ “የሰው ልጅ የሚመስል” የሚለውን አንዳቸውም መሲሁ እንደሆነ እንዳልተናገሩ የገለጸ ሲሆን በሁለተኛው ጽሑፉ ደግሞ ይህንን ግልፅ ቅጥፈቱን በማሻሻል “የእስራኤል ሕዝብ ነው” ብለው መተርጎማቸውን ይነግረናል፡፡ ትክክለኛው መረጃ ግን “የአይሁድ ሕዝብ ነው” በማለት የተረጎሙ በተለይም አንዳንድ ዘመንኛ የአይሁድ ሊቃውንት ቢኖሩም ከጥንት የነበረው አቋም “መሲሁ ነው” የሚል መሆኑ ነው፡፡ የወሒድ አገላለፅ ከመጀመርያው የተሻለ ቢሆንም አሁንም ሙሉ እውነታን የሚያንጸባርቅና ሃቀኛ አይደለም፡፡ ቢሆንም ግን ከቀደመው ቅጥፈቱ የተሻለ ነው፡፡ ነገር ግን ስንት ዘመን ሙሉ የተሳሳተ መረጃ በማስተላለፍ አንባቢን ሲያስቱ ከኖሩ በኋላ እንዲህ ድምጽ አጥፍቶ ኤዲት በማድረግ ለማረም መሞከር ፌር አይደለም፡፡ ስለዚህ ወሒድ ሃቀኛ መምህር ነኝ የሚል ከሆነ ስህተት መፈፀሙን በግልፅ አምኖ ያሳሳታቸውን ተከታዮቹን ይቅርታ ሊጠይቅ ይገባዋል፡፡ በጽሑፎቹ ውስጥ የሚገኙ ቀደም ሲል ያጋለጥናቸውን ሌሎች በርካታ የመረጃ ስህተቶችንም በዚሁ መንገድ ማረም ይኖርበታል፡፡ ነገር ግን ለዚህ የሚበቃ ስብዕና ያለው አይመስልም፡፡
ሙሉ ምላሻችንን በዚህ ሊንክ ታገኛላችሁ፡- http://www.ewnetlehulu.org/am/son-of-man/

👍3
"ሙስሊም-ጠልነት በኢትዮጵያ፤ የሰሜኑ ፖለቲካና አፈታሪክ ውርስ?" በተሰኘ ርዕስ ፋኢዝ መሐመድ የተባለ ጸሐፊ ወደ ገበያ ማውጣቱ ይታወሳል፡፡ ሰልቄ በብዙ ትዝብት አንብቤዋለሁ፡፡ ከዚህም መጽሐፍ ስርጭት በኋላ ሁሉም ማለት በሚያስችል ደረጃ ስለ ጠልነት በማውራት ቤተክርስቲያንንና ማጥቃት የሚፈልጉትን ብሔር በመወረፍ ላይ ይገኛሉ፡፡ ይህን ግዙፍ ኩሸት እያዩና እየሰሙ ዝም ማለት አላስቻለኝም፡፡ ስለዚህ ከቅርብ ቀን ጀምሮ "በኢትዮጵያ ሙስሊም-ጠልነት አለን? ካለስ ምክንያም ምንድን ነው?" በሚል ርእስ የመጽሐፉን ምልከታየን አቀርባለሁ፡፡
ሳሂህ ኢማን ነኝ፤
ቸር ይግጠመን!
ሳሂህ ኢማን ነኝ፤
ቸር ይግጠመን!
❤1
Forwarded from እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net
ተውራትና ኢንጅል መጽሐፍ ቅዱስ ናቸውን?
ለአቡ ሃይደርና ለመሰሎቹ ያላዋቂ ሙግት የተሰጠ የማያዳግም ምላሽ http://www.ewnetlehulu.org/am/the-holy-bible/tawrat-injil/
ለአቡ ሃይደርና ለመሰሎቹ ያላዋቂ ሙግት የተሰጠ የማያዳግም ምላሽ http://www.ewnetlehulu.org/am/the-holy-bible/tawrat-injil/
Forwarded from እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net
ሙሐመድ በኢሳያስ 29፡12?
“መጽሐፉን መንበብ ለማያውቅ፡- ይህን አንብብ ብለው በሰጡት ጊዜ እርሱ ፡- ማንበብ አላውቅም ይላቸዋል” 👇
http://www.ewnetlehulu.org/am/mo-in-isa-29-12/

ሙስሊም ጠልነት በኢትዮጵያ አለን? ካለስ ለምን?
ሙስሊም ጠልነት በኢትዮጵያ፤ የሰሜኑ ፖለቲካና አፈታሪክ ውርስ የተሰኘው መጽሐፍ
ምልከታ
በሳሂህ ኢማን
መንደርደሪያ፡-
እለቱ ሐሙስ ነው፤ ለአንድ ጉዳይ እግሮቼ እየመሩ አንዋር መስጊድ አካባቢ ወዳሉ ሱቆች አደረሱኝ፡፡ ዐልፎ ዐልፎ መጽሐፍት መግዛት ሲያሰኘኝ የምሄደውና የምገዛው እዛ ነው፡፡ በእግረ መንገድ ወደ አንዱ ኢስላማዊ መጽሐፍት ወደ ሚሸጡበት ሱቅ ጎራ ስል "ሙስሊም-ጠልነት በኢትዮጵያ፤ የሰሜኑ ፖለቲካና አፈታሪክ ውርስ" በሚል ርእስ በፋኢዝ ሙሐመድ የተጻፈው መጽሐፍ እይታዬ ውስጥ ገባ፡፡ በማኅበራዊ ሚዲያዎች ማስታወቂያውን ዐይቼ ነበር፡፡ እኔ አንዋር መስጊድ የደረስኩት በማስታወቂያ ከተነገረው መውጫ ቀን አንድ ቀን ቀደም ብዬ በመሆኑ መጽሓፉ ለሽያጭ የወጣበት የመጀመሪያው ቀን ላይ የደረስኩ ይመስለኛል፡፡ ወዲያው አነሣሁት አገላበጥኩት፤ በጀርባው ሽፋን ላይ የጸሐፊውን "ፊደል ዘለቅነት" ስመለከትማ ምን እንደሚል ለማየት ጉጉቴ ጨመረ፡፡ ለመጽሓፉ የተጠየኩትን ዋጋ ሳላቅማማ ከፍዬ የሄድኩበትን ጉዳይ ሳላከናውን ወደ ድንኳኔ ለመመለስ ታክሲ ውስጥ ገባሁ፡፡ አላስቻለኝም እዛው ንባቤን ጀመርኩ፡፡
የመጽሓፉን ርእስ በማኅበራዊ ሚዲያዎች ባየሁበት ወቅት አግራሞትን ፈጥሮብኛል፤ አበው "ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም" እንደሚሉት ጉድ እየሰማሁ እንዳለሁ ነበር የተሰማኝ፡፡ "በእርግጥ ሙስሊም ጠልነት ኢትዮጵያ ውስጥ አለን?" ብዬ ነበር ራሴን የጠየኩት፡፡ በእኔ ዕውቀት ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ ሙስሊምና ክርስቲያን አንድም በዝምድና፣ እልፍ ሲል ነፍስ ለነፍስ የተጋመደ ጓደኛማችነት፣ ሥራ፣ አገራዊ መልካም እሴቶች ያስተሳሰሩት ሕዝብ ነው፡፡ ለዚህ እንደ ምሳሌ ስለራሴ ብናገር ቅድመ አያቴ አባባ አሊ ይባላሉ፡፡ እንዴት ቢሆን በየትኛው አንጀቴ እኒህን የመገኛዬን ሥር ልጠላ እችላለሁ? እንደኔ ክርስቲያን ያልሆኑትን የእርሳቸውን ልጆችና የልጅ ልጆች እንዴት ቢሆን መጥላት ይቻለኛል? ከወንድም የሚጠጋጋኝን ውድ ጓደኛዬን ሐሰንን በየትኛው ልቤ ልጠላው እችላለሁ? የአባቴ የልብ ጓደኛ የሆኑትን አባባ ኢብራሒምን ከአብራካቸው እንደተከፈለ ልጃቸው ያሳደጉኝን እንዴት ልጠላ እችላለሁ? ባደኩበት አካባቢ ቤተ ክርስቲያን ሲገነባ ሙስሊሙም ሲያዋጣ፣ መስጊድ ሲታደስና አዲስ ሲገነባ፤ ክርስቲያኑ አብሮ ሲያዋጣ ነው እያየሁ ያደኩት፤ የምነግራችሁ በመጽሐፉ እንደ ምሳሌ ስለተጠቀሰው ስለ ወሎ ሳይሆን፤ ስለ ጎንደር ነው፡፡ ይህ ነው ጉድ ሳይሰማ ያሰኘኝ፤ ለእኔ ጉድ ነውና፡፡ ለነገሩ ጊዜው ብዙ ጉዶች የምንሰማበት ሆኖ ካረፈው ቆየት አለ አይደል?
በእነዚህ ሐሳቦች ተጠፍንጌ ተይዤ ማንበብ ጀመርኩ፤ ምስጋናውን አንብቤ ወደ ማስታዎሻነቱ አለፍኩ፤ በዚህ ወቅት የመጽሐፉ ይዘት ምን ሊሆን እንደሚችል የጸሓፊውንም ስነ ልቡና መገመት አልከበደኝም፡፡ ሚዛናዊነቱን ተጠራጠርኩት፡፡ የጸሓፊው ፊደል ዘለቅነት (ለጸሓፊው ፊደል ዘለቅ በሚል ለመጥራት የተገደድኩት ከዛ በኋላ ነው፡፡ ምክንያቴም ዕውቀትና ትምህርት የዘለቀ ሰው ይለወጣል ብዬ ስለማምን ነው፤ እውነት ለመናገር ከሆነ ግን በፋኢዝ ለውጥን አላየሁም፡፡) በሃይማኖታዊ ቅንአት የእብለት ዳዋ እንደተዋጠ አመላከተኝ፡፡ መጽሐፉ በዘጠኝ ምዕራፎች እንደተዋቀረ እወቁልኝ የሚለውን ማውጫ አወራርጄ መግቢያውን፣ ምእራፍ አንድ፣ ሁለት እያልኩ ዘለቅሁ፡፡ ግምቴም ትዝብቴም ትክክል ሆኖ አግኝቼዋለሁ፡፡ ፋኢዝን እንድናውቀው፣ በዚህ ርእስ እንድንወያይና ሐሳባችንንም እንድንሰጥ መንገድ ስለሆናችሁን በምስጋናው ሥፍራ የተመሰገናችሁትን ወገኖች በሙሉ እኔም ከመቀመጫዬ ብድግ በማለት ክበሩልኝ ብያለሁ፡፡
የመጽሐፉን መግቢያ ሳነብ እንዲህ የሚል አንብቤ እንደነበር ትዝ ሲለኝ ብዕሬን አነሣሁ፡- "…ዋናው ሐሳቤ ተወያይተን ችግሮቻችንን እንድንፈታ ነውና የጎረበጣችሁን ወይም ያላሳመናችሁን ነገር ብትጠቁሙኝ ለማስተካከል ወይም ለመወያየት ዝግጁ መሆኔን እወቁልኝ፡፡" እናም በዚህ መጽሐፍ የጎረበጠኝንና ያላመንኩበትን እነሆኝ ለማለት ብዕሬን ሰድሬያለሁ፡፡
ወንድማችሁ ሳሂህ ኢማን ነኝ!
ይቀጥላል…