ለምን አልሰለምኩም?
3K subscribers
52 photos
10 videos
42 files
187 links
ይህ ቻነል ቅዱሱ የአምላካችን ቃል በ1ኛ ጴጥ 3:15 ላይ ባዘዘን መሠረት ሙስሊም ወገኖቻችን በክርስትና ላይ ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች እና ትችቶች ምላሽ የምንሰጥበት፣ ጥያቄዎቻቸውን ከነመልሳቸው በየጊዜው እያዘጋጀን የምንለጥፍበት፣ ለምን እንዳልሰለምን ፣ እንደማንሰልምም የምንገልጥበት ፣ የኢስላምን የጨለማ መንገድነት በእውነት ብርሀን የሚገልጡ ፅሁፎችን የምናስነብብበት መድረክ ነው።
Download Telegram
የቁርአን ትንቢት?
ሙሐመድ እውነተኛ ነቢይ አለመሆኑን ከሚያሳዩ ማስረጃዎች መካከል አንዱ ለፍጻሜ የበቃ አንዳችም ትንቢት አለመናገሩ ነው፡፡ ነቢይ ማለት መጻዒ ነገሮችን የመተንበይ ጸጋ ያለው እንደመሆኑ ከፈጣሪ ዘንድ ተልኬያለሁ የሚል ማንኛውንም ሰው በዚህ መስፈርት መመዘን እውነተኛነቱን ለማወቅ ጥሩ መንገድ ነው፡፡ ዳሩ ግን ሙሐመድን በዚህ ሚዛን የመዘንን እንደሆን ውድቅ ሆኖ ስለሚገኝ የመስፈርቱን ወሳኝነት የተገነዘቡ ሙስሊም ሰባኪያን ለነቢይነቱ ማረጋገጫ የሚሆኑ “የተፈጸሙ” ትንቢቶችን ፍለጋ ሲደክሙ ይታያሉ፡፡ በዚህ ጽሑፍ መሰል ጥረቶችን ካደረጉ ሰባኪያን መካከል የአንዱን ሙግት የምንመለከት ይሆናል፡፡
1. ፍሬዎች ፆታ አላቸውን?
በቁርአን ውስጥ ሙሐመድ ፍሬዎች ሁሉ ጥንድ ሆነው እንደተፈጠሩ ተናግሯል፡፡ ሙስሊሙ ሰባኪ የትንቢት ፍጻሜ በማስመሰል የጠቀሰው ጥቅስ እንዲህ ይነበባል፡-
“እርሱም ያ ምድርን የዘረጋ በእሷም ተራራዎችን እና ወንዞችን ያደረገ በውስጧም ከፍሬዎች ሁሉ ሁለት ሁለት ጥንዶችን ያደረገ ነው፡፡ ሌሊትን በቀን ይሸፍናል፡፡ በዚህም ውስጥ ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች ታምራቶች አሉ፡፡” (ሱራ 13፡3)
ሙስሊሙ ሰባኪ ይህ ጥቅስ “ትንቢታዊ” መሆኑን ሊያስረዳን የሚሞክረው እንዲህ በማለት ነው፡-
36፥36 ያ ምድር ከምታበቅለው፣ ከራሶቻቸውም፣ *ከማያውቁትም ነገር ጥንዶችን ሁሏንም የፈጠረ ጥራት ይገባው*፡፡

"ከማያውቁትም ነገር ጥንዶችን" ማለት በቁርኣን መውረድ ጊዜ የዕጽዋት ጥንድነት ዐለመታወቁን ያሳያል። አምላካችን አላህ ጊዜው ሲደርስ በ 19ኛው ክፍለ ዘመን ላይ ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች ታምራት ይሆን ዘንድ ዕፅዋት ጾታ እንዳላቸው ዐሳውቆናል። “ጋይኒ” γυνή ማለት “ሴቴ” ማለት ሲሆን ይህቺ የዕፅዋት እንቁላል ህዋስ”gynoecious” በሥነ-ሕይወት ጥናት “ካርፔልስ”carpels” ትባላለች፥ “አንድሮ” ἀνήρ ማለት “ወንዴ” ማለት ሲሆን የዕፅዋት የዘር ህዋስ”Androecium” በሥነ-ሕይወት ጥናት “ስቴመንስ”stamens” ይባላል። ቁርኣን ከያዛቸው መካከል “አል-ገይቡል ሙሥተቅበል” ٱلْغَيْب ٱلْمُسْتَقْبَل ማለትም “መጻእያት የሩቅ ወሬ” ነው፥ ይህንን ትንቢት ከጊዜ በኋላ በእርግጥ ታውቁታላችሁ ባለን መሠረት ዛሬ በዘመናችን ዐውቀነዋል፦
38፥88 *«ትንቢቱንም ከጊዜ በኋላ በእርግጥ ታውቁታላችሁ፡፡

የሙግቱን ስሁትነት ከማስረዳታችን በፊት የዚህን ሰው አንድ ስህተት በመጠቆም እንጀምር፡፡ ይህ ሰው ራሱን ምሑር ለማስመሰል ብዙ ጊዜ የግሪክ ቃላትን ሲጠቅስ ይታያል፡፡ ይህንንም የሚያደርገው ቋንቋውን በማወቅ ሳይሆን ለጽሑፉ ክብደት በመጨመር “ምሑር” ለመሰኘት ነው፡፡ አስቂኝ የሆነው ጉዳይ ግን እንኳንስ ቋንቋውን ሊያውቅ ይቅርና ፊደላቱን እንኳ ለይቶ አለማወቁ ነው፡፡ ለዚህም ነው γυνή (ጉኔ) የሚለውን “ጋይኒ”ἀνήρ (አኔር) የሚለውን “አንድሮ” ብሎ ያነበበው፡፡ በረባው ባልረባው የማያውቁትን ቋንቋ እየጠቀሱ ከመዘላበድ ቢቀርስ? አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ደግሞ የሚያውቁትን ሰዎች መጠየቅ፤ መጻሕፍትን ማመሳከር፤ ዕድል ከተገኘ ቋንቋውን መማር ይቻላል፡፡ በማያውቁት ገብቶ ምሑር ለመምሰል አጉል መወጣጠር ትርፉ ቅሌት ነው፡፡
ወደ ዋናው ጉዳይ ስንገባ ይህንን የቁርአን ጥቅስ “የተፈጸመ ትንቢት” በማስመሰል ማቅረብ ከጅምሩ ህተት ነው፡፡ ጥቅሱ የሙሐመድን ነቢይነት የሚያረጋግጥ ሳይሆን ተቃራኒውን የሚያረጋግጥ ነው፡፡ ስህተቱን በሦስት ከፍለን እንመልከት፡-
1. ወንዴና ሴቴ ዕፅዋት ወይንም የዕፅዋት አበቦች እንጂ ፆታ ያለው ፍሬ የለም፡፡ እንደዚህ የሚል ነገር በየትኛውም የሳይንስ መጽሐፍ ውስጥ አይገኝም፡፡ ቁርአን “ፍሬ” ሲል አጠቃላዩን ተክል ለማመልከት ነው ብለን ካላጠጋጋን በስተቀር ወንዴና ሴቴ የሚባል የፍሬ ዓይነት የለም፡፡ ይህ የመጀመርያው ስህተት ነው፡፡
2. በቁጥር አንድ ላይ የተጠቀሰውን ስህተት ችላ ብለን በዕፅዋት ደረጃ እናስብ ከተባለ ወንዴና ሴቴ የሆኑ ዕፅዋት በቁጥር አነስተኛ ሲሆኑ አብዛኞቹ ዕፅዋት በአበቦቻቸው ውስጥ ወንዴም ሴቴም ያላቸውና ሌሎች ደግሞ ያለ ፆታ መራባት የሚችሉ ናቸው፡፡ የቁርአን ጸሐፊ ግን ሁሉም ፍሬዎች ጥንድ ሆነው እንደተፈጠሩ ይነግረናል፡፡ ሙስሊሙ ሰባኪ ለዚህ ምላሽ ይሆንልኛል በማለት ተከታዩን ሐሳብ አቅርቧል፡-
ኩል” كُلٌّ ማለትም “ሁሉ” የሚለው ቃል ፍጹማዊ “Absolute” ሆኖ ሲመጣ “ሙጥለቅ” مُطْلَق ሲባል፥ በአንጻራዊ “Relative” ሆኖ ሲመጣ ደግሞ “ቀሪብ” قَرِيب‎ ይባላል፥ እዚህ አንቀጽ ላይ "ኩል" ቀሪብ ሆኖ የምናውቀው "ሁሉ" በሚለው ገላጭ ቅጽል መነሻ ላይ "ሚን" مِن ማለትም "ከ" የሚል መስተዋድድ መኖሩ ነው። "ከ"ፍሬዎች ሁሉ" ማለት እና "ፍሬዎች ሁሉ" ማለት ሁለት ለየቅል ትርጉም አላቸው፥ ከፍራፍሬዎች መካከል ጥንድ ያልሆኑ በከፊል መኖራቸው ይህንኑ ያሳያል።
ሙስሊሙ ሰባኪ “ሁሉ” የሚለው ቃል ትርጉሙ ምን እንደሆነ የሚያውቅ አይመስልም፡፡ "ከፍሬዎች ሁሉ" ማለት “ፍሬ ከተባለ ነገር ሁሉ” ማለት እንጂ “የተወሰኑ ፍሬዎች” ማለት አይደለም፡፡ “ሁሉ” የሚል ጠቅላይ ቃል እስከገባ ድረስ “ከ” የሚል መስተዋድድ በዚህ አውድ ለውጥ አያመጣም፡፡ “ከፍሬዎች ሁሉ” ማለት “ከሁሉም ፍሬዎች” ማለት ነው፡፡ ሰባኪው ከተናገረው በተጻራሪ የተለያዩ የእንግሊዘኛ ትርጉሞችን ስንመለከት ሁሉም ፍሬዎች ጥንድ ተደርገው እንደተፈጠሩ በሚያመለክት መንገድ ተርጉመውታል፡፡
and fruit of every kind He made in pairs, two and two (Yusuf Ali)
and of all fruits He placed therein two spouses (male and female). (Pickthall)
and of fruits of every kind HE made therein two sexes. (Sher Ali)
And from the different kinds of fruits, He made them into pairs - males and females. (Rashad Khalifa)
and from all of the fruits He made therein two mates; (Saheeh International)
and created thereon two sexes of every [kind of] plant; (Muhammad Asad)

ከላይ የተጠቀሱት ትርጉሞች ሁሉ እንደሚያመለክቱት የቁርአን ደራሲ ከፍሬዎች መካከል ስለተወሰኑት ሳይሆን ስለ ፍሬዎች ሁሉ እየተናገረ ነው፡፡ ቀደም ሲል እንዳልነው ፆታ ያለው ፍሬ አለመኖሩ እንደተጠበቀ ሆኖ “ፍሬ” ሲል አጠቃላዩን ተክል ለማመልከት የገባ ነው ቢባል እንኳ ሁሉም ተከሎች ጥንድ ፆታ ያላቸው ባለመሆናቸው ጥቅሱ ስህተት ነው፡፡
3. ሙስሊሙ ሰባኪ ጥንድ ዕፅዋት መኖራቸው በሙሐመድ ዘመን የማይታወቅ በማስመሰል ቢናገርም ሃቁ እንደርሱ አይደለም፡፡ እውነት ነው በጽሑፍ በሰፈሩት መረጃዎች መሠረት ዕፅዋት ፆታ እንዳላቸው የታወቀው በቅርብ ጊዜ ነው፡፡ ነገር ግን እንደ ቴምርና ፓፓያ ያሉ ዕፅዋት ጥንድ ተደርገው ካልተተከሉ በስተቀር ምርት አለመስጠታቸው ከጥንትም ያለ የተፈጥሮ እውነታ በመሆኑ ምናልባት በሙሐመድ ዘመን የነበሩ ሰዎች ሚስጥሩን አያውቁት ይሆናል እንጂ ጥንድ መሆናቸውን አለማወቅ የሚችሉበት ምንም ዓይነት ተዓምር የለም፡፡ ሙሐመድ በአረብያ በብዛት የሚመረተውን ቴምር በመመልከት ዕፅዋት ሁሉ ተመሳሳይ ተፈጥሯዊ ባሕርይ እንዳላቸው በመደምደም ይህንንም ስህተት የአምላክ መገለጥ በማስመሰል በመናገር ሐሰተኝነቱን ግልፅ አድርጓል፡፡ ሙስሊም ሰባኪያን ግን
😁31
“ምንተስኖት” በሆነው ምላሳቸው ሃቁን በማጣመም እውነትን ሐሰት ሐሰትን ደግሞ እውነት ለማድረግ ይፍጨረጨራሉ፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ማስተዋልን ይስጣቸው፡፡ አሜን፡፡
ይቀጥላል...
Audio
የዶ/ር ሊኮናን አስተያየት በተመለከተ ለየህያ መልስ
የዶ.ር ሊኮናን አስተያየት በተመለከተ ለየህያ መልስ - ዙር 2
ዳንኤል
የዶ.ር ሊኮናን አስተያየት በተመለከተ ለየህያ መልስ - ዙር 2
Audio
የ ዶ/ር ተስፋዬ ሮበሌን ትምህርት በተመለከተ ወሒድ ለተናገራቸው ብዙ ስህተቶች የተሰጠ መልስ

ክፍል 1

-በ Ναολ Τζιγι
@Jesuscrucified
መጥተናል! መጥተናል!

ሙስሊም-ጠልነት በኢትዮጵያ አለን? ካለስ ለምን ክፍል 5
“ከአል-ነጃሺ” ታሪክ በስተጀርባ የሚገኝ የአክራሪዎች ሤራ
http://www.ewnetlehulu.org/am/terrorism/najashi/
-----------
ሊንኩን ተከትለው ያንብቡ፤ ለሌሎችም ያካፍሉ።
Audio
የዶ/ር ተስፋዬ ሮበሌን ትምህርት በተመለከተ ወሒድ ለተናገራቸው ስህተቶች የተሰጠ መልስ

ክፍል 2

- Ναολ Τζιγι
@Jesuscrucified
ጀነት የሚገቡት እነማን ናቸው? ለሚለው የወሂድ ኡመር ቡጭርጭር የተሰጠ ምላሽ

መስከረም 10/2019 ላይ ረምላ ከወሂድ የተቀዳውን እንድናነብ እንደለቀቀችልን የሚታወስ ነው፡፡ እኔም ጊዜ ሳገኝ እንደምመለስበት ቃል ገብቼ ነበር፡፡ እነሆ በቃሌ ከተፍ ብያለሁ፡፡

በመጣጥፉ የተለመዱት የቁርአን አንቀጾች የተንሸዋረረና የቁርአንን ሥነ አፈታት ሥርዐት ባልጠበቀ ሁኔታ ተጠቃቅሰዋል፡፡ እያንዳንዱ የተጠቀሱ አንቀጾች ደግሞ በማጨብጨብ እንጂ መመርመርና መጠየቅ የማይወዱትን ዕውቀት አጠር ሙስሊሞችን ቢያታልል እንጂ እኛ መንደር ማንኳኳት እንኳን አይችልም፡፡ ሁሉም የተጠቀሱ የቁርአን አንቀጾች ቁርአን መለኮታዊ መጽሐፍ ያለመሆኑ ማሳያዎች መሆናቸውን ወሂድ የገባው አልመሰለኝም፡፡ ለማንኛውም እርሱን በሌላ ጊዜ መመለስ ይቻላል፡፡ አሁን ወደ ጀነት ገቢዎቹ ስመለስ መጣጥፉን እያነበብኩ ከት ብዬ መሳቄ አልቀረም፡፡ ወዲያውም "ድሀ በሕልሙ ቅቤ ባይጠጣ ምን ይውጠው ነበር?" የሚለው የአበው ብሂልም ትዝ አለኝ፡፡ ስለ ክርስቲያኖችና ስለ አይሁዶች የገነት መሆንና አለመሆን የቁርአን ምስክርነት አያስፈልገንም፤ እንደማያስፈልገንም ራሱ ወሂድ ጠንቅቆ ያውቀዋል፡፡ ይሁንና እንዳልከው ጀነት የሚገቡት ሙስሊሞች ከሆኑና በዚህ እርግጠኝነት ከተሰማህ ብዙ መጠየቅ ቢቻልም ለእነዚህ ጥያቄዎቼ መልስ ሊኖርህ ግድ ነው፡፡ እያልኩ ያለሁት አሁን ለማነሣቸው ጥያቄዎች መልስ ካለህ አሁኑኑ ዘርገፍገፍ አድርጋቸው፡፡ ጥያቄዎቼ እነሆ፡-

1. ሙስሊሞች ጀነት የሚገቡ ከሆነ ነቢዩ ሙሐመድ ጀነት ስለመግባታቸው አላህም ሆነ ራሳቸው ለምን እርግጠኛ መሆን ተሳናቸው? ነቢዩ ሙስሊም አልነበሩምን?
2.
ሱረቱል አል-አህቃፍ 46 ፡ 9
…. በእኔም በእናንተም ምን እንደሚሥሠራም አላውቅም፡፡ … በላቸው፡፡

የዚህ አንቀጽ አስባብና ማብራሪያ አሉ ኢማም ኢብን ከሲር ሳሂህ አል-ቡኻሪ ላይ እንዲህ በማለት ነቢዩ ተናግረው የሰፈረው ሐዲሳቸው ነው፡-

"…. Allah's Apostle said, 'As for him, by Allah, death has come to him. By Allah, I wish him all good (from Allah). By Allah, in spite of the fact that I am Allah's Apostle, I do not know what Allah will do to me.", Um Al−`Ala added, "By Allah, I will never attest the righteousness of anybody after that." (Bukhari Volume 9, Bk. 83: Blood Money (Ad−Diyat), # 131)
3. ሙስሊሞች ጀነት መግባታቸው እርግጥ ከሆነ ጀነት ቃል የተገባላቸው የነቢዩ ባልደረቦች ጀነትን ሲያስቡ የሰው ዐይነ ምድር እና የግመል ፋንድያ መሆንን ለምን ሊመኙ ቻሉ? ያን ሁሉ የተስፋ ክምር ምን በላባቸውና እንዲህ የወረደ ነገር አስመኛቸው ትላለህ?

"Al-Bayhaqi narrated in Shucab al-Iman that ad-Dahhak said: Abu Bakr said, ‘By Allah, I wish that I were a tree by the side of the road by which a camel passed, and it took me into its mouth, chewed me, swallowed me, passed me out as dung, and that I were not a man.’ Umar said, ‘Would that I were my family’s ram, which they were fattening as much as seemed right to them, until when I became as fat as could be, some people whom they love visit them, and they sacrifice me for them, make some of me into roasted meat, some of me into sun-dried meat, then eat me, and that I were not a human being.’" (Jalal ad din as suyuti, Histrory of Khalifahs, page 149-150)

4. ሱራ 2 ፡ 62 ሙስሊሞች ጀነት ስለመግባታቸው የሚያረጋግጥ የአላህ ቃል ከሆነ ለምን ታዲያ ሙስሊሙ ሁሉ እንድም ሳይቀር ጀሃነም እንደምትገቡ የራሱን ቃል ተቃርኖ አላህ አዋጅ አወጣባችሁ? ነው ወይስ ቀድሞ ምን እንዳለ እረስቶ ነው? እርስ በእርሱ የሚቃረን ከሆነ እንዴት እንደ አምላክ ቃል ሊታመን ይችላል?

ሱራ 19 ፡ 71
ከእናንተም ወደ እርሷ ወራጅ እንጂ አንድም የለም፡፡ (መውረዱም) ጌታህ የፈረደው ግዴታ ነው፡፡

መቼም ከኢብን አባስ የእኔ ትርጉም ይበልጣል እንደማትለኝ ተስፋ በማድረግ የሰጠውን ማብራሪያ እነሆ ብያለሁ፡-

(There is not one of you but shall approach it) there is not a single one of you, to the exclusion of prophets and messengers, save that he will enter it, i.e. hell. (That is a fixed ordinance of your Lord) it is a decree that must necessarily take place.

ሙግት እንደማይታክትህ ስለማውቅ ለአንቀጽ 72 ከወዲሁ ገደብ ላስቀምጥ፡-

"In a ḥadīth, the Prophet declares that none of those present with the Muslims at the Battle of Badr (2/624) and Ḥudybiyah (6/628) will enter the Fire. The Prophet’s wife Ḥafṣah then asked him about v. 71, indicating all would approach the Fire, and he responded by continuing to recite v. 72, which states that God shall save those who are reverent." (Seyyed Hossein Nasr, The study Quran A new translation and commentary)

በሁለቱ ጦርነቶች የተሳተፉት ተዋጊዎች ቁጥር ከፍተኛው 1950 ብቻ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ማለት እናንተ ከተስፋው ውጭ ናችሁ ማለት ነው፡፡ የሚገርመው ይህ ተስፋ በእጃቸው አለ የሚባልላቸው እንኳን ተስፋውን ማመን ተስኗቸው ፋንድያ መሆንን ተመኝተዋል ፡፡ ታዲያ አንተ ሙስሊሞች ጀነት ይገባሉ ያልከው ከየት አምጥተህ ነው?

5. አንተ (ወሂድ) ትንታኔ ለሰጠህበት ሱራ 2 ፡ 62 Dr. Muhammad Taqi-ud-Din Al-Hilali, Ph.D. & Dr. Muhammad Muhsin Khan በሠጡት ማብራሪያ እንዲህ ብለዋል፡-
@Jesuscrucified
1
(V.2:62) This Verse (and Verse 5:69), mentioned in the Qur:an should not be misinterpreted by the reader as mentioned by lbn Abbb (Tafsir AtTabar,) that the provision of this Verse was abrogated by the Verse 3:85: "And whosoever seeks a religion other than Islam, it will never be accepted of him, and in the Hereafter, he will, be one of the losers." (i.e. after the coming of Prophet Muhammad on the earth, no other religion except Islam, will be accepted from anyone). (The Noble Quran has been translated into the modern English Language by Dr. Muhammad Taqi-ud-Din Al-Hilali, Ph.D. & Dr. Muhammad Muhsin Khan)

እንዲህ ከሆነና አንቀጹ የተሻረ ከሆነ አንተ ራስህን ሊቅ ለማስመሰል ቁርአን ላይ ሸፍጥ ሠርተሀል ማለት ነው፡፡ የአንቀጹ መልእክት በቀጥታ በአንቀጹ የተጠቀሱት ሦስቱ ወገኖች ጀነት ይገባሉ የሚል እንጂ አንተ እንዳልከው አይደለም፡፡ ራስህን ከእነዚህ ሊቃውንት ጋር እንዴት ልታስታርቅ ትችላለህ? ማን ይታመን? መቼም እነዚህን የኢስላም ሊቃውንት እንደ ያሕያ ኢብኑ ኑሕ ከኦሬንታሊስቶች ቀድተው ነው አትላቸውም አይደል?

መቼም ይኼ ቁርአን ሊሟገቱለት ደፋ ቀና የሚሉትን ከማዋረድ አይመለስም፡፡ ተሟግተውለት አያድኑት፡፡ አንዱን ደፈንን ሲሉ በሌላው ይበጠረቃል፡፡ ተመልከት እነዚህም ሰዎች እንዳንተው ሌላ የችግር አጣብቂኝ ውስጥ ሲወድቁ፡፡ እንደ ቁርአን የሻሪ ተሻሪ ደንብ (ትክክል ባይሆንም) መሠረት ሱራ 2 ፡ 62 በሱራ 3 ፡ 85 ሊሻር ይችላል፡፡ ምክንያቱም ሰራ 2 ፡ 62 በመዲና 87ኛ ደረጃ የወረደ ሲሆን ሱራ 3 ፡ 85 ደግሞ በኋላ በመዲና 89ኛ ደረጃ የወረደ ሱራ ነው፡፡ ሱራ 5 ፡ 69 ን ግን የመሻር ሥልጣን ሊኖረው ከቶውን አይችልም፤ ሱራው 111ኛ ወይም 114ኛ ደረጃ በመዲና የወረደ የመጨረሻው ሱራ ነውና፡፡ ለዚህም አይሻ እንዲህ ስትል እንደተናገረች ኢማም ኢብን ካሲር ዘግበዋል፡-

"Al-Hakim narrated that Jubayr bin Nufayr said, "I performed Hajj once and visited A'ishah and she said to me, O Jubayr! Do you read (or memorize) Al-Ma'idah ' I answered Yes.' She said, It was the last Surah to be revealed. Therefore, whatever permissible matters you find in it, then consider (treat) them permissible. And whatever impermissible matters you find in it, then consider (treat) them impermissible.'''

ታዲያ ከየት መጥቶ ሙስሊሞች ጀነት ሊገቡ ይችላሉ?

6. ብዙ ማለቱን ልተወዉና "መልካም የሠራ" ስላልከው የተወሰነ ልበልና ላቁም፡፡ ለዚህ እንደምንጭ ነቢዩ ሙሐመድን ልጠቀም፡፡ ከቁርአን መጥቀስ የማልችል መስሎ እንዳይሰማህ፤ የትየለሌ አንቀጽ ከነማብራሪያው ማቅረብ እችላለሁ፡፡ አንተም ታውቃለህ፡-

Narrated Abu Huraira: Allah's Apostle said, "The deeds of anyone of you will not save you (from the (Hell) Fire)." They said, "Even you (will not be saved by your deeds), O Allah's Apostle?" He said, "No, even I (will not be saved) unless and until Allah bestows His Mercy on me. Therefore, do good deeds properly, sincerely and moderately, and worship Allah in the forenoon and in the afternoon and during a part of the night, and always adopt a middle, moderate, regular course whereby you will reach your target (Paradise). (Bukhari Bk 76: To make the Heart Tender (Ar−Riqaq), # 470)

ስለዚህ መልካም ሥራም ለሙስሊም ዋጋ የለውም፡፡ በምን ሒሳብ ጀነት የሙስሊም ልትሆን ትችላለች? ጀነት ለሙስሊም "ላም አለኝ በሰማይ" ነው ወዳጄ፡፡ ገሃነም አፏን ከፍታ መሄድክን እየተጠባበቀች ነው፡፡

ክርስቲያን መንግስተ ሠማይ ስለመግባቱ ግን ያኔ ተስፋ ታደርግቸው ከነበሩት ጣፋጭና እርግጠኛነትን በልብ ከሚያትሙት ከአምላካችን ከእግዚአብሔር ቅዱስ ቃል ውስጥ ሁለቱን ልጥቀስልህ፡፡ አንድን ክርስቲያን እርግጠኛ የሚያደርጉት ተስፋዎች የትየለሌ መሆናቸውን አንተም ታውቀው ነበር፤ ምን ያደርጋል፡፡ ለማንኛውም የአምላካችን ቅዱስ ቃል እንዲህ ይላል፡-

ዮሐ 3 ፡ 16-18
በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና። ዓለም በልጁ እንዲድን ነው እንጂ፥ በዓለም እንዲፈርድ እግዚአብሔር ወደ ዓለም አልላከውምና። በእርሱ በሚያምን አይፈረድበትም፤ በማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ አሁን ተፈርዶበታል።

1ኛ ዮሐ 5 ፡ 12-13
ልጁ ያለው ሕይወት አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም። የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ ታውቁ ዘንድ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ለምታምኑ ይህን ጽፌላችኋለሁ።
ውድ ሙስሊም ወንድሞቼና እህቶቼ ሆይ ለንስሀ የተሰጣችሁ ጊዜ ድንገት ሊያልቅ እንደሚችል ለእናንተ መንገር አስፈላጊዬ አይደለም፡፡ ታዲያ አፏን ከፍታ ከምትጠባበቃችሁ ገሃነም ማምለጥ የምትችሉት በጌታችንና በመድኀኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ብቻ ነው፡፡ ሌላ ማምለጫ ፈጽሞ የለም፡፡ ስለዚህ ኑና ፈጥናችሁ ለእርሱ እጃችሁን በመስጠት አብረን ለዘለአለም በደስታ ከእርሱ ጋር የምንኖርበትን ዋስትና ተቀበሉ፡፡ ያለ ሽንገላ እወዳችኋለሁ!

ወንድማችሁ
ሳሂህ ኢማን!
@Jesuscrucified
የወዳጄ የአህመድ ጥያቄ.pdf
358.2 KB
የሰሞኑ የሙስሊም ሰባኪያን የአተካሮ ርዕስ የዳንኤል ክብረት ንግግር ሆኗል፡፡ ጥቂት አስተያየቶች አሉኝ፡-

1. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓትሪያሪክ “አሕመድ አል-ነጋሺ የሚባል ንጉሥ በኢትዮጵያ አልነበረም” በሚል ርዕስ ኦፊሴላዊ በሆነ መንገድ ሁለት ቡክሌቶችን አሳትሞ ሳለ እንደ ተኩላ መንጋ በአንድ ግለሰብ ላይ አተኩሮ አምባጓሮ መፍጠር የጤና አይደለም፡፡ ከቻላችሁ ቤተክርስቲያኒቱ ኦፊሴላዊ በሆነ መንገድ ጉዳዩን በአደባባይ እንደተቃወመችው ሁሉ እናንተም በመጅሊሳችሁ አማካይነት ኦፊሴላዊ በሆነ መንገድ ምላሽ መስጠት እንጂ አንድን ግለሰብ ነጥሎ አገር ይያዝልኝ ማለትና ማስፈራራት የፈሪ ተግባር ነው፡፡

2. የሰለመ የአክሱም ንጉሥ ስለመኖሩ ፍንጭ ሊሰጥ የሚችል ምንም ዓይነት የጽሑፍም ሆነ የአርኪዎሎጂ ማስረጃ በሌለበት ሁኔታ ከክስተቱ ከክፍለ ዘመናት በኋላ የተፈበረኩ አፈ ታሪኮቻችሁን ጠቅሳችሁ የምታቀርቡት ሙግት ማንንም አያሳምንም፡፡ በነዚህ መጻሕፍታችሁ ውስጥ የተጻፈው ትርክት አሳማኝ እንዳልሆነና ምንም ዓይነት ውጪያዊ ማስረጃ እንደሌለው እየነገርናችሁ ባለንበት ሁኔታ እነዚያውኑ መጻሕፍት እየጠቀሳችሁ የምትከራከሩ ከሆነ ሙግታችሁ ውኀ ቅዳ ውኀ መልስ ነው፡፡

3. ከስደተኞቹ ጋር ወደ አክሱም የመጣው የሙሐመድ የአክስቱ ልጅና የሚስቱ ወንድም የነበረው ኡቤይዱላህ ኢብን ጃሽ እስልምና ሐሰት መሆኑን ተረድቶ ክርስትናን እንደተቀበለ የገዛ መጻሕፍታችሁ በሚመሰክሩበት ሁኔታ ንጉሡ ሰልሟል የሚለው ትርክት አሳማኝ አይደለም፡፡ በገዛ መጻሕፍታችሁ መሠረት ሙስሊም ስደተኞቹ ንጉሡ ፊት በቀረቡበት ወቅት ከክርስትና ጋር የሚስማሙ እስላማዊ አስተምህሮዎችን ብቻ በመናገር ራሳቸውን ክርስቲያን ሲያስመስሉ እንጂ ከክርስትና አስተምህሮዎች ጋር የሚጋጩ እስላማዊ አስተምህሮዎችን ሲናገሩ አልታዩም፡፡ ታድያ በእንዲህ ዓይነት ሁኔታ ንጉሡ እምነቱን ለውጧል እንዴት ሊባል ይችላል?

4. የአክሱም ነገሥታት ስም ዝርዝርና የነገሡባቸው ዘመናት በትክክል የሚታወቅ ሆኖ ሳለ በተረታ ተረት መጻሕፍታችሁ ውስጥ ከዘመኑ ጋር የማይገጥም ንጉሥ ስም ተጠቅሶ መገኘቱ ለትርክቱ ሐሰተኛነት ሌላው ማረጋገጫ ነው፡፡ የእስልምና እምነት ተከታዮች ወደ ኢትዮጵያ እንደመጡ የሚነገረው በ615 ዓ.ም. አካባቢ ሲሆን በወቅቱ በሥልጣን ላይ የነበረው ንጉሥ አካለ ውድም (615-623) እንደነበር ተመልክቷል፡፡ በመጻሕፍታችሁ መሠረት በወቅቱ የአክሱም ንጉሥ የነበረው አርማሕ እለጸሐም እንደሆነ ቢነገርም ቀዳማዊ አርማሕ ቅድመ እስልምና በ442-456 ዓ.ም. የነገሠና ዳግማዊ አርማሕ ደግሞ ድህረ እስልምና በ817-822 ዓ.ም. የነገሠ በመሆኑ ትክክል ሊሆን አይችልም፡፡ እንዲህ ያለ የታሪክ ተፋልፎ ያለበትን ትርክት በጭፍን የሚቀበል የለም፡፡

5. ከዚህ ቀደም የአገራችን ሙስሊሞች ኢትዮጵያ የነቢያቸውን ወዳጆች በመልካም ሁኔታ ያስተናገደች አገር መሆኗን በማመን ይህንን ታሪክ በበጎ መንገድ ይተረጉሙት ስለነበር ተረት መሆኑን ብናውቅም ታግሰነዋል፡፡ አሁን ግን የሰለመውን ንጉሥ ካህናቱና መኳንንቱ አሠቃይተው ገድለውታል የሚል የአክራሪዎች መርዝ ስለታከለበት ተረቱ ከጠቃሚነቱ ይልቅ ጎጂነቱ እየጎላ መጥቷል፡፡ እንዲህ ያለው ትራኬ ለክርስቲያኖችም ሆነ ለሙስሊሞች የማይበጅ በመሆኑ መቃወምና የታሪካችን አካል አለመሆኑን ማጋለጥ አስፈላጊ ነው፡፡ ተረቱ እውነት ነው፣ ያስፈልገኛል የሚል ማንኛውም ሰው ምሑራዊ የሆነ ሙግት አቅርቦ መሟገት እንጂ ግለሰቦችን እየነጠሉ መሳደብ፣ ማስፈራራትም ሆነ የጥላቻን መርዝ መርጨት ተቀባይነት የለውም፡፡
1
የእስላም ሎጂክ
እነዚህ ሰዎች በተዘዋዋሪ እያሉን ያሉት አንድ መስጊድ ብቻውን ከሚፈርስ ሁሉም መስጊዶች አንድ ላይ ይፍረሱ ነው። አይ ማስተዋል ማጣት!
ጠብ ያለሽ በዳቦ - የአክራሪ ሙስሊሞች መሰሪ ስልት
******************
አክራሪ ሙስሊሞች ከሚታወቁባቸው እኩይ አካሄዶች መካከል አንዱ አካባቢያዊ አጀንዳዎችን አገራዊ ብሎም ዓለም አቀፋዊ መልክ እንዲኖራቸው ማድረግ ነው፡፡ በቀላሉ ሊፈቱ የሚችሉ ችግሮችን ሕዝበ ሙስሊሙን ሊያስቆጡ የሚችሉ “ቅመማ ቅመሞችን” በመጨማመርና መርዝ በተነከረ እጃቸው በማማሰል ነገሮችን በማወሳሰብ ስውር አጀንዳቸውን ከግብ ለማድረስ መጠቀምን ያውቁበታል፡፡ ለዚህ የሚሆኑ በርካታ ማሳያዎችን መጥቀስ ይቻላል፡፡

ሰልማን ረሽዲ የተሰኘው እንግሊዛዊ ደራሲ በ 1988 እ.ጎ.አ. “The Satanic Verses” በሚል ርዕስ በጻፈው መጽሐፉ ውስጥ ሙሐመድን የሚተች መልእክት አስፍሯል በሚል አክራሪ ሙስሊሞች ዓለም አቀፍ ተቃውሞ አስነስተው እንደነበር ይታወሳል፡፡ አክራሪዎቹ የሙስሊሞችን ቁጣ ለመቀስቀስ የተጠሙት ዘዴ የረሽዲን ጽሑፍ የሙስሊሞችን ቁጣ ሊቀሰቅስ በሚችል መንገድ ማቅረብ ነበር፡፡ በመጽሐፉ ውስጥ ሙሐመድን ይተቻል የተባለው ክፍል ሙሐመድን በስም የማይጠቅስና ቢጨመቅ ከአንድ ገጽ ያልዘለለ ቢሆንም ሙሉ መጽሐፉ ነቢያቸውን የሚሳደብ በማስመሰል አስወርተዋል፡፡ ረሽዲ አንድ ግለሰብ ቢሆንም መጽሐፉን በእስልምና ላይ የተቃጣ የምዕራባውያን ትንኮሳ በማስመሰል ማቅረብ ሌላው ቁጣን የመቀስቀሻ ዘዴ ነበር፡፡ በወቅቱ ዓለም አቀፋዊ ትኩረትን ሲሻ የነበረው የኢራኑ አያቶላህ ሮሆላህ ኾሜይኒ ረሽዲን በከሃዲነት በመፈረጅ በተገኘበት እንዲገደል ‹‹ፋትዋ›› አውጥቶበት፡፡ “ሃይማኖትህ ተደፈረ” በሚል ቅስቀሳ መላው ሕዝበ ሙስሊም ለተቃውሞ እንዲነሳ ዓለም አቀፍ ጥሪ ከአክራሪዎች ዘንድ በተደጋጋሚ ሲሰማ ነበር፡፡ ጥሪውን ተከትሎ ምድር አንቀጥቅጥ ሰልፎች በመላው አውሮፓና በሙስሊም አገራት ተደረጉ፡፡ በርካታ ሰዎችም ተገደሉ፡፡ ነፍሱን ለማትረፍ ራሱን ለመሰወር የተገደደው ረሽዲም ይቅርታን በመጠየቅ ወደ እስልምና መመለሱን ቢያሳውቅም አክራሪዎች የእርሱን መጽሐፍ እንደ ሰበብ (Pretext) ተጠቀሙት እንጂ መነሻቸውም ግባቸውም እርሱ ባለመሆኑ ውጥረቱ ሊረግብ አልቻለም፡፡ እነሆ ያኔ በምድረ አውሮፓ ላይ ራሱን ቀና ያደረገው አክራሪ እስልምና እስከ አሁን ድረስ እየተንጠራራ የሰዎችን የመናገር መብት በመገደብ አልፎም በሽብር የምዕራቡን ዓለም በመናጥ የሰቆቃ ምንጭ መሆኑን ቀጥሏል፡፡

‹‹ጂላንድ ፖስተን›› የተሰኘው የዴንማርክ ጋዜጣ የሙሐመድን ካርቱን ይዞ በመውጣቱ ሳብያ በተመሳሳይ አክራሪዎች ጉዳዩን ዓለም አቀፍ አጀንዳ አድርገውት ነበር፡፡ በጋዜጣው ላይ የታተመውን ምስል እንዳለ ለሕዝበ ሙስሊሙ በማሳየት ለተቃውሞ መቀስቀስ ብዙም ውጤት እንደማይኖረው የተገነዘቡት አክራሪዎች፤ እናከብረዋለን፣ እንሞትለታለን የሚሉትን ነቢያቸውን እርቃኑን አድርገው ውሻ ከኋላ $%#@*! በመሳል ሕዝበ ሙስሊሙን አስቆጥተው አደባባይ እንዲወጣ አድርገውታል፡፡ በዚያን ጊዜ የተፈጸመው አስነዋሪ ተግባር ፅንፈኞች የሚፈልጉትን ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ግብ እስከመቱ ድረስ ለሃይማኖታቸው ግድ የሌላቸው መሆናቸውን በጥሩ ሁኔታ ያሳየ ነበር፡፡ ብዙ መሰል አጋጣሚዎችን መጥቀስ ይቻላል፡፡

ሰሞኑን በአማራ ክልል ሞጣ ከተማ የተፈጸመውን መስጊዶችን የማቃጠል ተግባር ተከትሎ በአገራችን እየታየ ያለው ሁኔታ ከዚህ የተለየ አይደለም፡፡ በእውነቱ ከሆነ አብያተ ክርስቲያናትም ሆኑ መስጊዶች የአገር ኃብት ናቸው፡፡ የእምነት ተቋማትንና የእምነት መጻሕፍትን ማቃጠልም ሆነ ማንቋሸሽ በከፋ ደረጃ ሊታይ የሚገባው የድንቁርና ተግባር ነው፡፡ እንዲህ ያለ እኩይ ተግባር የሚፈፅሙ ወገኖች በመጨረሻው የውግዘት ቃል ሊወገዙና ለፍርድ ሊቀርቡ ይገባል፡፡ ነገር ግን ከዚህ ቀደም ተመሳሳይ ችግሮች ሲፈጸሙ እንደነበረው ሁሉ በአካባቢው የተፈጸመውን ችግር በፍትህ አካላት፣ በአካባቢው የአገር ሽማግሌዎችና በሃይማኖት አባቶች ርብርብ ርቆ ሳይሄድ መፍታት ሲቻል ጉዳዩን አገር አቀፋዊ በማድረግ የጦርነትና የጭፍጨፋ፣ አንድን ሕዝብ ለይቶ የመሳደብና አገርን የማፍረስ መፈክር ይዞ ለባሰ ጥፋትና የእርስ በርስ እልቂት አደባባይ መውጣት፣ ሰላማዊውንም ሕዝብ ለመሰል ተግባር ማነሳሳት እጅግ አስነዋሪ ተግባር ነው፡፡ በተለይም ደግሞ አገራችን በእንዲህ ዓይነት ጭንቀትና የመፍረስ አደጋ ውስጥ ባለችበት ወቅት የሐሰት ምስሎችንና ቪድዮዎችን ሳይቀር ተጠቅሞ እንዲህ ያለ ቅስቀሳ ማድረግ በግል ጥቅም የመታወርና የግድ የለሽነት ጥግ ነው፡፡ ይህንን ቅስቀሳ እያደረጉና አገራችንን ወደ ጥፋት አዘቅት እየመሩ የሚገኙትን ኡስታዝ አሕመዲን ጀበልንና መሰሎቻቸውን የተወሰኑ የኅሊና ጥያቄዎችን ልንጠይቃቸው እንወዳለን፡-
1. ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአገራችን የተከሰተውን አለመረጋጋት ተስታኮ በእምነት ተቋማት ላይ ውድመት እየደረሰ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በሚሊኒየሙ ዋዜማ በጅማ ዞን በክርስቲያኖች ላይ የተፈጸመውን አሳቃቂ ጭፍጨፋና አብያተ ክርስቲያናትን የማቃጠል ዘመቻ ሳንቆጥር ሁለት ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በርካታ አብያተ ክርስቲያናት ተቃጥለዋል፣ ካህናት፣ መጋቢያንና ምዕመናንም ታርደዋል፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን በጥቂትም በብዙም የተደረጉ የተወሰኑ (በአመዛኙ ፖለቲካዊ መልክ የነበራቸው) ሰልፎች እንደነበሩ ቢታወቅም ሕዝበ ክርስቲያኑ እርስ በርስ፣ ከሙስሊም ወገኖቹና ከመንግሥት ባለ ሥልጣናት ጋር እየተመካከረና እየተናበበ ሁኔታዎችን ለማረጋጋት ዋጋ ከፈለ እንጂ ሰይፍ እያወናጨፈ፣ የጦርነት ሰንደቅ እያውለበለበ፣ አገር የማፍረስና ሕዝቦችን የመጨፍጨፍ መፈክር ይዞ አደባባይ ለመውጣት አንዱ ሌላውን መች ቀሰቀሰ? እርስ በርስ እንጠፋፋ ከተባለ እኮ ከናንተ ይልቅ ሕዝበ ክርስቲያኑ በቂ ምክንያቶች አሉት፡፡ ነገር ግን ሰላም ይሻላል፤ ለሰላም የመጨረሻውን ዋጋ መክፈል ያዋጣል በሚል ታግሷል፡፡ ደግሞም ትክክል ነው፡፡
2. እናንተ የጦርነት ነጋሪት እየደለቃችሁ ሕዝበ ሙስሊሙን ለጠብ እያነሳሳችሁት እንዳላችሁት ሁሉ በክርስቲያኑ ወገን ያሉት መሪዎችም ተመሳሳይ ተግባር ቢፈጽሙ ውጤቱ ምን የሚሆን ይመስላችኋል? ማነው ተጎጂው ማነው ተጠቃሚው? ምናልባት እናንተ ቅጥረኛ አክራሪዎችና ታሪካዊ ጠላቶቻችን ተጠቃሚ ልትሆኑ ትችላላችሁ ነገር ግን ግጥሚያው ስንት ፐርሰንት ለስንትም ቢሆን የዋሁ ሕዝበ ሙስሊምም ሆነ ሕዝበ ክርስቲያኑ ተጎጂ መሆኑ ግልፅ ነው፡፡ በእንዲህ ዓይነት ሁኔታ ተሸናፊ እንጂ አሸናፊ ወገን አይኖርም፡፡ ተግባራችሁ አገር አፍራሽ ሰይጣናዊ ተግባር ነው፡፡
3. እነ አሕመዲን ጀበልና መሰሎቹ ከዚህ ቀደም በታሰራችሁ ጊዜ ብዙ ክርስቲያን ወገኖች ለነፃነታችሁ ሲታገሉ እንደነበር ከመቼው ዘነጋችሁት? በተለይም ኡስታዝ አሕመዲን ክርስትናን የሚያንቋሽሹ በርካታ ጽሑፎችን እንዳዘጋጀህ በሚታወቅበት ሁኔታ ሕዝበ ክርስቲያኑ ቂም አልያዘብህም፡፡ የሰላም ጭንብል ለብሰህ በሚድያ ስትቀርብም በአድናቆት አጨበጨበልህ እንጂ በክፋት አልፈረጀህም፡፡ ታድያ ሰበብ ፈልጎ ሕዝበ ሙስሊሙን በክርስቲያን ወንድሞቹ ላይ ማነሳሳት ከዚህ ቀደም ሳይገባህ ለተቀበለህ ሕዝብ ውለታ መሆኑ ነው? መላው ሕዝበ ክርስቲያን ተባብሮ በጠላትነት ቢፈርጅህ እኮ መግቢያ የለህም፡፡ ክርስቲያን ግን እንዲህ አያደርግም፡፡ ይልቅስ በዚህ አጋጣሚ ጭንብልህ ወልቆ ሊለወጥ የማይችለውን መሰሪ ማንነትህን በገሃድ ስላየ ካንተና ከመሰሎችህ ይጠነቀቃል፡፡ “ሰይፍን የሚያነሱ በሰይፍ ይጠፋሉ” ተብሎ እንደተጻፈ የመዘዝከው ሰይፍህ በቅርቡ አንተኑ እንደሚያጠፋህ ጥርጥር የለውም፡፡
4. ሕዝበ ሙስሊሙ እንዲህ ለመቆጣትና አደባባይ ለመውጣት በቂ ሰበብ አለው እንበል፡፡ ነገር ግን አገራችን ኢትዮጵያ የዘር ግጭት ተበራክቶ በሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ምክንያትም በግብፅና በግብረ አበሮቿ ጥርስ ተነክሶባት አደገኛ አጣብቂኝ ውስጥ ባለችበት ሁኔታ ፅንፍ ይዞ የሃይማኖት ጦርነት ነጋሪት መደለቅ ተገቢ ነውን? ምንስ ትርፍ ልታገኙ?
5. የሕዝበ ሙስሊሙ መብት ታሪካዊ ሊባል በሚችልበት ደረጃ እየተከበረና አንዳንዴም ተገቢ ያልሆኑ ለሌሎች ሃይማኖታት ያልተሰጡ ጥቅሞችን እያገኘ ባለበት ሁኔታ ሰበብ ፈልጎ ከሌላው ሕዝብም ሆነ ከመንግሥት ጋር ወደ ግጭት እንዲገባ ማነሳሳት በግል ፍላጎታችሁ የታወራችሁና ለአገርም ሆነ እንወክለዋለን ለምትሉት ሕዝብ የማታስቡ መሆናችሁን አያሳይምን?
6. እናንተ የምትከተሉት የጽንፈኝነት አካሄድ እንኳንስ አብዛኛው ሕዝብ የክርስትና እምነት ተከታይ በሆነባትና ቁልፍ ዓለም አቀፍ ሚና ባላት በአገራችን ይቅርና በሙስሊም አገራት እንኳ ሊሠራ አልቻለም፡፡ በሊብያ፣ በሶማሊያ፣ በማሊ፣ በኢራቅ፣ በሦርያና በመሳሰሉት አገራት አክራሪ የእስላም ምንግሥት የመመሥረት ጥረት ከሽፎ አገራቱን ለከፋ ችግር ዳርጓል፡፡ በግብፅ የሙስሊም ወንድማማቾች ፓርቲ የተከናነበውን ውርደት አስታውሱ፡፡ ሳዑዲ አረብያም እንደማያዋጣት አውቃ እያለዘበች ነው፡፡ የኢራን ኢስላማዊ መንግሥት እየተንገዳገደ ነው፡፡ አጋጣሚዎችን ጠብቃችሁ ሰበብ እየፈለጋችሁ በሕዝበ ሙስሊሙ መሥዋዕትነት ልታመጡት የምትፈልጉት እስላማዊ መንግሥት ህልም ብቻ መሆኑን እንዴት ማስተዋል ተነሳናችሁ? ፈጽሞ ለማይሳካ ምኞት አገሪቱን ባታውኩ ምን አለበት?

ውድ አንባቢያን፤ ማስተዋል የጎደላቸው ደናቁርት እዚህም እዚያም ቤት እስካሉ ድረስ ለግጭት እንድንጋበዝ ሰበብ የሚሆኑ መሰል ክስተቶች ወደ ፊትም ቢሆን መፈጠራቸው አይቀርም፡፡ እኩይ አጀንዳ ያላቸው አክራሪዎች ከአገር ሽማግሌዎችና ከሃይማኖት አባቶች የማያልፉ እንዲህ ያሉ አካባቢያዊ ጉዳዮችን አገር አቀፋዊና ዓለም አቀፋዊ መልክ በመስጠት የህልም ዓለም ምኞታቸውን ለማሳካት የዋሁን ሕዝብ መማገድ ልማዳቸው ነው፡፡ ዛሬ እንደ ዋዛ የቀሰቀስነውን ግጭት ማብረድ በማንችልበት ደረጃ ላይ ደርሰን ከምንጠፋፋና አገርም ከምትፈርስ የያዝነውን የቁልቁለት መንገድ ትተን የሰላሙንና የቀናውን መንገድ ብንመርጥ ይበጀናል፡፡ ጥግ ይዘው ተቀምጠው ሊማግዱንና እርስ በርስ ሊያጠፋፉን በማሕበራዊ ሚድያ ቅስቀሳ እያደረጉ የሚገኙትን ከትላንት ስህተታቸው መማር ያልቻሉትን አሕመዲን ጀበልን የመሳሰሉትን የአስተሳሰብ ድኩማን መስማት ትርፉ እልቂት ነውና እናስተውል፡፡ ነገረ መለኮታዊ ልዩነቶቻችንን በሰለጠነ መንገድ እንወያይባቸው፣ እንከራከርባቸው፡፡ ግጭት ቀስቃሽ ክስተቶችን ደግሞ ጨዋነትን በተሞላው ኢትዮጵያዊ ባሕላችን እንፍታቸው፣ እናርግባቸው፡፡ በዙርያችን ለሚገኙት አገራት ያልበጀ የአክራሪነት አስተሳሰብ ለኛም አይበጀንምና አንታለል፡፡ የሰላሙ አምላክ ልዑል እግዚአብሔር ማስተዋልን ይስጠን፤ አገራችንን ኢትዮጵያንም ይጠብቅልን፡፡ አሜን፡፡
1
Audio
Merry Christmas to you all!
" በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።"
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የአሕመዲን ጀበል ምልምሎች ጂሃድ እያወጁ ነው። ይህንን ማስረጃ ለሕግ አካላት አድርሱ።
Ergamtoonni Ahmaddiin Jabal jihaada labsaa jiru. Ragaa kana qaamota seeraa biraan gahaa.