ለምን አልሰለምኩም?
3.01K subscribers
52 photos
10 videos
42 files
187 links
ይህ ቻነል ቅዱሱ የአምላካችን ቃል በ1ኛ ጴጥ 3:15 ላይ ባዘዘን መሠረት ሙስሊም ወገኖቻችን በክርስትና ላይ ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች እና ትችቶች ምላሽ የምንሰጥበት፣ ጥያቄዎቻቸውን ከነመልሳቸው በየጊዜው እያዘጋጀን የምንለጥፍበት፣ ለምን እንዳልሰለምን ፣ እንደማንሰልምም የምንገልጥበት ፣ የኢስላምን የጨለማ መንገድነት በእውነት ብርሀን የሚገልጡ ፅሁፎችን የምናስነብብበት መድረክ ነው።
Download Telegram
ግራንቪል ሻርፕ፦የዮሓኒስ ወንጌል 20:28

ሙሓመዳውያን መፅሓፍ ቅዱስ ውስጥ ተፅፎ የክርስቶስን አምላክነት በ ግልፅ የሚያሳዩ ጥቅሶችን ከራሳቸው ሳይሆን ከ ስላሴ ተቃዋሚያን፣ ግን ክርስቲያን ነን ባዮች በሚሰበስቡት የወረደና በ ብዙ ምሁራን የፈረሰ ሙግት ይዞ እንደ አዲስ መቅረባቸውን ቀጥሏል። ዮሓኒስ 20:28 ከ ጥቅሶቹ መካከል አንዱ ነው።


(የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 20)
----------
27፤ ከዚያም በኋላ ቶማስን። ጣትህን ወደዚህ አምጣና እጆቼን እይ፤ እጅህንም አምጣና በጎኔ አግባው፤ ያመንህ እንጂ ያላመንህ አትሁን አለው።

28፤ ቶማስም። #ጌታዬ #አምላኬም ብሎ መለሰለት።

29፤ ኢየሱስም። ስለ አየኸኝ አምነሃል፤ ሳያዩ የሚያምኑ ብፁዓን ናቸው አለው።

ἀπεκρίθη Θωμᾶς καὶ εἶπεν #αὐτῷ#κύριός μου καὶ ὁ #θεός μου.( ho Kyrios mou kai ho Theos mou)

"28 And Thomas answered and said unto #him, The #Lord of me and The #God of me."
(John 20:28)

ከላይ ያነበብነውን ፅሁፍ በ አጭሩ ስንገልፅ
1. ቶማስ እየሱስን ጌታዬ እና #አምላኬ(θεός) ብሎ ጠራው
2. እየሱስም ቶማስ ለሱ የሰጠውን ስም (ጌታና #አምላክ) ተቀበለ፦ (…ስለ አየኸኝ አምነሃል፤ ሳያዩ የሚያምኑ ብፁዓን ናቸው አለው)

3. ስለዚህ እየሱስ #አምላክ ነው ማለት ነው።

ይሁን እንጂ ሙሓመዳውያን ይህንን ክፍል ለማፍረስ አሁንም ልክ ቲቶ 2:13 ላይ እንዳነሱት ግራንቪል ሻርፕ ባስቀመጠው ሕግ ይሟገታሉ።  የሚያሳዝነው ግን የ ግራንቪል ሻርፕ ሕጎችን እንኳን ማወቅ ይቅርና ክፍሉን ራሱ እንደላጠኑ ያሳውቅባቸዋል።

የ ሻርፕ ስድስተኛው ሕግ

የ ግሪክ ቋንቋ ስኮላር ግራንቪል ሻርፕ እራሱ በ 1798 "The"( ὁ) የተሰኘች definite article አጠቃቀም ዙሪያ ላይ ባሳተመው መፅሓፍ ውስጥ ስድስተኛው ሕግ ላይ ቀጥሎ ያለውን ሕግ ፅፏል።

"ሁለት ተመሳሳይ ሙያ (same case) ያላቸው ስሞች
 καὶ (እና) በሚለው መስተፃምር ተያይዞ ግን በ ሁለቱም ስሞች ፊትለፊት 'ὁ' 'The' ከገባ፣ ሁለቱ ስሞች ሁለት የተለያዩ አካላትን ይገልፃሉ።... ነገር ግን ሕጉን የሚገድቡ ቅድመ ሁኔታዎች አሉ።

1. የ አረፍተ ነገሩ አውድ
2. ከ አረፍተ ነገሩ ፊትለፊት ሁለቱም ስሞች ለ አንድ አካል መሆኑን የሚያሳይ ገላጭ ካለ (e.g. pronoun) ሁለቱም ስሞች ለ አንድ አካል( person) መሆኑን ያሳያል።

ምሳሌ፦  ራእይ 1:8

" ያለውና የነበረው የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ። አልፋና ዖሜጋ እኔ ነኝ ይላል።"
"Ἐγώ εἰμι #τὸ Ἄλφα καὶ #τὸ Ὦ,.."
I am #The Alpha and #The Omega

በዚህ ምሳሌ ላይ 'አልፋ' ፊትለፊት እንዲውም ደግሞ 'ኦሜጋ' ፊትለፊት "THE" የሚለው አርቲክል ገብቷል። ነገር ግን ሁለቱም "እየሱስን" ለመግለፅ እንጂ 'አልፋ' እየሱስን ገልፆ 'ኦሜጋ' ደግሞ አብን ለመግለፅ አልገባም። ምክኒያቱም፦
1. Ἐγώ (እኔ፣ I) የሚለው personal/possessive pronoun Nominative ሲሆን ሁለቱ ስሞች (አልፋና ኦሜጋ) አንድን አካል (እየሱስን) እንደሚገልፁ ያሳያል።
2. አውዱም (context) እየሱስ እረሱን፣ማንነቱን ለመግለፅ የተጠቀመበት እንደሆነ ግልፅ ነው።

በተመሳሳይ ሙግት የዮሓኒስ ወንጌል 20:28ን እንመልከት

#αὐτῷ#κύριός μου καὶ ὁ #θεός μου

"28 And Thomas answered and said unto #him, The #Lord of me and The #God of me."

በዚህ ክፍል በ ሁለቱም ስሞች ፊትለፊት  (κύριός(ጌታ) እና (θεός) ) ' Ὁ' "The" ገብታለች። ስለዚህ እውነት ሙስሊሞቹ እንደሚሉት "ጌታ" የሚለው ለ እየሱስ ሲሆን " አምላክ" የሚለው ደግሞ ለ አብ ነውን??

በ እርግጥ ይህንን ሙግት የሚያቀርበው ከንቱ ተቺ፣ወይ የ ሕጉን ቅድመ ሆኔታዎች ባለየ አልፎታል ወይም ሕጉን አላጠናም።

መልሱ 'በ ፍፁም አይደለም' ነው። ግራምቪል እራሱ በ መፅሓፉ ገጽ 14-16 ላይ የዮሓኒስ 20:28ን ሰዋ ሰው ሲያብራራ ሁለቱም ስሞች((κύριός(ጌታ) እና (θεός) ) ለ አንድ person እሱም #ለእየሱስ እንደሆነ ማስረጃ አቅርቧል።

1. αὐτῷ( said unto #him; 'አለው') የሚለው personal/possessive pronoun dative ሲሆን፣ ሁለቱም ስሞች (ጌታ እና አምላክ)የሚገልፁት አንድን person እሱም #እየሱስን እንደሆነ ያሳያል። ልብ በል " dative case(ሙያ)" መሆኑ አረፍተ ነገሩ ላይ ችግር አያመጣም።ምክኒያቱም ሕጉ ተመሳሳይ ሙያ እንዲሆኑ የጠየቀው ለ ስሞቹ( nouns) እንጂ ለ pronoun አይደለም።

2. የ ክፍሉ አውድ የሚነግረን ቶማስ ለ እየሱስ ለራሱ ይህንን ንግግር እያደረሰ ስለሆነ ሁለቱም ስሞች እየሱስን የሚገልፁ ናቸው።

ልብ በሉ፤ ይህ ደካማ ተቺ፣ ሙግቱን ያቀረበው ግራንቪል ሻርፕን ምንጭ (reference) አድርጎ ነው። ግን ሒደን ግራንቪል እራሱ በዚህ ክፍል ላይ (ዮሓኒስ 20:28) የሰጠውን ማብራሪያ ስናነብ " ክፍሉ እየሱስን" "አምላክ" እንደሚል ተብራርቶ እናገኛለን።  ለዛም ነው ይህንን ኡስታዝ ነኝ ባይ "ከንቱ" ያልነው።

ግራንቪል በራሱ እጅ የፃፈውን ከታች በፎቶ አያይዝላቹሓለው። አንብቡት!!

እየሱስ ለዘላለም ጌታ ነው!!

" እንግዲህ። በኃጢአታችሁ ትሞታላችሁ አልኋችሁ፤ እኔ እንደሆንሁ ባታምኑ በኃጢአታችሁ ትሞታላችሁና አላቸው።"
(የዮሐንስ ወንጌል 8:24)

Reference

Remarks on The Uses of the Definitive Article  in the Greek text of Of the New Testament, Granville Sharp; page 14-16
@Jesuscrucified
@Jesuscrucified