ግጥም ብቻ 📘
67.3K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#የግርጣት_ሰላምታ
© ሲራክ ወንድሙ @siraaq
.
ለደባ እሩቅ ናት - ዝምታ ነው ቤቷ - ሰቀላው ሰገነት ፣
ጅራፏ ውሽንፍር - ቁጣዋ ሞት ጠሪ - የዘላለም ግርጣት ።
የአድማስ ማዶው - ቅላት ምስሏን ዘዋሪ ፣
ግዛቷ ገመገም - የመብረቅ ስባሪ ።
ግልምጫዋ እቶን - የጉድ ቁና ሰፈፍ ፣
ሰማይ ከዋክብቱን - አጥምዶ ሚያረግፍ ።
የሸማዋ ጥለት - ቢሸመን በእግዜር እጅ ፣
ቢደወር ቢታጠብ - ቢሰጣ አርያም ደጅ ።
እሷ እንደው እሷ ናት - አይሞቃት አይደንቃት ፣
ዝም ነው አመሏ - አይዳዳትም ቅብጠት ፣
ጥለቷ ነውና -
ያ ቀስተ ደመና - የሰማይ መቀነት ።
"""""""""""""".........///////...... """"""""""""""""" #________ሲራክ_ወንድሙ
___
```````````
_________
@getem
@getem
@getem
👍2