ግጥም ብቻ 📘
67.3K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#ስጋት_የገባው_ልብ
...................©ሲራክ ወንድሙ
እቱ የኔ ገላ ፥ የመንገዴ ማሾ ፣
የፍቅሬ ጥንስሱ ፥ ብቅልና ጌሾ ፤
እቱ የኔ ሰፈፍ ፥ የነብስ ወንዜ ቅጂ ፣
ናፍቆትሽ አስዳኸኝ ...
ፍቅርሽ አስለቀሰኝ ፥ እንደመንፈቅ ልጂ ።
.
ሚሻልም ቢመጣ ፥ አንድ አይስቴው ተኳሽ ፣
ፈሪ አይናቅም ፥ ውጭ ውጩን 'ማያመሽ ።
ተይማ ፥ ተይማ ፣
ተይማ ፥ ተይማ ፣
ጣል ጣል አታርጊኝ ፥ እንዳደፈ ሸማ።
................. // ................
@getem
@getem
@getem
👍2