ግጥም ብቻ 📘
67.5K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#ጥላዬ

ፊን-ፊን ስትይ ፥ በሰማዩ ጋሪ
ሽቦ የታደለ ፥ ዣንጥላ ወጣሪ
ጥበብ ከነ መርፌ ፥ መጨበጡን ረሳሽ
ያገው ጥላ መሰል
ከፍ ያልሽበት ሰማይ ፥ ለዝንት የዘረጋሽ።
ይልቅ ተመከሪ ፥ ገርነት አይግፋሽ
አውታርሽ መብዛቱ
ገትሮ የሚውል ፥ የሚጥል ቃሬዛ
አይምሰልሽ ዋዛ !!!
ዝናብ ካላስጣለ ፥ ሽንቁሩ እየበዛ
ፀሀይ ካልከለለ ፥ ማድያት ከነዛ
ማን ወዶ ሊጠለል ...ማን ስርሽ ሊገዛ
የከበበ ሳይሆን
ያስተዳደረ ነው ፥ እድሜ የሚገዛ።

ነሀሴ 2011
#አብርሀም_ተክሉ

@getem
@getem
@getem