ግጥም ብቻ 📘
67.4K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#ይድረስ #ለሀገሬ

በዚህ ጩኸት መሐል
ችለሽ ባትሰሚኝም ~ አይቀር መናገሬ
እኔ እንዳለው አለሁ ~ እንዴት ነሽ ሀገሬ
እንዴት ነሽ ሃገሬ ~ ንገሪኝ ግዴለም
ስለ ደህንነትሽ ~ የማልሰማው የለም
\
/
\
/
በአድርባይ እጆቹ ~ ደረት እየደቃ
ወድቃለች ይለኛል ~ ገፍትሮሽ ሲያበቃ
አመሉን ላይረሳ ~ ቦርጭ ቢመነኩስ
ታረዘች ይለኛል ~ የገፈፈሽ እርኩስ
በግፍ ተቀብትቶ ~ ቦርጭ ወጥሮት ገላው
ተራበች ይለኛል ~ ቀምቶሽ የበላው
ያላየሁት መስሎት
በትኩሳትሽ ላይ ~ እሳት መለኮሱን
ቅዠት ሲያቃትትሽ
ቀወሰች ይለኛል ~ ያሳብደው እሱን
ሊገነጣጥልሽ ~ ቢላውን አስሎ
ሞታለች ይለኛል ~ አስተዛዛኝ መስሎ
• • •
በቁሙ እያለ ~ የጁን እንዲያገኘው
ካንቺ ቀድሞ አይሙት ~ ሞትሽን የተመኘው
በጎሽን ማይወዱ ~ ሟርተኞች በሙሉ
መኖርሽን ይዩት ~ በህይወት እያሉ
* * *
እኔ ‘ምልሽ
ግን እንዴት ነሽ አንቺ ~ ጤናሽን ደህና ነሽ ?
ወደፊት እንዳትሄጅ
አላራምድ ያለሽ ~ እግርሽን ተሻለሽ ?
#ጎሽ
ማገገም መልካም ነው
ከርሞ ትድኛለሽ ~ ፈጣሪ ከረዳን
ፈፅሞ አይቻልም
ከዘመን በሽታ ~ በአንድ ጀምበር መዳን
ቀላል ነው እያለ ~ ወጌሻሽ ቢዋሽም
የዘመን ወለምታ ~ በጊዜ አይታሽም
• • •
እየጠዘጠዘ ~ በሕመም ቢያስነክስም
የትዉልድ ውልቃት ~ በአንዴ አይመለስም
• • •
ጠባብሶ ለማብላት ~ አራጅ ባይጀግንም
የዘመን ስብራት ~ በበግ አይጠግንም
• • •
ትእግስትሽ ተሟጦ ~ ተስፋሽ ፍፁም ሳይነጥፍ
ቀድሞ የዘረጋሽው ~ እጅሽ ሳይታጠፍ
ወደፊት ተመልከች ~ የኃላሽ ይረሳል
እያረፉ ማዝገም ~ ቢረፍድም ያደርሳል
ካሰብሽበት ቦታ ~ ደርሰሽ እስክታርፊ
እያስነከሰሽም ~ ይሄን ቀን እለፊ
====||====
ከሙሉቀን ሰ•


@getem
@getem
@getem
👍3