ግጥም ብቻ 📘
67.5K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#ድርሳነ ፍቅር!
(ሚካኤል አስጨናቂ)
።።።
አንቺ የእኔ ጣዖት!
እኔ ያንቺ አማኝ
የምዕመኑ ጠሎት ቅዳሴና አዛኑ
በየት በኩል ይሰማኝ?
።።።
እሳት ያንቺ ትንፋሽ ~ መብረቅ ያንቺ መውደድ
በየት መንገድ ልጓዝ ~ እምን ላይ ልራመድ?
እቴ ያንቺ ገላ
እንደ ጥቅምት አዝዕርት ፥ በአይን የሚበላ
አወይ የዓይኖችሽ... ግርማቸው ጉልላት
አወይ የጥርሶችሽ ... የገፃቸው ንፃት
በመዳፍሽ ቅጠል .... በጣትሽ አለንጋ
ሠንበር የወረሰው ~ ቁስል ልቤን ይዤ
እንደምን አልሰጋ?
።።።።
#እኔ
መድሀኒቴ አንቺ
በሽታዬም አንቺ
አንቺን እየዋጥሁኝ ~ አንቺን የምታመም
ባንቺ እየታመምሁኝ ~ ባንቺ የምታከም
.
ባለ አንድ ድዌያም ~ ባለ አንድ ክኒና
ወይ አልሞት ፥ ወይ አልድን
ወይ አልኖር በደህና!

@getem
@getem
@paappii