ግጥም ብቻ 📘
67.6K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#፪ ነፍስ ገዳዮች!
(ሚካኤል አስጨናቂ)
።።።።።።።።።
#ይኸው ዛሬም ድረስ!
የሰንበር ሀምሳያው ፥ ገመድ ተደራርቶ
አክሊለ እሾሁ ፦
ተምሳሌት እንዲሆን ፥ ለምስክር ወጥቶ
እየደበደቡ.. .. እየቀጠቀጡ
ግጥም አሰናኝተው ዜማ የሚያወጡ
እስክስታ 'ሚወርዱ ...
ከበሮ አንጋቾች አሉ በመንገዱ።
#ደግሞም ወዲህ ማዶ !
የሙት አካል ቆዳን
እየረመረሙ እየረጋገጡ
ስልቻ አበጅተው ገበያ ሚወጡ
በካቻምና ዝናብ ...
ዛሬ አርሰናል ብለው ፥ መግለጫ ሚሰጡ
አሉ ጎዳናው ላይ ፥
ሀቅታ ነው ብለው ፥ እብለት እየሸጡ ።
#ይኸው ተመልከቺ.. .
ከነ መግላችን ፣ ከነ ሰንበራችን
እሳት ባነፈረው ፥ ተበዳይ ገላችን
ሽቱ ሆነን ለሳሎን
ለእልፍኝ ለአዳራሽ...
እጣን ናቸው ብለው ቤታቸው ሲጫጫስ
#እይ ተመልከቺ
ጌጥ ሆነን ለአያያዝ ፥ ቅንጦት ሆነን ለአማኝ
ክሩ ደምስራችን.. .ለመዝሙራት ሲቃኝ
#እይ ተመልከቺ !
ከሙት አካላችን ...
ከፍራሽ ገላችን ፥ በሸለቱት ቆዳ
ከበሮዋቸው ሆነን ፥ ዜማቸው ሲቀዳ
#እይ ተመልከቺ !
እኛ በጨመቅነው ፥ በዘራነው እንባ
ውሀ ነው ተብሎ ...
ገዳያችን ሊፀድቅ ፥ ከጥምቀት ሲገባ
#እይ ተመልከቺ!
ከስጋችን ማዶ ፥ መንፈሳችን ሲቀል
ባልዋልንበት ሜዳ ...
ኩበት ተሰብስቦ ፥ ዳቦዋቸው ሲበሰል።

@getem
@getem
@getem
👍1
#ያንድ መስቀል እውነት! !

(ሚካኤል አስጨናቂ)

.

ውዴ አንተ ጌታ ...

እነሆኝ ያቃልህ የረቡዕ ትዝታ

ትጉና ፀልዩ የሚሉ ቃላቶች

ፍርሀትን በእምነት

ድልመንሳት የመቻል ልዩ ምልክቶች

.

ይኸው የረቡዕ ዕለት

የምክራቸው ስ'ተት .. .

.

#አንተ ኤልሻዴይ ጌታ !

ምሉዕ ሆነህ ሳለህ አልፋና ኦሜጋ

እንደምን ተዋረድህ በመክበርህ ፈንታ ?

ለምን ተሰቃይተህ ስጋህ ተንገላታ ?

ብዬ እንዳልጠይቅ ከእግርህ ስር ወድቄ

በፊትህ ጥፊዎች አለሁኝ ደምቄ ።

.

አንተ የእኔ እራት

የሀሙስ ግብዣዬ 

በልቼህ የጠገብሁ ፣ ጠጥቼህ የረካሁ

ከዘመን በደሌ ፥ እስር የተፈታሁ

ከጎኔ ቁጭ ብለህ ፥ ጥበብ የለገስከኝ

ሞትህ ቅኔ ሆኖ ፥ አለሁኝ ሲደንቀኝ።

.

ውዴ  አንተ ጌታ

እነሆኝ ያ ስቃይ የአርቡ ትዝታ

ሺህ ጠበኛ እጆች የሚገፉት አካል

የዓለም ፈራጅ ስጋህ ጅራፍ ይቀበላል

ፊትህ ደምግባትህ ምራቅ አርፎበታል

መስቀል ያጎበጠው ትከሻህ ተናንሶ 

የእናትህ ሀዘን ይሰማኛል ለቅሶ 

.

#ደግሞም ወዲህ ማዶ ...

ለቅኔው ስቃይህ መልስ የማጣው እኔ

አንተን ለማሰቀል ከበርባን ወግኜ 

በሞትህ ቀናቶች መሀል ተከልዬ

አዳምን እንዳየው ጥልቁን ተለይቶ

መሲሁ ይታሰር ወምበዴው ተፈቶ 

እላለሁኝ ቆ ሜ ጮሄ ባደባባይ 

ስቅለት ህ ድህነት ነው የሚጣፍጥ ስቃይ።

@getem
@getem
@paappii