ግጥም ብቻ 📘
67.6K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
ዛሬ ከግጥም ውጪ በሆነ ጉዳይ ....ነው ብቅ ያልነው....👇👇

ብሔራዊ ጀግና💚💛❤️

የአንድ ሀገር የፓለቲካ ሁኔታ ሲበላሽ ሌባ እንደ ጀግና ይቆጠራል ። ሀገር አፍራሽ ጀግና ይባላል። በመሠረቱ ብሔራዊ ጀግና ማለት የራሱን ጥቅም ትቶ ፤ ያለፈውን የሀገር ታሪክ አስጠብቆ ፤ የዛሬውንና የነገውን መንገድ ብሩህ የሚያደርግ ነው። ጀግና ትሁት ነው ፤ ከራሱ አልፎ ለሌሎችም ከዚያም አልፎ ለመጪው ትውልድ የሚያስብ ነው ጀግና የሚባለው።

ኢትዮጵያ ጀግኖች ነበሯት። እንደ አብነ ጴጥሮስ ያሉ ለእምነታቸው፣ለወገናቸው ለሀገራቸው ሲሉ መከራን ለመቀበል የቆረጡ የመንፈስ መሪነት የተላበሱ ብሔራዊ ጀግኖች ነበሩ። ጀግንነታቸው በጊዜ ሂደት ዋጋ ያጣል የማይባል ነው። አንዲት ሀገር በመቶ ዓመታት ውስጥ አንድ ብሔራዊ ጀግና ካገኘች የታደለች ናት። ኢትዮጵያ አድዋ ላይ የጥቁር ህዝብ ነፃነትን የፈነጠቀ ድል ያስመዘገቡ ጀግኖች ሀገር ናት። ይህን ድል የመሩት ዐጤ ምኒሊክ ብሔራዊ ጀግናችን ተብለው ብቻ አይገልጹም፤ የጥቁር ህዝብ ኩራት ናቸው። ምኒልክ ለጀግና ከተቀመጠው ትርጉም አንፃር፤ ከፍ ያሉ ብሔራዊ ጀግና ናቸው።

ብሔራዊ ጀግኖች በህይወት ሳይኖሩም፤በስራቸው ህያው ሆነው አቅጣጫ አመላካች ናቸው። ዐጤ ምኒልክ ፣ እቴጌ ጣይቱ ፣ አሉላ አባ ነጋ፣ፊትውራሪ ገበየሁ ፣ ባልቻ አባነፍሶ እና ሌሎችም የአድዋ ድል ያስመዘገቡ ኢትዮጵያን በሰሯቸው ብሔራዊ ጀግና ሆነዋል።

ፓለቲካውን በጥላቻ የሚሰሩ ቡድኖች ዐጤ ምኒሊክን እና ተከታዮቻቸው የነበሩትን ጥላሸት ሲቀቡ እና ሊያቃልሉ ሲሞክሩ ይስተዋላሉ። ይህ የትውልዱን ሞራል እና የሀገር ፍቅር ስሜቱን ዝቅ ማድረግ ነው። ምኒሊክ በጦር ሊወጓቸው የተነሱትን ርህራሄ ያልነፈጉ ሰው ነበሩ። ይህንን በአርዓያነት ልንከተለው የሚገባ እንጂ ልናጣጥለው መድፈር አይገባንም። ጀግንነታቸው እሴታችን ነው። ዐጤ ቴድሮስም በራዕያቸው ብሔራዊ ጀግናችን ሆነዋል።

በአጠቃላይ፣ ኢትዮጵያ በታሪኳ ብሔራዊ ጀግኖች እንደነበሯት መካድ አይቻልም። ሆኖም አሁን ላይ እንደ ቀደሙት ከፍ ያለ ቦታ የምንሰጣቸው ብሔራዊ ጀግኖች የሉንም። በበኩሌ፣ በዚህ ወቅት አሉን የምንላቸው ጀግኖች ፣ ብሔራዊ ጀግኖቻችን የመሆን ደረጃ የደረሱ ናቸው ለማለት እቸገራለሁ።

በሌላ በኩል ፣ ብሔራዊ ጀግኖቻችን እንደ ነቀዝ ታሪካቸውን የመቦርቦር ስራ ይስተዋላል። ይህ አሳፋሪ ብቻ ሳይሆን ፣ ትንሽነትም ነው። ብሔራዊ ጀግኖቻችን የሚከተል፤አርዓያነታቸውን ለበጎ ሥራ መነሻነት የሚጠቀም ትውልድ ነው ሀገር የሚገነባው። ጀግናን ማንኳሰስ ጀግንነትን መሸሽ ነው። የአሁኑ ትውልድ ያለፉትን ጀግኖቻችን አለማክበርና ላነሰ ተግባር መሰለፍ፤ <<ወይራ ዶግ ይወልዳል >> እንደሚባለው ከአያት እና ቅድመ አያት ማነስ ይሆናል። ያለፈውን ያለፈውን ጉልህ አስተዋጽኦ በመካድ ወደፊት መራመድ አይቻልም። በለጸጉ የሚባሉ ሀገራት ህዝቦች ብሔራዊ ጀግኖቻቸውን ሲያከብሩ ነው የሚታዮት። የጀግኖቻችን ምልክት ስንከተል ነው ራዕይ የሚኖረን። ካለፋት ጀግኖች የተሻለ ታሪክ ለማስመዝገብ ሥራዎቻቸውን እውቅና ሰጥተን መመርመርና ለመማር ዝግጁ መሆንንን ይጠይቃል።

((( ዶ/ር ባይለኝ ጣሰው ))

ምንጭ:- ኢትዮጲስ ጋዜጣ ቁጥር 10 ኀዳር 16 ቀን 2011 ( ተቀንጭቦ የቀረበ )
---------------------------------------------------


የኛስ ትውልድ የሚያስማሙን ብሔራዊ ጀግኖች አሉት..? እነማን..?

ብሔራዊ ጀግናቹን አስተዋውቁን ህይወታቸው የሚማርከን አገልግሎታቸው ቀልባችንን የሚገዛው፤ትግላቸው ወይ ብልሀታቸው በፈለጋቹት መስፈርት ሊሆን ይችላል #የኔ ብሔራዊ ጀግና ብለን ልዩ ስፍራ የሰጠናቸውን ግለሰቦች አስተዋውቁን

#እንደማሳሰብያ
1 የጀግናችንን ማንንነት
2 ያበረከቱት አስተዋፆ
3 በጥበብ ያለፉትን መሰናክል
4ያሳለፉትንት ፅናት ወይም መከራ
5 ያላቸው ብቃት
6.ወ.ዘ.ተ......ቢዘረዘር ስለ ብሔራዊ ጀግኖቻቹ ያለን ምስል ሙሉ ይሆናል

#እየጠበቅናቹ ነው !!!!!

ሸጋ ሸጊቱ ምሽት 💚💛❤️

👇👇👇👇
@balmbaras
@Lula_al_greeko
@wegoch
@wegoch
👍1
💚💛❤️
የአድዋ ሳምንት ላይ እኮ ነው ያለነው እንዴት ዝም ይባላል።

አሁን ልጅ ቢኖረንና "አደዋ ግን ምንድን ነው?" ቢለን ምን ልንለው ነው?

ለናንተ አድዋ ምንድነው...? አድዋን ስታስቡ ምን ይሰማቹሃል...?


#እየጠበቅናቹ ነው.......ዛሬ እስቲ ስለዚህ እናውጋ....አድዋ ሁለት ቀንም አይደል የቀረው.....

👇👇👇
@balmbaras
@Gebriel_19
@getem
@getem