ግጥም ብቻ 📘
67.6K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#እንዲያ_ነው_መረዳት . . . ፩
¢
#አሌክስ_ይህ
.
.
ሀ ሁ ሂ ሃ ሄ ህ ሆ
ሊረሳሽ : ነው : መሰል : ልቤ : ጮሆ : ጮሆ
መ ሙ ሚ ማ ሜ ም ሞ
ሊረሳሽ : ነው : መሰል : ልቤ : ታሞ : ታሞ
. . .
ልቤ : ታሞ : ታሞ
ልቤ : ጮሆ : ጮሆ
እንደ : መንፈቅ : ህፃን : ማውራት : እንዳቃተው
ኣልቅሶ : ለፍልፎ : ደክሞት : እንደሚተው
እውነቱን : ለማርዳት : ቃል : እንደሚቸገር
ሃዘኑን : መሻቱን : በእንባ : እንደሚናገር
. . .
እንዲያው : ዝም : ብቻ
በፀጥታ : ባህር : ሰላም : ላይ : መነከር
ምንም : ኣለማለት
በምንም : ከማንም : ኣለመከራከር
በሖነው : ባልሆነው : ከንፈር : ኣለመንከስ
ህይወት : ገበያ : ላዪ
እንደ : ኣልማዝ : መወደድ : እንደ : መዳብ : መርከስ
. . .
በቃ ! እንደዛ መሆን !
እንደ : ኣንዲት : ብፅዕት
ከችሎት : ፊት : ቆማ : ሆድ : እንደሚብሳት
እውነቷን : ለመንገር : ኣቅም : እንዳነሳት
ዝም : ብሎ : መስማት
ዝም : ብሎ : ማየት : እንባ : እያፈሰሱ
በህይወት : መንገድ : ላዪ
ለኣንዳንዱ : ጥያቄም : እንደዛ : ነው : መልሱ
. . .
እንደዛ : ነው : መልሱ
ከጥሞና : ገዝፎ
ከዝምታ : በልጦ
ቃል : ላይችል : ማስረዳት
ኣንዳንዱ
ንም : ስሜት : እንዲያ : ነው : መረዳት
.
.
.
.
በቃ ! ዝምምም : ማለት🙏

@getem
@getem
@getem