ግጥም ብቻ 📘
67.5K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
አንችን የሳምኩለት
( © #እሱባለው_ኢትዮጵያዊ )

ገነት እንደገባሁ ~ ልቤ ተደስቶ
ሀጥያተኛ ሲማር ~ ሲኦልም ተከፍቶ
ክዋክብት በሀሴት~ ከሰማይ ሲረግፉ
ተራሮች ተንደው ~ ምድር ሲነጠፉ
ደራሲያን ሁሉ ~ ስላንቺ ሲፅፉ


ስደተኛ ሁሉ ~ እቤት ተመልሶ
ጤና የነሳቸው ~ ሁሉም ተፈውሶ
ስራ ፈላጊዎች ~ አግኝተው እንጀራ
እናት በልጆቿ ~ በልቧ ስትኮራ
በሰልፍ የሰለቹት
ታክሲ ጠባቂዎች ~ መኪና ሲገዙ
አበዳሪ ሀገራት~ እዳ ሲሰርዙ
መንግሥት ያሰረውን ~ በምህረት ሲፈታ
ሀሳብ አሸንፎ ~ ጥይትን ሲረታ
ጎዳና እሚተኛው~ ቪላ ተሸልሞ
ብሄርተኛው ሁሉ~ ባንድነቱ ቆሞ


ፍጡራን በሙሉ
በደስታ ሲሞሉ

በረሃዉ ለምልሞ~ በአበቦች ይደምቃል
አራዊት በፊናው~ በፍቅር ይስቃል
የምመኘው ሁሉ ~ ሆኖ ይታየኛል
አንቺን የሳምኩለት ~ እንዲህ ያደርገኛል ።
______ ዛሬ |2010_______

@getem
@getem
@lula_al_greeko
🤩1
የሰው ሀገር የት ነው
የግጥም ስብስብ እና አጫጭር ታሪኮች
በቅርብ ቀን
#እሱባለው_ኢትዮጵያዊ

@tebeb_mereja
@tebeb_mereja
ግጥም ብቻ 📘
Audio
<< የምትወዱትን እስካልሰጣቹ ድረስ አላመናቹም>> (ነብዩ መሀመድ )

እኔ ደሞ ለምን ትንሽ ለወጥ ባደርገውስ የምትወዱት የወደዳችሁትን ነገር መስጠት እንኳን ባትችሉ ያ የወደዳችሁትን ነገር ሰዎች እንዲፈልጉት እንዲገዙት እንዲያነቡት እስካላደረጋችሁ ድረስ እናንተ ስስታም ናቹ። መስጠት ማለት ቁስን ብቻ ማካፈል መለገስ አይመስለኝ ...ፈገግታም መስጠት ነውና። መልካም ንግግርም መስጠት ነው።

#እኔ ዛሬ የወደድኩትን ውስጤን እያሞቀኝ ያለውን አንድ መፅሐፍ አለ። "ትዝታዬ ለኔ ትዝታዬ ለአንቺ ይሰኛል"

ለመጻፍ መቸክቸክ ብቻ በቂ አይደለም ። መጻፍ ለመጻፍ ሱስ ማውጫም ከሆነ ችግር ነው ። አንዳንዶች ደግሞ አሉ ። ሰከን ርግት ብለው ላገር ለወገን የሚበጅ ረብ ያለው ሃሳብ የሚጽፉ ። ሸጋውን መርጠው ለነፍስ የሚደርሱትን እንካቹ የሚሉን። እነርሱን ባነበብን ጊዜ እንጽናናለን ።ውስጣችን ሲረጥብ ይሰማናል። ከጥቂቶቹ መሃከል አንዱን እነሆ ላስተዋቅቃችሁ ።
#እሱባለው አበራ ንጉሤ ይባላል ። ሸግየ ጸሃፊ ነው ። ጸሃፊ ነው ስላችሁ ጸሃፊ ነው!!!! መፅሐፉ በቅርቡ ማለትም በሀምሌ ወር መጨረሻዎች ላይ ነው የወጣው...ብዙ ሰዎች ገዝተውት ወደውታል እናንተም ገዝታቹ ብታነቡት በእርግጠኝነት መናገር የምችለው ትወዱታላችሁ።

ዋጋው 120 ብር ነው ጃዕፈር ጋር ጎራ የምትሉ ከሆነ ግን 70 ብር ታገኙታላቹ...🙏

!!!!! መጣፍማ ሃቂቃው ነው! !!!

እንኪቶ ማሂቶ! !!! ይኸው ነው!!!!!!!!!!!!!
ተመኜሁላችሁ!!!!!
ሽብርቅርቅ፣
ድምቅምቅ፣
ፍልቅልቅ ያለ፣ በሳቅና በደስታ የተሞሸረ፣ ንባብ
ጀባ!!!!!!!

@getem
@getem
@Nagayta