ግጥም ብቻ 📘
67.6K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
" #ባውቶማቲክ_ግዜ#መሸከሙ_ጓንዴ ...
#አይከብድም_ወይ_ጓዴ"

ይብላኙን ለነሱ…
በጠዋት ገስግሰው ፥ አንድ ኪሎ ሎሚ ፥ ገዝተው ለደረሱ
ያውም በዚ ግዜ
ሎሚ ጥሪው ከብሮ ፥ ከጅ ላይ በጠፋ ፥.... በተወደደበት
ሜክ አፕ የለቀመው ፥ ሴቱም እንከን የለሽ ፥ ውበት በደፋበት
ወንዱም አቅሉን ስቶ
ሎሚ በተረሳው ፥ የመኪና ቁልፉን ፥ እያነጣጠረ
አይፎኑን ደረት ላይ ፥ ሰዶ እያነጠረ

"አይፎን ብወረውር .....እስፖንጇን መታሁት
አወይ ተሳክቶልኝ......ጡቷን ባገኘሁት"

በሚል ሀርሞኒካ .....ትዳር የሚናፍቅ
አልሞ ተኳሿ .....ከሷ ብዙም ሳይርቅ

እያረጋገፈች ከመሬት አንስታ
የላክልኝ አይፎን .....የሰደድከው ቁልፉ
ከደረቴ ነጥሮ....መሬት መዘርገፉ
አንተም ጎበዝ አጥቂ.....
ጎበዝ ተከላካይ ፥ መርጦ ገራም ልብህ የመሸናነፉ
ማመላከቻ ነው ፥ ቅኔው ሲተረተር ፥ እንዲያው በግርድፉ
ለዚህ ....ለዚህ እንጂ ፥ ዱላ ለመመከት
ውበት ጎሎት አይደል
በል ነዳጁን ስጠው ፥ ቦታ እንያዝ እና ፥ ማማሩን ተመልከት
ብለው ተያይዘው ፥ ከስርፋው ታበሱ
ያንን ሁሉ ሎሚ ፥ የሸመተው ጉብል ፥ ለማን ይስጠው እርሱ
በዚህ የሀሳብ ዚቅ....... እንደተዘፈቀ
ታቦቱን ያጀበ ፥ የሞንሟኖች መንጋ ፥ ሳይገላመጠው ከተራው አለቀ
ይህን እያየሁኝ....
ከሎሚም ፣ ከቁልፉ ፥ የቀረሁኝ እኔ
ጉብታው ላይ ቆሜ ፥ ሲወጣና ሲወርድ ፥ አየዋለው ባይኔ
ድንገት ፥ ተስፋ ራሱ ፥ ተስፋ ቆርጦ ሳለ
ለመሄድ ሲነሳ ፥ የኪሎ ዘንቢሉን ፥ እንደጠቀለለ
አምሮት የምታጭር...ጥበቃ እምትገታ
ካለችነት ቦታ ፥ በፍጥነት ተነስታ
ወደርሱ ቸኮለች ፥ ተሳልሞ ለመሄድ ፥መነሳቱን አይታ
ለጥቂት ሰአታት ፥ አንድ ላይ አወሩ
ፈገግ አለች እሷ......ተፈታ ግንባሩ
ነጠላ ሸፍና ፥ እጁን ጨበጠችው
ያንን ሁሉ ሎሚ ፥ አንድ ራሷ መጥታ ፥ እሷው ወሰደችው።

ይህኔ...
የማላውቀው ጓዴ
በለስ ቀንቶት ባየው ፥ በባከነው አይኔ
እሰይ..........አልኩኝ እኔ....
እንደአቅሙ ጣጥሯል ...
አልተሰበሰበም ...በተስፋ መቁረጥ ውስጥ ፥ አዝኖ ልክ እንደኔ
ከቆመ የዳኸ ፥ አስር እጅ እንዲሻል ፥ መክሮኛል ዘመኔ ።

#ኋላ_ግን_ስሰማ .... #ልጅቷ_ጭማቂ_ቤት_አላት...(😁😁😁)

#አብርሀም_ተክሉ ( #መርዕድ)

@Abr_sh

@getem
@getem
@getem