ግጥም ብቻ 📘
67.5K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#ሀሰሳ #አክቲቭ — ኢ — ዝም
በዚህ በኔ ትውልድ
በዚህ በኛ ዘመን
ከሰዎች ሞት ይልቅ ~ አሟሟት ቢታይም
ገዳዩ ነው እንጂ ~ ሞት አይለያይም
#እኔ #አክቲቪስት #ነኝ
ለሰዎች ምታገል ~ የህሊና ባለእዳ
ሰው በሰውነቱ ~ ደርሶ እንዳይጎዳ
ለሌሎች ልሞላ ~ ከራሴ ላይ ምዘርፍ
ርቀቴን ጠብቄ ~ ትውልዴን የማተርፍ
#እኔ #አክቲቪስት #ነኝ
በዛሬ ቀለሜ ~ የሰው ነገን ምስል
ሸፍኜ ማስነጥስ ~ አፌን ይዤ ምስል
ሠው ከመሆን ውጪ ~ ብዙ ማልጠበብ
ነብሶችን ለማዳን ~ እጆቼን ምታጠብ
#እኛ #አክቲቪስትቶች #ነን
የኛ ቢጤ ሰዎች
በፍፁም ነፃነት ~ በደህና እንዲሄዱ
ዛሬ በር ዘግተን
ቤት የተቀመጥን ~ ነገ እንዲራመዱ
———||———
ከሙሉቀን ሰ•

@getem
@getem
@peppac