ግጥም ብቻ 📘
67.5K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#ንግስተ_ምላስ
…………………………………
ሁሉ ተነጫናጭ…ሁሉ ተናጋሪ፡
አለቃቃሽ ብቻ…የውስጥ ብሶት አውሪ፡
የራስ ጆሮ ሸጦ…በሠው ጆሮ ኗሪ፡
ያላዳምጥም ባይ…የልናገር ዘመን፡
አመዛዝኘ ነው…ብሎ ሲሠጥ ስልጣን፡
ለምላስ ንግስና…ኩሊ አድርጎ ጆሮን፡
ትክክል ነኝ ይላል…አሹሎ ምላሱን፡
እናም በዚህ ዘመን…የኔ አዳማጭነት፡
ሊያሠማኝ ካልሆነ…የሁሉንም ብሶት፡
ለኔ ጥቅም የለው
ምላሴ ካልጮኸ…ምኞቴን ለማግኘት፡
ነገር ግን…………
ያዳማጭ ምላስ…ለተናጋሪ አጭር ነው ብለው፡
የኔ እሪ ማለት ካልተሠማቸው፡
ልክ እንደነሡ እለፈልፍ ዘንድ፡
ምላሴ ይርዘም ይሁን ፩ ክንድ፡
ጆሮየን ልቁረጥ ልቀጥል ከሡ፡
ሆኗልና አሁን…
የሠው ማንነት…ጥቁር ምላሱ።
#ተፃፈ_በዳዊት_ሠለሞን
ለግጥሙ አስተያየት @davaye

@getem
@getem
@gebriel_19