ግጥም ብቻ 📘
67.6K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#ነገ_አገኝሻለው_!!

#ምናባቱ....ጀምበር ~ ከሰው ምን ፈልጎ ?
በሰጋር ፈረሱ ~ በደቂቃ ፉርጎ
እየቀጣጠለ ፥ በግዜ ሀዲድ ላይ ፥ እለቱን ይስባል
ቢሞላም ቢጎልም
እስኪበጠስ ክሩ ፥ ተጓዡም ይከንፋል
ከሳይንስ የራቁ ፥ ከእምነት የቀሩ
ውሉ ተማቷቸው...... ለተደናገሩ
አፍንጫና ጭራው ፥ አይለይም ባቡሩ
መጨረሻ ያሉት ፥ ከፊት ይዞርና ፥ ይዘረጋል እግሩ
በፈረስ የጠፋ ፥ በኮቴ ይገኛል ፥ ብለው ሲዘምሩ
#አንቺን_ያጣ_ልቤ
የህይወት ኮምፓሱ
ተሰብሮበት ዘንጉ ፥ ሼመንደፈር ቆሟል
ፌርማታሽ እርቆ
ስንቄ ያልኩት ተስፋ
በመገተር ብዛት ፥ ሚዛኑ ተዛሟል
#ቢሆንም_ግን
እስክወድቅ ድረስ ፥ በድኔ እስኪዘረጋ
#እጠብቅሻለው
እለቴ እየመሸ ፥ ጉጉቴ እየነጋ !!

#አብርሀም_ተክሉ ( #መርዕድ)

👉 @Abr_sh

@getem
@getem