ግጥም ብቻ 📘
67.3K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#ቴዎድሮስ_ካሳ
ኦ ፍቅሬ ፀደይ ኾይ !
.

ምን በወጣዉና ፥
በነፍሴ ፍም እሳት ገላየ ይንገብገብ
በመንፈሴ ዚሎሽ ፥ ሁለንታየ ይርገብ ።
-
በልጅ ንፁህ ገላ ፥ የጥያቄ መንፈስ እንደሚለቆጠዉ ፣
ከሽማግሌ ልብ ፥ የሞት ሀያል በትር ፥ የህይዎት ከንቱ ማር እንደሚቆረጠዉ ፣
ፍቅርሽ እንደዚያ ነዉ !
መጣሁ መጣሁ ይላል ~ መሄጃዉ ሲጨንቀዉ !!
-
በበድን ገላየ አዚም አንተርሶ
ከዓለም ያስተኛኛል፥ ከነፍሴ ቀስቅሶ ።

ከልቦናየ ባህር ፊት የሚቆም ፥ የጊዜን አሳ አስጋሪ
ተሻሚና ፤ ጎልብችና
ለጎጆሽ ጎጆ ስሪ ።
...ኦ ዉዴ ፀደይ ኾይ ...
ደንባራ ፥ ድንጉላ ፈረስሽን ፡ በጥላቻሽ ጅራፍ ግሪዉ
የፍቅርን ሀያል ህመም ፥ ቁስሉን ፥ ስቃዩን እንድታዉቂዉ ።
ደግሞም ዝም ብለሽ
የጥላቻሽን ጦር ስበቂና ፥ የፍቅርሽን ጋኑን ስበሪዉ
በተወጋሽዉ ልክ ነዉና ፥ የምትመግይዉ የምትደሚዉ ።
ኦ ፍቅሬ ፀደይ ኾይ !
ለማይጎህ ለልቤ ፅልመት
ለማይቆም ለአይኖቸ ጅረት
ሞክንያት ባይኾን ምናለ
ጣዖቱ ፥ የልብሽ ዉበት ።
አታዉቂና...
ከፍቅርሽ ጉድጓድ እንደማያንስ የጥላቻየም ጥልቀት ።
ደግሞም ፥

@getem
@getem
@getem
#እምወድሽዋ! ቅዳሜዋ! ሸጋዬዋ!


ዛሬ ከድር ናቸዉ ይሏል ወሎየ !
ከቅዳሜ ቆሌ የተዳረ ለታ ፥
የትኛዉ ቀን ይደብርሃል ብባል ፥ የትኛዉም ልል እችላለሁ ። ሸገር ካለሁ ግን ምን መዓት
ቢመጣ ቅዳሜ አይደብረኝም ።
የአዲስ አበባ ቡና ቅዳሜ ቅዳሜ ይለያል ፥ ወላ ለምን በጨዉ አትጠጣዉም ( ሃሃ ወዮ
ክባድ ! ) ። የለመድከዉን አሰልች ሰዉ እየተመለከትክ ፥ ያን ሰዉ በቅዳሜ ስትመለከተዉ
አትጠግበዉም ፥ ብርቅ ይኾንብሃል ። መፅሔቱ ፣ ጋዜጣዉ ይጎርፋል ፥ በቅዳሜ ። ሳምንቱን
በስራ ተጠፍሮ የነበረዉ ከተሜ ፥ በእለተ ቅዳሜ የወሬ ጋኑን ይፈታል ፣ ወገቡን ለሳቅ እና
ለጨዋታ ያዘጋጃል ። ሀብታም ከባንኮኒዉ ፤ ድሀም ከስኒዉ ስር ይለገታል ፥ በቅዳሜ ።
እንደኛ ያለ የገጠር ልጅ አዲሲቷን ልብሱን የሚለብሰዉ ለበዓል ነዉ ሃሃ ፥ የአዲስ አበቤ
ቆንጆዎችስ በቅዳሜ ቀሚስ ላይ የፈሰሱ የአልማዝ ፈርጦች መስለዉ ይዉላሉ ።
በቅዳሜ የጓደኞች ሳቅ ይጎርፋል ፣ ከሩቅ ሀገር ጨዋታ ይሰማል ። ሁላማ ስትራመድ
ትነጥራለህ ስልህ ፥ ስለምነጥር ነዉ ።
የዛሬዉ ቅዳሜ ደግሞ በቃ ይለያል ፥ አይንህ ስትገልጥ ሀገሩ ፍስለታን ሞሽሮ ቁሟል ።
አንተስ ምን ታደርጋለህ ደጀ ሰላሙን ትሳለምና ፣ ከመፀሀፍት ደንበኛህ አለላ መፅሔትን
ትገዛና ( ፍትህ የምትሉ ፥ ነገር አትፈልጉኝ ) ፣ የኤፍሬም ስዩምን 'ምክንያቱም ዛሬ ቀኑ
ቅዳሜ ነዉ ግጥም ' በቃልህ ትወጣዉና ፣ የጠዋት አጃኢበኛ የዶሮ አይን ቡናህን ትልፍና ፣
ከሰዐት ሸገር ኤፍ ኤምን አሻግረህ እየናፈቅህ ፥ ቀኑን የሚያረዝምልህን አምላክ
ትጋተተዋለህ ።
ኤፍሬምን ትንሽ እናዉርደዉ እስኪ
-
ቀጭን ወገቧ ላይ
ከእንብርቷ በላይ ልብሷ ተንጠልጥሏል
የወርቅ መስቀሏ
ጡቶቿ መካከል ዘንበል ብሎ ወድቋል
መንገድ ላይ ያየኃት
የማላዉቃት ሴት ናት ።
ወዴት እንደምትሄድ ባሳቤ ገመትኩኝ
አንድ የቀጠራትን ወንደላጤ አሰብኩኝ
ሠባት እንቁላሎች
ግማሽ ኪሎ ሥጋ....( ገዝቶ )
ከርሷ ጋር ካልሆነ
ቡና አልጠጣም ብሎ አሥሬ እያዛጋ
መጽሐፏን ከፍቶ
በሩን ክፍት ትቶ
መልሶ መላልሶ ሠዓቱን እያየ
የሚጠብቃት ሠዉ
ሐሳቤ ዉል አለዉ
ምክንያቱም ዛሬ ቀኑ ቅዳሜ ነዉ ።
-
ይችን የቅዳሜ ከረሜላ እንዳታልቅብኝ እየሳሳሁ መምጠጥ ጀምሬያለሁ ፥ መልካም ቅዳሜ
ይሁንላችሁ ወዳጆች ።
አለላን አንብቡት ፣ በቃ ምርጥ ነዉ
ወላ ከመፀሀፍ እኩል ነዉ
አጃኢበኛ ብዕረኞች ዘምተዉበታል
ጋብዣለሁ ።
ደግሞ ደግሞ " ማርሲላስ " የሚል መፀሀፍ ገዝታችኃል ፥ በሉ ቶሎ ግዙ ። ደራሲዉ ነፍሱን
ሰጥቷል። በአንድ ሰሞን ሙሉጌታ ተስፋየ ለቅሶ ሄዶ ማስተዛዘኛ " ግጥም ሰጠ " ሲባል
ሰምቸ ጉድ ብያለሁ ። የዚህኛዉ ደግሞ ባሰ ፥ ጊዜዉን ፣ ነፍሱን ፣ መጣፈጡን ሁሉ ነዉ
የቸረዉ ። አህመድ ሁስ ፥ መልካም ቅዳሜ ኸይር አሳብየዋ ። የቅዳሜን ቡና በጋበዝኩህ
በወደድኩ ነበር ።

#ቴዎድሮስ ካሳ

@getem
@getem
@balmbaras
#ቴዎድሮስ_ካሳ
~
የለም ፥
አማሁሽ ለነፍሴ ህዋይ
ዘራሁሽ በፀፀት ሰማይ
ቃኘኹሽ በክፏ ሀሳቤ
ጣር ኾነ ፥ ሳቅሽ ለልቤ
የፀደይ ፊት የሚመስለዉ ፣ ብርሀን ገላሽ ጨለመኝ
ከነፍስሽ ስር የሚፈስሰዉ ፥ ቃል ልቦናሽ አሳመመኝ
አየ የእኔ'ና ያንቺ ነገር ተቋጨ ፥
ፍቅር አበቃ መሰለኝ !

@getem
@getem
የህይዎት ጣዕም
የህይዎት ጠረን

ውብ ብርጭቆ
ቆንጆ ሲኒ ፤
ትኩስ ቡና
ቀዝቃዛ ወይን ፤
የሞላበት ።

ቀዝቃዛ እድሜ
ወጣት ደረት ፤
ትኩስ ሌሊት
የሚያድግበት ።

ቀዝቃዛ እኔ
በረዶ እኔ ፤
ትኩስ አንቺ ያለሽበት ።

የህይዎት ጣዕም
የህይዎት ውበት

ቀዝቃዛ ሻይ
እጅሽ መሃል የበረደ ፤

ግማሽ እድሜ
አንቺን ሲያስብ የነጎደ ፤

ጅምር ሀሳብ
ጅምር ግጥም
ጠርቶ ያመጣው ፤

ውብ ወዘና
ጎረምሳ ሌት የሚጠጣው ።

የህይዎት መልክ
የህይዎት እድሜ

የአንቺ በራፍ
የአንቺ መስኮት ፤

የዓይን ፍቅር
በዓይን ስርቆት ፤

ትንሽ ቁስል
እድሜን ሙሉ ትዝ የምትል ፤

የአንቺ ፍቅር
ስር የሚሰድድ ከጅማት ስር ፤

የህይዎት ጣዕም
የህይዎት ውበት

መኖር ሳስቶ
ፍቅርን መስሎ ፤

መኖር ሳስቶ
ገላን ጥሎ
' የለምን' ያህል አክሎ ።

#ቴዎድሮስ_ካሳ

@getem
@getem
👍4542🔥1😱1