ግጥም ብቻ 📘
67.6K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#በእውቀቱ_ስዩም
.
እንደ ጊዜው መክፋት
እንደ ግፉ መስፋት
እንዳገሩ ክስመት
እንዳገሬው ጥመት
እንደሰው ጭካኔ፤ እንደ ልቡ ፍሬ
ታምር ነው መትረፍሽ ፤ ታምር ነው መኖሬ::

የበጎ ሰው ሀሳብ ፤ ሲካድ እለት በለት
ጉድጏድ ተምሶለት
ሰብእና ሲቀበር፤
በዚህ ምድር መኖር ፤ አያስመኝም ነበር::

ምድሩ ሳር ቅጠሉ፤ በስጋት ተሞልቶ
የማለዳው ሰማይ፤ እንዳንቀልባ ቀልቶ
ታረደ
ነደደ
ከዘብጥያ ወጥቶ
ዘብጥያ ወረደ
የሚል ዜና ብቻ አየሩን ሲሞላው
ሰው በገዛ ጥላው
በርግጎ ሲሸበር
በዚህ ምድር መኖር ፤አያስመኝም ነበር::

አዎ
ለጊዜውም ቢሆን፤ ግፍ ያደነዝዛል
በደል ያስተክዛል
ጊዜም ጠብን ሽሮ፤ ወደ ፊት ይጏዛል
በልብ ሰሌዳ ላይ ፤ቂም ይደበዝዛል
በነገ ያመነ
ልጁን ቀብሮ መጥቶ፤ ሚስቱን ያስረግዛል::

ይቅርታና ምህረት
ፍቅርና ህብረት
ከግፍ ጋር ፍልሚያቸው ፤ ቢሆን የሞት ሽረት
ዳገት ይወጣሉ ፤ በንጥፍጣፊ አቅም
የመኖር ፍላጎት
ዘመም ይላል እንጂ ፤ ተገርስሶ አይወድቅም::

@getem
@getem
@getem
1👍1
የነገው ንፋስ
_________
ያንን ገለባ ልብ፣
ከደጅ የወደቀው።
አድራሻህ ወዴት ነው፣
ብለ አጠይቀው።
የነገው ንፋስ ነው፣
መንገዱን የሚያውቀው።

@getem
@getem
@paappii

#በእውቀቱ ስዩም
አንተው ህግ አርቃቂ
አንተው ፍርድ አፅዳቂ
የወህኒው ጠባቂ፤
ደካማው ሰለባህ በሀይልህ ስር ታስሮ
ያመልጥ ይሆን ሰብሮ? ይበቀለኝ ዞሮ
ምን ያስብ ምን ያቅድ ?
ምን ይክብ ምን ይንድ ?
ብለህ በማውጠንጠን እረፍት ከምታጣ
ምርኮኛህን ፈተህ አንተው ነፃ ውጣ ።

@getem
@getem
@paappii
#በእውቀቱ ስዩም
👍1
ድሎት እየዘሩ

#በእውቀቱ ስዩም

ይቅርብኝ ፍሪዳው፥
አልጠግብ- ባይ ይብላው
ወይኑም በፅዋ ላይ ፤ እንደ እንኮይ የቀላው
ግዴለም ይለፈኝ !

ጊዜ ምቾት ነስቶ
ምንጣፉን አንስቶ ፤
ፅናቱን ያውሰኝ
በመጋዝ ጠርዝ ላይ፤
መራመድ ከተማርኩ፤ ማንም አይመልሰኝ::

አውቃለሁ

አሳር አሻራውን፣ ግንባር ላይ ሳያትም
ድሎት እየዘሩ ፥ ድል አይመረትም ::

@getem
@getem
@beckyalexander
😁1