ግጥም ብቻ 📘
67.6K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#እመ_መከራ

[#በእውቀቱ_ሥዩም]

ኢትዮጵያ እመ መከራ
የግዜር መመራመሪያው
የስቃይ ቤተ-ሙከራ
መውደቅማ ነበር ያባት
እንደ ያሬድ እስከ ሰባት
እንደ በላ ብላቴና
የእንክርዳድ ሙልሙል እንጎቻ
የትውልዴ እጣ ፈንታ
መውደቅ፥ መውደቅ፦ መውደቅ ብቻ!

#Share
@getem
@getem
@getem
👍1
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሠላም አደረሳችሁ

__ለአባቴ______

ሰው ብቻ አይደለህም፥ካፈር ወጥተህ ላፈር
መልእክ ነህ ሉሲፈር*
ክብርህ ማንነትህ ባመጽ የሚታፈር
የማትንበረከክ
የማትርመጠመጥ
ከባለጌ ዙፋን ፥በርጩማ የምትመርጥ፣

ያለ ባሕር ሰርጓጅ፥ያለ ሙሴ በትር
በመታገስ ብቻ ፥ባሕር የምትመትር
ካዘልከኝ ጀምሮ፥እንኮኮ ጫንቃህ ላይ
ከፍታውን እንጂ፥ዝቅታውን ላላይ
እንደንስር መጠቅሁ፥እንደ ምስራቅ በራሁ
የገዛ ክንፎቼን፥እንደ ዳንቴል ሠራሁ፤

በርግጥ ደሀ ነበርክ
ከሰላምታ በቀር፥የማታበረክት
ነጠላህ መናኛ፥ሰውነትህ የክት፤

በርግጥ ደሀ ነበርክ፥የነጣህ የጠራህ
ከጦር ሜዳ ይልቅ፥ገበያ ሚያስፈራህ
ቤሳ ባታወርሰኝ፥አወረስከኝ ትግል
የትም እንዳይጥለኝ፥ሕይወት እንደ ፈንግል፤

አባዬ ብርሃን
አባ የምስራቅ በር
ገመና ሸሻጊ፥እንደ ካባ ገበር
አባቴ ባትሆን፥ምን ይውጠኝ ነበር።


(*'ሉሲፈር' አጥቢያ ኮከብም እንደማለት ነው)

#በእውቀቱ ሥዩም
የማለዳ ድባብ
ገፅ 72

@getem
@getem
@beckyalexander