ግጥም ብቻ 📘
67.3K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#እምዬ #ያልታደለች
(በገጣሚ #በረከት #በላይነህ )

እምዬ ያልታደለች
ተመዘኚ ሲሏት ~ መዛኝ ነኝ ትላለች
እምዬ ሰከረች
ልትመዘን ወጥታ ~ መዛኝ ሆና ቀረች!
የቅቤን ስብራት ~ በቅመም ለማከም
በወቀጣ መዛል ~ በድለዛ መድከም
የቅቤን ወለምታ ~ በቅመም ለማሸት
ሲደቁሱ አድረው ~ ሲቀይጡ ማምሸት
የቅቤን ጉብዝና ~ በቅመም ለማትጋት
እያመሱ መዋል ~ እየፈጩ ማንጋት
* * *
ይልቅ ግድ የለሽም !
ለቅቤ ጥፍጥና
ለቅቤ መአዛ
ቅመም ከመደቆስ ~ ቅመም ከማበጠር
ከቅቤያችን በፊት ~ ከብቶቹን ነው ማንጠር
እንስራ ወዝውዞ
በጢሳጢስ ናውዞ
ለቅቤ ከማማጥ ~ ለአይብ ከማማጥ
ከወተቱ በፊት ~ እስቲ ላሟ ትናጥ
ማለቢያ ከማስፋት ~ ማለቢያ ከማጥበብ
ከግቷ አስቀድሞ
ከሆዷ አስቀድሞ ~ ምግቧን ነው ማጠብ
* * *
ለምሽቱ ድምቀት — ቀኑን ሳይበርዙ
እንዲህ ነው ፊተኞች — ‘ሩቅ የሚጓዙ
እንዲህ ነው መስማማት — መግባባት ከዛፉ
ከስር ሳይመትሩ — አይታይም ጫፉ !
* * *
ግራ ነኝ ይለኛል
ቀኝ ነኝ ይለኛል —መሀል ነኝ ይለኛል
ዳሩ ካልተያዘ — መሀል የት ይገኛል?
እውቀት አባ አያልቄ
እውቀት አባ አይፈሬ — ጥያቄ ሲያድለው
ለግራም የራሱ — ግራና ቀኝ አለው
ለቀኝም የራሱ — ቀኝና ግራ አለው
መሃልም ለራሱ — ሌላ መሀል አለው
* * *
እይዉ!
ሰው መጠየቅ ትቷል
ሰው ፍለጋ ትቷል ~ ሰው ማጣጣም ትቷል
ለመንስኤ ዝሏል ~ ለአመክንዮ ታክቷል
በጥድፊያ ሊያስታግስ~የመሰንበት ሱሱን
ጥያቄ ነው ይላል ~ የከሸፈ መልሱን
ነፍስያን ተብትቦ —በስሜት ሰንሰለት
መቀያየጥ ሆኗል —መጠያየቅ ማለት
መመሳሰል ሆኗል —መመላለስ ማለት
* * *
ኩሬ ነው?
ወንዝ ነው?
ሃይቅ ነው?
ባህር ነው? ጎርፍ ነው?
ገባሩ? ጅረቱ? ማእበሉ? ምንጮቹ?
አዞ አለ? አሳ አለ?
.
.
እኮ የምን ጥያቄ ! ~ እኮ የምን ክርክር !
በቃ!
“ዋና ነው!” ይልሽና ~ ከነልብሱ ንክር።
አዎ!
“ዋና ነው!” ይልሻል ~ “አጨብጭቢ!” ይልሻል
“ዋናህስ?” አትበይው
አሽሟጠጠች ብሎ ~ ችሎት ያቆምሻል
ያው!
ችሎቱ የእነሱ — ችሎታው የሌላ
ይልቅ አጨብጭቢ —አዞ እራቱን ይብላ!
ለንክር ጭብጨባ —ለዝፍዝፍ ጭብጨባ
ሆዱ አሳ ሲለው — አዞ ለሚያረባ
* * *
ተመልከች!
ሽንቁራም እውቀትሽ —ንፋሱን ሲነዛ
ከጋላቢሽ ይልቅ —የሚገለብ በዛ
ንፋሳም እውቀትሽ —ውርጩን እየነዛ
ከሚያነደው ይልቅ —የሚያከስለው በዛ
ግልብልብ እውቀትሽ —ወላፈን ደሞዙ
የሚለበለቡት — ከሚበስሉት በዙ።
እይው!
ማእዘን አፍርሶ —ግድግዳ እያደሰ
ወለሉን ሰውቶ —ጣሪያ እየቀለሰ
ቅርንጫፍ ሊያሳምር —ስር እየበጠሰ
እልፍኝ ተደፈረ —አጥር ተገሰሰ
መስማት ጥንቡን —ጣለ ማየት ረከሰ
ቋንቋ መነመነ — ለትርጉም አነሰ
* * *
ቆይ እኔ የምልሽ!
ተፈጥሮ ሂደቷ — እንዲህ ሳይጓደል
ለመሮጥ መንደርደር — ግድ ነበር አይደል?!
ታዲያ! ቀረ እኮ ነው ‘ምልሽ
መንደርደር መመርመር መፈከር መዘርዘር
አኩርፈው የሄዱት — በየት በኩል ነበር?
* * *
የወል ቀማሽ ሁላ
ድፍርስ እየጠጣ — ሽርክት እየበላ
በግርድፍ አኝኮ — ለግርድፍ ተሻምቶ
“ውጫለሁ!” ይልሻል — ወደ ሆዱ ተፍቶ
* * *
የምር ደስ አይልም!
የጥርስን በአንጀት
የጆሮን በምላስ — ʻያፍንጫን በመዳፍ
ግብር እያቀማሙ — ዋጋና ስም መጻፍ
የምር ደስ አይልም!
የልብን ደረት ላይ
የነፍስን ልብስ ላይ— ቀያይጦ በማፍካት
ጣእምን መመርመር — ውበትን መለካት
ደስስስስስ አይልም!
* * *
እምዬ!
አትላፊ አትዳሪ ከእንክርዳድሽ
ይልቅ
ወንፊት ግዢ ለወንፊትሽ
ሰፌድ ግዢ ለሰፌድሽ
* * *
ቀማሽ ሲደራረብ —ጣእም ተቀያየጠ
ባለቤት ሳያጌጥ —ውበት አመለጠ
ከእህሉም አይደለ
ከቅመሙም አይደል
ጨው አንሶም አይደለ
የምላስ ህመም —ነው ጣእም የገደለ
* * *
ምን አረገሽና!
ቀቃዩ ጠባሹ
ከታፊው አማሹ
ወቃጩ ነስናሹ
ለርካሽነትሽ — ይጠየቅ ቀማሹ
ማገዶ ቢራቀቅ
ምጣድ ቢቀያየር — ጋጋሪ ቢንጋጋ
በቀማሽ ልክ ነው —የገበታሽ ዋጋ
* * *
ኧረ ሚዛን! ሚዛን!
ኧረ መዛኝ! መዛኝ!
በልክ የሚሰፍር በልክ የሚገዛኝ!
እንደየቃናችን — ማድመቅ ያላወቀ
ቀማሽ አሳነሰን — እያደባለቀ!!!
====||====

@getem
@getem
@peppa1

(በገጣሚ #በረከት #በላይነህ)
👍1
#እምዬ #ያልታደለች

(በገጣሚ #በረከት #በላይነህ )

እምዬ ያልታደለች
ተመዘኚ ሲሏት ~ መዛኝ ነኝ ትላለች
እምዬ ሰከረች
ልትመዘን ወጥታ ~ መዛኝ ሆና ቀረች!

የቅቤን ስብራት ~ በቅመም ለማከም
በወቀጣ መዛል ~ በድለዛ መድከም
የቅቤን ወለምታ ~ በቅመም ለማሸት
ሲደቁሱ አድረው ~ ሲቀይጡ ማምሸት
የቅቤን ጉብዝና ~ በቅመም ለማትጋት
እያመሱ መዋል ~ እየፈጩ ማንጋት
* * *
ይልቅ ግድ የለሽም !
ለቅቤ ጥፍጥና
ለቅቤ መአዛ
ቅመም ከመደቆስ ~ ቅመም ከማበጠር
ከቅቤያችን በፊት ~ ከብቶቹን ነው ማንጠር
እንስራ ወዝውዞ
በጢሳጢስ ናውዞ
ለቅቤ ከማማጥ ~ ለአይብ ከማማጥ
ከወተቱ በፊት ~ እስቲ ላሟ ትናጥ
ማለቢያ ከማስፋት ~ ማለቢያ ከማጥበብ
ከግቷ አስቀድሞ
ከሆዷ አስቀድሞ ~ ምግቧን ነው ማጠብ
* * *
ለምሽቱ ድምቀት — ቀኑን ሳይበርዙ
እንዲህ ነው ፊተኞች — ‘ሩቅ የሚጓዙ
እንዲህ ነው መስማማት — መግባባት ከዛፉ
ከስር ሳይመትሩ — አይታይም ጫፉ !
* * *
ግራ ነኝ ይለኛል
ቀኝ ነኝ ይለኛል —መሀል ነኝ ይለኛል
ዳሩ ካልተያዘ — መሀል የት ይገኛል?
እውቀት አባ አያልቄ
እውቀት አባ አይፈሬ — ጥያቄ ሲያድለው
ለግራም የራሱ — ግራና ቀኝ አለው
ለቀኝም የራሱ — ቀኝና ግራ አለው
መሃልም ለራሱ — ሌላ መሀል አለው
* * *
እይዉ!
ሰው መጠየቅ ትቷል
ሰው ፍለጋ ትቷል ~ ሰው ማጣጣም ትቷል
ለመንስኤ ዝሏል ~ ለአመክንዮ ታክቷል
በጥድፊያ ሊያስታግስ~የመሰንበት ሱሱን
ጥያቄ ነው ይላል ~ የከሸፈ መልሱን
ነፍስያን ተብትቦ —በስሜት ሰንሰለት
መቀያየጥ ሆኗል —መጠያየቅ ማለት
መመሳሰል ሆኗል —መመላለስ ማለት
* * *
ኩሬ ነው?
ወንዝ ነው?
ሃይቅ ነው?
ባህር ነው? ጎርፍ ነው?
ገባሩ? ጅረቱ? ማእበሉ? ምንጮቹ?
አዞ አለ? አሳ አለ?
.
.
.
እኮ የምን ጥያቄ ! ~ እኮ የምን ክርክር !
በቃ!
“ዋና ነው!” ይልሽና ~ ከነልብሱ ንክር።
አዎ!
“ዋና ነው!” ይልሻል ~ “አጨብጭቢ!” ይልሻል
“ዋናህስ?” አትበይው
አሽሟጠጠች ብሎ ~ ችሎት ያቆምሻል
ያው!
ችሎቱ የእነሱ — ችሎታው የሌላ
ይልቅ አጨብጭቢ —አዞ እራቱን ይብላ!
ለንክር ጭብጨባ —ለዝፍዝፍ ጭብጨባ
ሆዱ አሳ ሲለው — አዞ ለሚያረባ
* * *
ተመልከች!
ሽንቁራም እውቀትሽ —ንፋሱን ሲነዛ
ከጋላቢሽ ይልቅ —የሚገለብ በዛ
ንፋሳም እውቀትሽ —ውርጩን እየነዛ
ከሚያነደው ይልቅ —የሚያከስለው በዛ
ግልብልብ እውቀትሽ —ወላፈን ደሞዙ
የሚለበለቡት — ከሚበስሉት በዙ።
እይው!
ማእዘን አፍርሶ —ግድግዳ እያደሰ
ወለሉን ሰውቶ —ጣሪያ እየቀለሰ
ቅርንጫፍ ሊያሳምር —ስር እየበጠሰ
እልፍኝ ተደፈረ —አጥር ተገሰሰ
መስማት ጥንቡን —ጣለ ማየት ረከሰ
ቋንቋ መነመነ — ለትርጉም አነሰ
* * *
ቆይ እኔ የምልሽ!
ተፈጥሮ ሂደቷ — እንዲህ ሳይጓደል
ለመሮጥ መንደርደር — ግድ ነበር አይደል?!
ታዲያ! ቀረ እኮ ነው ‘ምልሽ
መንደርደር መመርመር መፈከር መዘርዘር
አኩርፈው የሄዱት — በየት በኩል ነበር?
* * *
የወል ቀማሽ ሁላ
ድፍርስ እየጠጣ — ሽርክት እየበላ
በግርድፍ አኝኮ — ለግርድፍ ተሻምቶ
“ውጫለሁ!” ይልሻል — ወደ ሆዱ ተፍቶ
* * *
የምር ደስ አይልም!
የጥርስን በአንጀት
የጆሮን በምላስ — ʻያፍንጫን በመዳፍ
ግብር እያቀማሙ — ዋጋና ስም መጻፍ
የምር ደስ አይልም!
የልብን ደረት ላይ
የነፍስን ልብስ ላይ— ቀያይጦ በማፍካት
ጣእምን መመርመር — ውበትን መለካት
ደስስስስስ አይልም!
* * *
እምዬ!
አትላፊ አትዳሪ ከእንክርዳድሽ
ይልቅ
ወንፊት ግዢ ለወንፊትሽ
ሰፌድ ግዢ ለሰፌድሽ
* * *
ቀማሽ ሲደራረብ —ጣእም ተቀያየጠ
ባለቤት ሳያጌጥ —ውበት አመለጠ
ከእህሉም አይደለ
ከቅመሙም አይደል
ጨው አንሶም አይደለ
የምላስ ህመም —ነው ጣእም የገደለ
* * *
ምን አረገሽና!
ቀቃዩ ጠባሹ
ከታፊው አማሹ
ወቃጩ ነስናሹ
ለርካሽነትሽ — ይጠየቅ ቀማሹ
ማገዶ ቢራቀቅ
ምጣድ ቢቀያየር — ጋጋሪ ቢንጋጋ
በቀማሽ ልክ ነው —የገበታሽ ዋጋ
* * *
ኧረ ሚዛን! ሚዛን!
ኧረ መዛኝ! መዛኝ!
በልክ የሚሰፍር በልክ የሚገዛኝ!
እንደየቃናችን — ማድመቅ ያላወቀ
ቀማሽ አሳነሰን — እያደባለቀ!!!

©በረከት በላይነህ
@getem
@getem
@getem
👍4