#ሳይጠፋ_ሰዋሰው
#አሌክስ_ይህ ©
.
.
ያለማመድሽኝን ፥ ‘የሞኝነት’ ፥ ኣለም
ለምጄ ፥ መታደም ፥ ለምጄ ፥ መሳለም
መሽቶ ፥ ሌሊት ፥ ሆኖ
ጀንበር ፥ ጠልቃ ፥ ማታ
ስጠብቅሽ ፥ ኣደርኩ ፥ ካልቀጠርኩሽ ፥ ቦታ
.
.
ማረፍ ፥ እንኳን ፥ ኣልችል !
ያውቀኛል ፥ ጎዳናው
ለመተው ፥ ኣይመች
ይሰማኛል ፥ ዳናው
የሚያውቀኝ ፥ መሬቱ ፥ ካንቺ ፥ የሚያደርሰኝ
እረፍት ፥ ይነሳኛል ፥ ስትራመጂበት ፥ እየቀሰቀሰኝ
.
.
የመጣሽ ፥ ሲመስለኝ !
ድምፅሽን ፥ ስሰማ ፥ እንደ ፥ ኩራዝ ፥ በራሁ
እንደ ፥ በልግ ፥ ምድር ፥ በኣበባ ፥ ተሰራሁ
‘ስትጠፊ’ ደግሞ !
እንኳን ፥ እኔን ፥ ቀርቶ ፥ መንገዱን ፥ ኣመመው
በረገጥሽው ፥ ቁጥር ፥ እግርሽን ፥ የሳመው
እስኪ ልለምነሽ . . .
በዓይኖችሽ ፥ ኣማልዕክት
በእግሮችሽ ፥ ታምራት
ዘላለም ፥ የሚጥም ፥ ኣሳሳም ፥ ስመሽኝ
ወዪ ፥ ኣልተበተንኩኝ ፥ ወዪ ፥ ኣልሰበሰብሽኝ
ሳይጠፋ ፥ ሰዋሰው ፥ የሚወደድ ፥ ባ`ገር
እሽ ፥ ምን ፥ ይባላል ?
ቃል ፥ ኣለመተንፈስ ፥ ቃል ፥ ኣለመናገር ?
.
.
ይ ሔ ው _ ነ ው _ እ ን ግ ዲ ህ !
.
.
ከውል ፥ ከተፈጥሮ !
ጉዳይ ፥ ኣለኝ ፥ እና
በርሽን ፥ ላንኳኳ ፥ መጣሁ ፥ ደግሞ ፥ ሲመሽ
እስኪ ፥ ወደ ፥ መኖር ፥ መልሽኝ ፥ ደጋግመሽ
@getem
@getem
@getem
#አሌክስ_ይህ ©
.
.
ያለማመድሽኝን ፥ ‘የሞኝነት’ ፥ ኣለም
ለምጄ ፥ መታደም ፥ ለምጄ ፥ መሳለም
መሽቶ ፥ ሌሊት ፥ ሆኖ
ጀንበር ፥ ጠልቃ ፥ ማታ
ስጠብቅሽ ፥ ኣደርኩ ፥ ካልቀጠርኩሽ ፥ ቦታ
.
.
ማረፍ ፥ እንኳን ፥ ኣልችል !
ያውቀኛል ፥ ጎዳናው
ለመተው ፥ ኣይመች
ይሰማኛል ፥ ዳናው
የሚያውቀኝ ፥ መሬቱ ፥ ካንቺ ፥ የሚያደርሰኝ
እረፍት ፥ ይነሳኛል ፥ ስትራመጂበት ፥ እየቀሰቀሰኝ
.
.
የመጣሽ ፥ ሲመስለኝ !
ድምፅሽን ፥ ስሰማ ፥ እንደ ፥ ኩራዝ ፥ በራሁ
እንደ ፥ በልግ ፥ ምድር ፥ በኣበባ ፥ ተሰራሁ
‘ስትጠፊ’ ደግሞ !
እንኳን ፥ እኔን ፥ ቀርቶ ፥ መንገዱን ፥ ኣመመው
በረገጥሽው ፥ ቁጥር ፥ እግርሽን ፥ የሳመው
እስኪ ልለምነሽ . . .
በዓይኖችሽ ፥ ኣማልዕክት
በእግሮችሽ ፥ ታምራት
ዎ ድ ሻ ለ ሑ ና
‘ትመጣለች’ ፥ ብዬ ፥ ለነፍሴ ፥ ልንገራት !
.
.
ኧ ረ _ የ ኣ
ን ቺ ስ _ ለ ጉ ድ _ ነ ው !ዘላለም ፥ የሚጥም ፥ ኣሳሳም ፥ ስመሽኝ
ወዪ ፥ ኣልተበተንኩኝ ፥ ወዪ ፥ ኣልሰበሰብሽኝ
ሳይጠፋ ፥ ሰዋሰው ፥ የሚወደድ ፥ ባ`ገር
እሽ ፥ ምን ፥ ይባላል ?
ቃል ፥ ኣለመተንፈስ ፥ ቃል ፥ ኣለመናገር ?
.
.
ይ ሔ ው _ ነ ው _ እ ን ግ ዲ ህ !
.
.
ከውል ፥ ከተፈጥሮ !
ጉዳይ ፥ ኣለኝ ፥ እና
በርሽን ፥ ላንኳኳ ፥ መጣሁ ፥ ደግሞ ፥ ሲመሽ
እስኪ ፥ ወደ ፥ መኖር ፥ መልሽኝ ፥ ደጋግመሽ
@getem
@getem
@getem