ቀናሁ
=== ===
ለመንኩት አምላክን
አበባ እንዲያደርግሽ
ንብ ሆኜ መጥቼ
እየዞርኩ ልቀስምሽ
ማለዳ ማለዳ
በበራፋችሁ ሳልፍ
ብመለከት ጊዜ
ፀሀይ ስትሞቂ
ፈጣሪን ለመንኩት
"ፀሀይ አርገኝ "ብዬ
ውብ #ሠውነትሽ ላይ
እንዳርፍ ዘና ብዬ፡፡
ያንገትሽ #ማተብ
ያለ ማንም ከልካይ
ገብቶ ሲንከላወስ
በጡቶችሽ ክፋይ
ብመለከት ጊዜ...
ቀናሁ በማተብሽ
ቀናው በመስቀሉ
ጡትሽን ተንተርሶ
በመዋል በማደሩ፡፡
#ቅዳሜ እረፋድ ላይ
ስትመጭ ከገበያ....
ትኩስ ለጋ ጎመን
በክንድሽ ታቅፈሽ
በሌላኛው እጅሽ
ዘንቢል አንጠልጥለሽ..
ብመለከት ጊዜ...
እንደ ጎመን መሆን
ተመኘው ለቅፅበት
በአካሌ እንዲሠራጭ
የአክናድሽ ሙቀት
ተመኘው ለቅፅበት
መሆን እንደ ዘንቢል
ውብ ለሥላሳ ጣትሽ
በገላዬ እንዲውል፡፡
ትናንትና ደግሞ..
ከኛ ቤት ፊት ለፊት
ውሐ ስትቀጂ
ከየት እንደ መጣ
ያልታወቀ ንፋስ
ቀሚስሽን ገልቦ
ጀምበር የመሠለ
ያ ውቡ ጭንሽን
ቢያሳየኝ በስሱ
እምልልሻለው
ቀናሁ በንፋሱ፡፡
doju.
@getem
@getem
@getem
=== ===
ለመንኩት አምላክን
አበባ እንዲያደርግሽ
ንብ ሆኜ መጥቼ
እየዞርኩ ልቀስምሽ
ማለዳ ማለዳ
በበራፋችሁ ሳልፍ
ብመለከት ጊዜ
ፀሀይ ስትሞቂ
ፈጣሪን ለመንኩት
"ፀሀይ አርገኝ "ብዬ
ውብ #ሠውነትሽ ላይ
እንዳርፍ ዘና ብዬ፡፡
ያንገትሽ #ማተብ
ያለ ማንም ከልካይ
ገብቶ ሲንከላወስ
በጡቶችሽ ክፋይ
ብመለከት ጊዜ...
ቀናሁ በማተብሽ
ቀናው በመስቀሉ
ጡትሽን ተንተርሶ
በመዋል በማደሩ፡፡
#ቅዳሜ እረፋድ ላይ
ስትመጭ ከገበያ....
ትኩስ ለጋ ጎመን
በክንድሽ ታቅፈሽ
በሌላኛው እጅሽ
ዘንቢል አንጠልጥለሽ..
ብመለከት ጊዜ...
እንደ ጎመን መሆን
ተመኘው ለቅፅበት
በአካሌ እንዲሠራጭ
የአክናድሽ ሙቀት
ተመኘው ለቅፅበት
መሆን እንደ ዘንቢል
ውብ ለሥላሳ ጣትሽ
በገላዬ እንዲውል፡፡
ትናንትና ደግሞ..
ከኛ ቤት ፊት ለፊት
ውሐ ስትቀጂ
ከየት እንደ መጣ
ያልታወቀ ንፋስ
ቀሚስሽን ገልቦ
ጀምበር የመሠለ
ያ ውቡ ጭንሽን
ቢያሳየኝ በስሱ
እምልልሻለው
ቀናሁ በንፋሱ፡፡
doju.
@getem
@getem
@getem
😁1