ግጥም ብቻ 📘
67.6K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#ዘላለም_ለመኖር ’ ፪

#አሌክስ_ይህ
.
ዘመናት ኣልፈዋል !
...
መስታዎት ኣንስታ _ ፊቷ ደቀነችው
የራሷን ኣምሳያ
በዓይኗ እየተቆጣች
ደጋግማ ታዘበች _ ደጋግማ ቃኘችው
...
ሁሉም ተቀይሯል
ጊዜ የሄደበት ...
ዘመን ያረፈበት
የግንባሯ ፀዳል _ ከቦታው ተንዶ
‘እንደ ፈርጥ ያበራል’
የተባለለቱ _ የዓይኗ ውበት ወርዶ
ኣየችው ደጋግማ _ ቃኘችው ተገርማ
የትናንቱን ገጿን _ ራሷን ፍለጋ በትዝታ ሰጥማ
...
በኣለማመን መንፈስ
በጊዜ ምንነት _ ሃሳብ ተወጥራ
ምስሏን ቃኘቸው
ከትናንት የሌለ
ከዛሬም ያልሆነ _ ኣዲስ ዓለም ፈጥራ
...
ከ‘ነበር’ በስተቀር
የእርሷ ማንነት _ ተቀይሯል ሁሉም
በረዶ ጥርሶቿ
እንኮይ ከንፈሮቿ _ ከቦታቸው የሉም
ኣየችው ደጋግማ _ ቃኘችው ተገርማ
መልኳን እንደ በላው
ጊዜ እየበረረ _ ዘመን እየሮጠ
ቀስስስ.... እያለ ገባት
የጊዜ ሌብነት _ የስጋ ከንቱነት እየተገለጠ
...
መስታወቷን ኣቅፋ !
ወደ ላይ እያየች
እንደ እሳት ሲፈጃት _ ትዝታ ገንፍሎ
የድሮ ፎቶዋን _ ስ`ርቅ ኣርጋ ኣየችው
ከቤቷ ግድግዳ _ ኮርና ላይ ተሰቅሎ
...
ኣየችው ደጋግማ _ ቃኘችው ተገርማ
ነፍስ እና ስጋዋ
በሃሳብ ተወግተው _ እንደ ደነዘዙ
የሟሸሹ ዓይኖቿ _ በእንባ እየወረዙ
ኣየችው ደጋግማ _ ቃኘችው ተገርማ
ዘመን እያለፈች ...
ከፍታ እየወጣች _ በሃሳብ መሰላል
ፎቶዋን ስታየው
#መልካምነት’ እንጂ
‘ሁሉም ኣላፊ ነው’ _ የሚላት ይመስላል !
...
እናም ኣለሜ ሆይ !
‘ዘላለም’ ለመኖር
በይ ስምሽን ቀቢው
መዓዛው የማይነጥፍ _ ከርቤና ሉባንጃ
ለዓይን እና ለጥርስሽ
‘ጊዜ’ የሚሉት ክንፍ _ ኣለው መጋረጃ

@getem
@getem
@getem