ግጥም ብቻ 📘
67.6K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#ዝም_ያለ_መሸታ

#አብርሀም_ተክሉ ( #መርዕድ)

የተጋባ ዋንጫ
ተደቅኖ ፊትሽ ፥ ጠላሽን ስጠማ
ቦለቲካው ይዞሽ
በሆዴ አመሀኝተሽ ፥ ጆሮዬ ሲደማ
በሰዎች ቋምጬ ፥ በዋጥኩት አረፋ
ከሳባ ጀምሮ
የነገርሽኝ ታሪክ ፥ በኔ ዘመን ጠፋ ።
ኧ........ረ #ቅጅልኝ !!
#ሆ !!......
እገሌ....... እንዲህ አደረገ
እገሌ........ ይህን አመጣ
በዚያን ዘመን ........የተገፋ
በዚህ ግዜ........ ቀኑ ወጣ
ይሄኛው ለሾርኒ ፥ ለቧልት ተቆጣ
ይህኛው ደንገጡር ፥ ጭን-ገረድ አወጣ
#የኔ_ዘር ....
#ያንተ_ዘር...
ይህን አወደመ
ይህን አመረተ
አትበይኝ ................ #ወ_ዘ_ተ
በሄድኩበት ሁሉ
ዘር ሽሉ እያደገ ፥ ወላድ እየሞተ
ቅርናት ቅርናት ቃና ፥ ሀገር እሳት ገብታ ፥ ስለተሻተተ
ልጠጣነው የመጣሁ...
እራሴን ልረሳ
የጆሮዬን ቅርሚያ ፥ ሳይወድል ላከሳ
ዝ.........ም ብለሽ ቅጅልኝ
ዝ..........ም ብዬ ልጠጣ
ለመሳም ካልሆነ በቀር
ከንፈርሽ አይንቀላወስ ፥ ምላስሽ ጉልበት አያውጣ።

@Abr_sh

@getem
@getem
@GETEM