ግጥም ብቻ 📘
67.3K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
👆👆👆👆👆
#የነፍስ_ከፍታ

ሱርማ ነው !! ይሉኛል
ባለ ቀጭን ጨንገር
ባለ ረጅም በትር
ቆዳ እያቀለመ
ከንፈር የሚመትር
የመተጫጫ ቀን
አቅሙ ሊፈተን ፥ ጉልበቱ ሊለካ
ዘጠኝ ከብት ላይ
ፈጥኖ ተረማምዶ ፥ መሬት የሚነካ።
ታዲያ ለምን ቦቃ ?
ምን ይሉታል #ቡሬ ?
እንዲህ መስፈንጠሩ
ውሻ ጮሆ ብታይ ፥ ስርፋ መቀየሩ
ለማረስ የሰራው ፥ ሻኛና ትከሻ
ነፃ ለመውጣቱ ፥ ከፍርሀቱ ዋሻ
ቀንድክ ሆኖ ጨሬ
ራስህ ሆኖ ጋሻ
ይሄ #ሁሉ !! ዝላይ
ከቶ ለምን አሻ ?

#አብርሀም_ተክሉ

@getem
@getem
@getem