#ይብቃሽ~እታለሜ
፡
ሀገር እያላቸው ኑሮን ለማሸነፍ በሰው ሀገር
ከሰው በታች ሆነው ለሚኖሩ እህቶቻችን መታሰቢያነት የተፃፈ፡፡ ይሄ ከላይ ያለው ፎቶ የኑሯቸውን መራርነት ስለሚያሳኝ ሁሌም ባየሁት ቁጥር ልቤን እያደማ ግጥም ያፅፈኛል፡፡ እንሆ ዛሬም ይህን ቋጠርኩ፡፡
፡
ድህነትን ሽሽት
ለባዕድ ግርድና ማንነት ሲበተን
ከ'ናት ጎጆ ርቆ
በሰቀቀን ድካም ሴትነት ሲፈተን
ከባህሩ ማዶ
አድማሱን ተሻግሮ ባንቺ እየታየኝ
ኑሮሽን ሳስበው
በማይድን ስብራት ህመም አሰቃየኝ፡፡
፡
ህልም አለሽ አውቃለሁ
ከባርነት አልጋ ተኝተሽ ያለምሽው
ለዚህ ነው እህቴ
ኑሮሽን ለመጣል ቆመሽ የተኛሽው፡፡
እንጂማ ሳይታክት
የማዳምን ቁጣ ገላሽ ተሸክሞ
ከ'ናት ቤት የራቀ
መከረኛ ልብሽ ባ'ገር ናቆት ታሞ
ሰርክ እያሰቀቀ
በባዕዳን አለም እንባሽን ሲያፈሰው
ለምን ትይው ነበር
ሀገር አለሽና አንቺም ልክ እንደሰው፡፡
፡
ግና ጊዜ ጥሎሽ
እንደ እድሜ እኩዮችሽ ለመኖር ሳትጓጊ
ላ'ፈር ገፊ አባትሽ
ለእናትሽ ሀዘን ደስታን ልትፈልጊ
የኸው በሰው ሀገር
ስትንከራተቺ በጊዜ ሀዲድ ላይ ሰርክ እየከነፉ
ከመከራሽ ጋራ
መታገል ሳይበቃሽ አመታት አለፉ፡፡
፡
ነይልን አለሜ
ይብቃሽ መታገሉ
ክንድሽ እየዛለ እኛን አታበርቺን
አልቅሰሽ አንስቅም
ለደሀ ጎጆአችን
ማግኘት ምን ያደርጋል እያሳጣን አንቺን?
(((ልብ አልባው ገጣሚ)))
@getem
@getem
@getem
፡
ሀገር እያላቸው ኑሮን ለማሸነፍ በሰው ሀገር
ከሰው በታች ሆነው ለሚኖሩ እህቶቻችን መታሰቢያነት የተፃፈ፡፡ ይሄ ከላይ ያለው ፎቶ የኑሯቸውን መራርነት ስለሚያሳኝ ሁሌም ባየሁት ቁጥር ልቤን እያደማ ግጥም ያፅፈኛል፡፡ እንሆ ዛሬም ይህን ቋጠርኩ፡፡
፡
ድህነትን ሽሽት
ለባዕድ ግርድና ማንነት ሲበተን
ከ'ናት ጎጆ ርቆ
በሰቀቀን ድካም ሴትነት ሲፈተን
ከባህሩ ማዶ
አድማሱን ተሻግሮ ባንቺ እየታየኝ
ኑሮሽን ሳስበው
በማይድን ስብራት ህመም አሰቃየኝ፡፡
፡
ህልም አለሽ አውቃለሁ
ከባርነት አልጋ ተኝተሽ ያለምሽው
ለዚህ ነው እህቴ
ኑሮሽን ለመጣል ቆመሽ የተኛሽው፡፡
እንጂማ ሳይታክት
የማዳምን ቁጣ ገላሽ ተሸክሞ
ከ'ናት ቤት የራቀ
መከረኛ ልብሽ ባ'ገር ናቆት ታሞ
ሰርክ እያሰቀቀ
በባዕዳን አለም እንባሽን ሲያፈሰው
ለምን ትይው ነበር
ሀገር አለሽና አንቺም ልክ እንደሰው፡፡
፡
ግና ጊዜ ጥሎሽ
እንደ እድሜ እኩዮችሽ ለመኖር ሳትጓጊ
ላ'ፈር ገፊ አባትሽ
ለእናትሽ ሀዘን ደስታን ልትፈልጊ
የኸው በሰው ሀገር
ስትንከራተቺ በጊዜ ሀዲድ ላይ ሰርክ እየከነፉ
ከመከራሽ ጋራ
መታገል ሳይበቃሽ አመታት አለፉ፡፡
፡
ነይልን አለሜ
ይብቃሽ መታገሉ
ክንድሽ እየዛለ እኛን አታበርቺን
አልቅሰሽ አንስቅም
ለደሀ ጎጆአችን
ማግኘት ምን ያደርጋል እያሳጣን አንቺን?
(((ልብ አልባው ገጣሚ)))
@getem
@getem
@getem
❤1
#አዎ ~ባላ'ገር~ነህ!!!
፡
የደመናን እንባ
የናፈቁ አይኖችህ
ሽቅብ ወደ ሰማይ ዘውትር ሲዋትቱ
ከደረቀ መሬት
ትግል የገጠሙ
ሻካራ እጆችህ ሞፈር ሲጎትቱ
ከበሬ ተጣምደህ
አፈር ስትገፋ ቀንበር ስትሸከም
ያኔ ነው የገባኝ
የህይወትህ ምሬት ለኔ ያንተ መድከም፡፡
፡
ግና ከተሜው ሰው
የባላገር ትርጉም ያልገባው ምፃጉ
ለስም አልባ ስሙ
መሆንህን እረስቶ ክብርና ማረጉ
አርሰህ ባጎረስከው
ውለታቢስ ሆዱ ለባእዳን ሰግዶ
ባላገር ይልሀል
በመዘመን ብሂል እርሱ ሀገሩን ክዶ፡፡
፡
አዎ ባላ'ገር ነህ
ሀገር ስላለህ ነው ባላ'ገር ምትባል
እውነትም ይሄ ስም
ከማንም በላቀ ለክብርህ ይገባል፡፡
፡
ስለዚህ ለነሱ
ለከተሜው ጭሶች ባላገር ለናቁ
ሀገር እያላቸው
ሀገር አልባ ሆነው ሀገር ለናፈቁ
ባላ'ገር ነህና
ይበሉህ ባላገር ሀገርን እስኪያውቁ፡፡
((ልብ አልባው ገጣሚ))
@getem
@getem
@getem
፡
የደመናን እንባ
የናፈቁ አይኖችህ
ሽቅብ ወደ ሰማይ ዘውትር ሲዋትቱ
ከደረቀ መሬት
ትግል የገጠሙ
ሻካራ እጆችህ ሞፈር ሲጎትቱ
ከበሬ ተጣምደህ
አፈር ስትገፋ ቀንበር ስትሸከም
ያኔ ነው የገባኝ
የህይወትህ ምሬት ለኔ ያንተ መድከም፡፡
፡
ግና ከተሜው ሰው
የባላገር ትርጉም ያልገባው ምፃጉ
ለስም አልባ ስሙ
መሆንህን እረስቶ ክብርና ማረጉ
አርሰህ ባጎረስከው
ውለታቢስ ሆዱ ለባእዳን ሰግዶ
ባላገር ይልሀል
በመዘመን ብሂል እርሱ ሀገሩን ክዶ፡፡
፡
አዎ ባላ'ገር ነህ
ሀገር ስላለህ ነው ባላ'ገር ምትባል
እውነትም ይሄ ስም
ከማንም በላቀ ለክብርህ ይገባል፡፡
፡
ስለዚህ ለነሱ
ለከተሜው ጭሶች ባላገር ለናቁ
ሀገር እያላቸው
ሀገር አልባ ሆነው ሀገር ለናፈቁ
ባላ'ገር ነህና
ይበሉህ ባላገር ሀገርን እስኪያውቁ፡፡
((ልብ አልባው ገጣሚ))
@getem
@getem
@getem
❤1👍1
ዮሃንስ ፬ ፤ ያንተም ቀን ደረሰ!
ያጎረሰውን እጅ የሚናከስ በዝቶ
የቤቱን ምሰሶ የሚጥል ጎትቶ
ባዘለው ጀርባ ላይ የሚዝት በዛና
ሰማዩንም ችሎ ላይጋርድ ደመና
ስንቱ ቂል አዝማሪ በከንቱ ዘፈነ
ስንቱ ግንዱን ትቶ ስንጥር አገነነ።
የተምቤኑ ካሳ ደመ መራራው
አስራስምንት አመት እንቅልፍ ያልተኛው
የቴድሮስን ሀገር ርስቱን ተረክቦ
ያንዲትን ኢትዮጵያ አላማ አንግቦ
ወራሪና ባንዳን ሬት እያቀመሰ
ጎንደር መተማ ላይ ደሙን አፈሰሰ።
ሀገሩን ያልሸጠ ለነጭ ያልዘመረ
የሀበሻን ድንበር ባንገቱ ያጠረ
ዮሃንስ ራብዓይ ንጉሠ ነገስት
የሀገር ጠባቂ ያበሻ አባት።
ምን ትል ነበር ይሆን ብታይ ቀና ብለህ
በእምዬ ውጫሌ ስትሸጥ ርስትህ
የሓማሴን ጌታ ፣ ያካለ ጉዛይ
የምፅዋ አምበሳ የአረብ ገዳይ
አንተ ግብፃ-ግብፁን ካንድም ሁለት ሶስቴ ባትዘርረውማ
አባይና አገሬው ማተቡን ባስቀማ።
አንተ መሃዲስቱን ጀሃዱን ቀልብሰህ ባታረገው ውሻ
ምን ይሆን ነበረ የኛ መጨረሻ?
ካሳ ካንተ ኋላ ሀገሬን ከፍቷቷል
ያክሱሙ ሃውልትም ከአዱሊስ ተጣልቷል።
ባገር ምስረታ ስም ብዙ ግፍ ተሰርቷል
ወዲ ጅግና ካሳ ስምህም ተረስቷል።
እውነት ግን ለወትሮው አይጠፋንምና
ከሰማይ ሲገፈፍ ጥቁሩ ደመና
የትግራይ ልጅ ካሳ ስምህ ይነሳሳል
ኢትዮጵያዊ ሁሉ እውነቱን ይረዳል።
ቀይና ቢጫውን አረንጓዴውን
አንተእንደጀመርከው ስንቱ ያውቅ ይሆን?
ለሙስሉሙ ህዝብህ ያልነጃሺን መሬት አራት እጥፍ አርገህ እንደሸላለምከው
አዝማሪዎች ቀጥረህ ምነው ባዘፈንከው።
የመይሳው ካሳ በጠጣው ጥይት
የተምቤኑ ካሳ በሰጠው አንገት
በትግራይ በሸዋ በጎንደር ኤርትራ
በስንቱ ደም አጥንት ፀንታ የምትኮራ
በውቧ ሀገርህ በጥንታዊ ርስትህ
ባንዳና ሰላቶ ባዝማሪ መሰንቆ ሲወደስ ዋለልህ
የሀገሩን መሬት ከህዝቡ ጋር አርጎ
ለጣልያን የሸጠ ለፒዛና ለእርጎ
ዳግም ላያቅራራ ባንተ ስራ ወዝቶ
በእውቀት የታጠቀ ነቄ ትውልድ መጥቶ
ታሪክህ ሊታደስ ቅኔ እየፈሰሰ
የቀይ ባህሩ ጀግና ያንተ ቀን ደረሰ!
ገጣሚ Utopiawi
🌞🌍🌙
🇪🇹🇪🇷
@getem
@getem
@getem
ያጎረሰውን እጅ የሚናከስ በዝቶ
የቤቱን ምሰሶ የሚጥል ጎትቶ
ባዘለው ጀርባ ላይ የሚዝት በዛና
ሰማዩንም ችሎ ላይጋርድ ደመና
ስንቱ ቂል አዝማሪ በከንቱ ዘፈነ
ስንቱ ግንዱን ትቶ ስንጥር አገነነ።
የተምቤኑ ካሳ ደመ መራራው
አስራስምንት አመት እንቅልፍ ያልተኛው
የቴድሮስን ሀገር ርስቱን ተረክቦ
ያንዲትን ኢትዮጵያ አላማ አንግቦ
ወራሪና ባንዳን ሬት እያቀመሰ
ጎንደር መተማ ላይ ደሙን አፈሰሰ።
ሀገሩን ያልሸጠ ለነጭ ያልዘመረ
የሀበሻን ድንበር ባንገቱ ያጠረ
ዮሃንስ ራብዓይ ንጉሠ ነገስት
የሀገር ጠባቂ ያበሻ አባት።
ምን ትል ነበር ይሆን ብታይ ቀና ብለህ
በእምዬ ውጫሌ ስትሸጥ ርስትህ
የሓማሴን ጌታ ፣ ያካለ ጉዛይ
የምፅዋ አምበሳ የአረብ ገዳይ
አንተ ግብፃ-ግብፁን ካንድም ሁለት ሶስቴ ባትዘርረውማ
አባይና አገሬው ማተቡን ባስቀማ።
አንተ መሃዲስቱን ጀሃዱን ቀልብሰህ ባታረገው ውሻ
ምን ይሆን ነበረ የኛ መጨረሻ?
ካሳ ካንተ ኋላ ሀገሬን ከፍቷቷል
ያክሱሙ ሃውልትም ከአዱሊስ ተጣልቷል።
ባገር ምስረታ ስም ብዙ ግፍ ተሰርቷል
ወዲ ጅግና ካሳ ስምህም ተረስቷል።
እውነት ግን ለወትሮው አይጠፋንምና
ከሰማይ ሲገፈፍ ጥቁሩ ደመና
የትግራይ ልጅ ካሳ ስምህ ይነሳሳል
ኢትዮጵያዊ ሁሉ እውነቱን ይረዳል።
ቀይና ቢጫውን አረንጓዴውን
አንተእንደጀመርከው ስንቱ ያውቅ ይሆን?
ለሙስሉሙ ህዝብህ ያልነጃሺን መሬት አራት እጥፍ አርገህ እንደሸላለምከው
አዝማሪዎች ቀጥረህ ምነው ባዘፈንከው።
የመይሳው ካሳ በጠጣው ጥይት
የተምቤኑ ካሳ በሰጠው አንገት
በትግራይ በሸዋ በጎንደር ኤርትራ
በስንቱ ደም አጥንት ፀንታ የምትኮራ
በውቧ ሀገርህ በጥንታዊ ርስትህ
ባንዳና ሰላቶ ባዝማሪ መሰንቆ ሲወደስ ዋለልህ
የሀገሩን መሬት ከህዝቡ ጋር አርጎ
ለጣልያን የሸጠ ለፒዛና ለእርጎ
ዳግም ላያቅራራ ባንተ ስራ ወዝቶ
በእውቀት የታጠቀ ነቄ ትውልድ መጥቶ
ታሪክህ ሊታደስ ቅኔ እየፈሰሰ
የቀይ ባህሩ ጀግና ያንተ ቀን ደረሰ!
ገጣሚ Utopiawi
🌞🌍🌙
🇪🇹🇪🇷
@getem
@getem
@getem
❤1
#እመጣልሃለሁ !
~
እንዴት ነህ ወዳጄ?
የጭንቅ አማላጄ የበረሃው ሽፍታ
መች እረሳውና እኔ ያንተን ውለታ!
~
ስብሓት ይሁን ላንተ ...
ከጠላትህ ደጃፍ ታስሬ አግኝተኸኝ
በሰላም ሂድ ብለህ ፈተህ ለለቀከኝ።
~
ገፋፊ - ዘራፊ ብትሆን ነብሰ-በላ
ፅዋህ እለት-ተለት በደም ብትመላ፣ ...
ወቃሽ የለም ብዬ
ሙቀት ተከትዬ፣ ...
አልገላበጥም - አልከንፍም በወረት
ታሪክህን ክጄ - አልለውም "ተረት!!"
-
ስምክን ሳላነሳ
ሳላሞጋግስህ መሽቶም አይነጋልኝ
ሞልቶልን ሰልቶልን
ባይን እስክንተያይ አማን ያቆይልኝ።
-
ከለታት አንድ ቀን ...
ዳገት ቁልቁለቱን
ዱር ገደል ጫካውን በጽናት ተጉዤ
ከተፍ እላለሁኝ
የወግ የልማዱን እጅ መንሻ ይዤ።
-
በመሃሪነትህ
በመልካምነትህ
ሀ-ሞቴን ሳልጠጣት ካለፈች ጽዋዬ
ባንተው ፈለግ ሄጄ
እስኪ እኔም ለሌሎች ልዋል በተራዬ!
-
ማ ር ያ ም ን አልቀርም!
ከእናቴ ይነጥለኝ እውነት እልሃለሁ
መግደል ያሳበዳት
ነብስህን ልወስዳት
ስካለብ - ስጣደፍ እ መ ጣ ል ሃ ለ ሁ!!
-
እ መ ጣ ል ሃ ለ ሁ
በባህር ቀዛፊ
ባየር ተንሳፋፊ - ጦር አደራጅቼ
ሽፍታጋ'ማ ታበርኩ
መትረፌ ምን ረባ ከሙት ተለይቼ?
============//=======
( በርናባስ ከበደ )
@getem
@getem
@getem
~
እንዴት ነህ ወዳጄ?
የጭንቅ አማላጄ የበረሃው ሽፍታ
መች እረሳውና እኔ ያንተን ውለታ!
~
ስብሓት ይሁን ላንተ ...
ከጠላትህ ደጃፍ ታስሬ አግኝተኸኝ
በሰላም ሂድ ብለህ ፈተህ ለለቀከኝ።
~
ገፋፊ - ዘራፊ ብትሆን ነብሰ-በላ
ፅዋህ እለት-ተለት በደም ብትመላ፣ ...
ወቃሽ የለም ብዬ
ሙቀት ተከትዬ፣ ...
አልገላበጥም - አልከንፍም በወረት
ታሪክህን ክጄ - አልለውም "ተረት!!"
-
ስምክን ሳላነሳ
ሳላሞጋግስህ መሽቶም አይነጋልኝ
ሞልቶልን ሰልቶልን
ባይን እስክንተያይ አማን ያቆይልኝ።
-
ከለታት አንድ ቀን ...
ዳገት ቁልቁለቱን
ዱር ገደል ጫካውን በጽናት ተጉዤ
ከተፍ እላለሁኝ
የወግ የልማዱን እጅ መንሻ ይዤ።
-
በመሃሪነትህ
በመልካምነትህ
ሀ-ሞቴን ሳልጠጣት ካለፈች ጽዋዬ
ባንተው ፈለግ ሄጄ
እስኪ እኔም ለሌሎች ልዋል በተራዬ!
-
ማ ር ያ ም ን አልቀርም!
ከእናቴ ይነጥለኝ እውነት እልሃለሁ
መግደል ያሳበዳት
ነብስህን ልወስዳት
ስካለብ - ስጣደፍ እ መ ጣ ል ሃ ለ ሁ!!
-
እ መ ጣ ል ሃ ለ ሁ
በባህር ቀዛፊ
ባየር ተንሳፋፊ - ጦር አደራጅቼ
ሽፍታጋ'ማ ታበርኩ
መትረፌ ምን ረባ ከሙት ተለይቼ?
============//=======
( በርናባስ ከበደ )
@getem
@getem
@getem
ይህቺ ዘንባባ እና የፍቅር ማኅልይ የተሰኘች አጭር የልቦለድ እና የግጥም መጽሃፍ ወደ ራሳችን የምትመልሰን መንገድ እንዳላት አምናለሁ፡፡ አምኜም ይህን እመሰክራለሁ፡፡ እያንዳንዱ ጥሩ መፅሐፍ ከልባችን ጋር ያገናኘናል፡፡ በስራ ጫና፣ በሌሎች ወሬና አሉባልታ፣ በፖለቲካ እንካ ሰላንቲያ፣ በድብርት እና በመሳሰሉት ከራሳችን ተፋተን ከሆነ፤ ይህቺ መጽሃፍ ወደ ልባችን መመለሻ አቋራጭ ናትና… ከጥሩ መጽሃፎች ተርታ እመድባታለሁ፡፡
ቢንያም ገብሩ
@getem
@getem
@Gebriel_19
ቢንያም ገብሩ
@getem
@getem
@Gebriel_19
ላቻም የለሽ
አንቺን.
እንደመስከረም አስውቦ
ባደይ በፅጌ ከቦ.
እንዲያመጣልኝ.
ለቅዱስ ሚካኤል ሥለት አለብኝ፡፡
እናማ ቅዱሱ.
አይቀርምና መንገሱ
ጥላ ይዤ ላስጠልለው.
ዘቢብ ዕጣን ላቀብለው
በግርማ ድባብ ከብቤ.
በጧፍ ጠሎት ጠብሼ
ስባሄ መዝሙር ላበላው.
የፊታችን ህዳር ባመትሽ
ሚኪያል ከኔ ቀጠሮ አለው፡፡
ደረሰልሽ፡፡
ህዳር ጠባ.
ኦና ልቤ ውበት ገባ፡፡
አንቺ መጣሽ.
(ጠጠር መጣያ እስከሚጠፋ)
ነፍሴን ሞላሽ፡፡
ታድያ በማግስቱ…
የመቅሰፍት መአት ሆነ፡፡
ሚካኤል ተቆጣ፡፡
ከሰጠሁት ከርቤ.
ከሰጠሁት ሽቱ.
ከሰጠሁት ዘቢብ.
ካስጠለልኩት ድባብ
የሚስተካከልሽ. አንድ እንኳ ቢያጣ
እሷን ስጠኝ አለኝ
አንቺን ስላመጣ፡፡
(ወላሂ!! ቢሳልሽም አልሰጠው፡፡)
።ዘንባባ ከተሰኘችው መፅሀፍ የተወሰደ።
(ምግባር ሲራጅ)
@getem
@getem
@getem
አንቺን.
እንደመስከረም አስውቦ
ባደይ በፅጌ ከቦ.
እንዲያመጣልኝ.
ለቅዱስ ሚካኤል ሥለት አለብኝ፡፡
እናማ ቅዱሱ.
አይቀርምና መንገሱ
ጥላ ይዤ ላስጠልለው.
ዘቢብ ዕጣን ላቀብለው
በግርማ ድባብ ከብቤ.
በጧፍ ጠሎት ጠብሼ
ስባሄ መዝሙር ላበላው.
የፊታችን ህዳር ባመትሽ
ሚኪያል ከኔ ቀጠሮ አለው፡፡
ደረሰልሽ፡፡
ህዳር ጠባ.
ኦና ልቤ ውበት ገባ፡፡
አንቺ መጣሽ.
(ጠጠር መጣያ እስከሚጠፋ)
ነፍሴን ሞላሽ፡፡
ታድያ በማግስቱ…
የመቅሰፍት መአት ሆነ፡፡
ሚካኤል ተቆጣ፡፡
ከሰጠሁት ከርቤ.
ከሰጠሁት ሽቱ.
ከሰጠሁት ዘቢብ.
ካስጠለልኩት ድባብ
የሚስተካከልሽ. አንድ እንኳ ቢያጣ
እሷን ስጠኝ አለኝ
አንቺን ስላመጣ፡፡
(ወላሂ!! ቢሳልሽም አልሰጠው፡፡)
።ዘንባባ ከተሰኘችው መፅሀፍ የተወሰደ።
(ምግባር ሲራጅ)
@getem
@getem
@getem
የጀግና ሀገር ግጥም
*
ሁሉ ነገር ደም ነው~ የጀግና ሀገር ውሎ
ውበት እንኳ ሲያደንቅ~ የደም ገንቦ ብሎ
ደሙ ነው ሚታየው ~ከ አካሏ ነጥሎ።
*
የፍቅር ጥልቀቱን
ለሀገሩ የዋለውን ~ለሚወዳት ሲገልጽ
ደሜን አፍስሼ ነው ~ ከልብሽ የምሰርጽ።
*
እያለ ስኬቱን ~ በደም እየሳለ
ጥርጣሬ እንዳይኖር ~በደም እየማለ
*
አመታት ሲነጉዱ ~እለታት ሲርቁ
ደምን የሚሰጡት ~ምንጮቹ ሲደርቁ
ድል መንሳት ሲያቅተው~ ሽንፈቱን ሲያጣጥም
ደመ ከልብ ይሆናል ~ የጀግና ሀገር ግጥም።
*
*
እሱባለው Ethiopian
@getem
@getem
@getem
*
ሁሉ ነገር ደም ነው~ የጀግና ሀገር ውሎ
ውበት እንኳ ሲያደንቅ~ የደም ገንቦ ብሎ
ደሙ ነው ሚታየው ~ከ አካሏ ነጥሎ።
*
የፍቅር ጥልቀቱን
ለሀገሩ የዋለውን ~ለሚወዳት ሲገልጽ
ደሜን አፍስሼ ነው ~ ከልብሽ የምሰርጽ።
*
እያለ ስኬቱን ~ በደም እየሳለ
ጥርጣሬ እንዳይኖር ~በደም እየማለ
*
አመታት ሲነጉዱ ~እለታት ሲርቁ
ደምን የሚሰጡት ~ምንጮቹ ሲደርቁ
ድል መንሳት ሲያቅተው~ ሽንፈቱን ሲያጣጥም
ደመ ከልብ ይሆናል ~ የጀግና ሀገር ግጥም።
*
*
እሱባለው Ethiopian
@getem
@getem
@getem
👍1
#አላምንም!
እስኪ ተጠየቁ...!
-
የዝንጀሮ መልኳ አስቀያሚ እንደሆን
በልሳን ብ'ነግራት ትደነግጥ ይሆን?
-
ስናወራ ሰምታ - ወፍ እንደምታምር
ፉጨቷን አቋርጣ - ትለን ይሆን "የምር??"
-
እህሳ?!.....
ታድያ የት ተለከፍን? ምን ነክቶን ነው እኛ?
ስለ አቋም መልካችን ...
እንዴት ባለው ልኬት - ሆንን እርግጠኛ??
.
የቱ ቡዳ በላን?
ምን ቀን ሰፈረብን? ተያዝን በመንፈስ
ለምን ተጠመድን?
ስለራስ በማዜም - ስለራስ በማልቀስ።
.
ቢያማልል ....
ቢያባብል...
ማር ቢሆን ቢጣፍጥ - ነገር በምሳሌ
ባለማመን የማምን -
ተጠራጣሪ ነኝ - እኔ በበኩሌ።
-
-
"ሔዋን እንደዚ ነች!"
"አዳም እንደዚ ነው!"
የሚል ጥቅስ ቢናኝ - አየሩን ቢሞላ
ማንንም አላምንም - ከእንግዲህ በኋላ!!
.
በቃ አላምንም ከቶ፣
ግርምቱን - ትዝብቱን ሳይጨምር - ሳያስቀር
"ሰው እንዲህ ነው!" ብሎ -
ሰው ያልሆነ ፍጥረት - ካልነገረኝ በቀር።
============//==========
(በርናባስ ከበደ)
@getem
@getem
@gebriel_19
እስኪ ተጠየቁ...!
-
የዝንጀሮ መልኳ አስቀያሚ እንደሆን
በልሳን ብ'ነግራት ትደነግጥ ይሆን?
-
ስናወራ ሰምታ - ወፍ እንደምታምር
ፉጨቷን አቋርጣ - ትለን ይሆን "የምር??"
-
እህሳ?!.....
ታድያ የት ተለከፍን? ምን ነክቶን ነው እኛ?
ስለ አቋም መልካችን ...
እንዴት ባለው ልኬት - ሆንን እርግጠኛ??
.
የቱ ቡዳ በላን?
ምን ቀን ሰፈረብን? ተያዝን በመንፈስ
ለምን ተጠመድን?
ስለራስ በማዜም - ስለራስ በማልቀስ።
.
ቢያማልል ....
ቢያባብል...
ማር ቢሆን ቢጣፍጥ - ነገር በምሳሌ
ባለማመን የማምን -
ተጠራጣሪ ነኝ - እኔ በበኩሌ።
-
-
"ሔዋን እንደዚ ነች!"
"አዳም እንደዚ ነው!"
የሚል ጥቅስ ቢናኝ - አየሩን ቢሞላ
ማንንም አላምንም - ከእንግዲህ በኋላ!!
.
በቃ አላምንም ከቶ፣
ግርምቱን - ትዝብቱን ሳይጨምር - ሳያስቀር
"ሰው እንዲህ ነው!" ብሎ -
ሰው ያልሆነ ፍጥረት - ካልነገረኝ በቀር።
============//==========
(በርናባስ ከበደ)
@getem
@getem
@gebriel_19
👍3❤1
😔😔😔😔😔😔😔😔😔😔😔😔
ተማሪ ፂዮን አበበ ነሐሴ16ቀን 2011ዓ.ም ከምሽቱ 3:00 አካባቢ እንደወጣች አልተመለሰችም ። ፅዮን አበበ ለመጨረሻ ጊዜ የታየችው አዲስ አበባ ቀበና መድሃኒዓለም ቤተክርስቲያን አካባቢ ሲሆን የለበሰችዉ ልብስ ሰማያዊ ሱሪ እና ከላይ ኮፍያ ያለው ሹራብ ነበር ። በ እለቱ እናትዋ ስለሞተችባት በመሪር ሀዘን እራስዋን እራስዋን ማረጋጋት ስላቃታት እንደወጣች አልተመለሰችም። ፅዮን ምንም አይነት የአዕምሮ ህመም የሌለባት ሲሆን ያለችበትን የሚያውቅ በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች ደውለው ቢያሳውቁን ወሮታዉን በእግዚአብሔር ስም እንከፍላለን ቤተሰቦቹዋ።
0911815050
0920856595
ተማሪ ፂዮን አበበ ነሐሴ16ቀን 2011ዓ.ም ከምሽቱ 3:00 አካባቢ እንደወጣች አልተመለሰችም ። ፅዮን አበበ ለመጨረሻ ጊዜ የታየችው አዲስ አበባ ቀበና መድሃኒዓለም ቤተክርስቲያን አካባቢ ሲሆን የለበሰችዉ ልብስ ሰማያዊ ሱሪ እና ከላይ ኮፍያ ያለው ሹራብ ነበር ። በ እለቱ እናትዋ ስለሞተችባት በመሪር ሀዘን እራስዋን እራስዋን ማረጋጋት ስላቃታት እንደወጣች አልተመለሰችም። ፅዮን ምንም አይነት የአዕምሮ ህመም የሌለባት ሲሆን ያለችበትን የሚያውቅ በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች ደውለው ቢያሳውቁን ወሮታዉን በእግዚአብሔር ስም እንከፍላለን ቤተሰቦቹዋ።
0911815050
0920856595
ወድጄ ነው እንዴ??
(መንግስቱ መርሃፅዮን)
'ርቄ ስሸሸው
ጎዳና አሳብሮ ቀድሞ እየጠበቀኝ
ዋኝቼ ሳመልጠው
ቁልቁል እየሳበ መልሶ ሲደፍቀኝ
ከስርሽ መንግዬ-ነቅዬ ስጥልሽ
እንዳፈሉት ችግኝ-በውስጤ እየበዛሽ
ከቶም ፈውስሽ ላልሆን - ስትሆኚኝ ህመሜ
ስንጥቅ ልቤን ስጠቅም
በትዝታ መርፌ-በናፍቆት ቀምቅሜ
ስወድሽ......ስወድሽ.....ስወድሽ......ስ..................ወድሽ
አፍላነቴ ከስሞ-አጎበጠኝ እድሜ!
*
*
*
እንደኩፍኝ ድውይ "ወጣሽልኝ" ብዬ
ስለቴን ሳገባ
የአብሮነት ውሏችን "አከተመ!" እያልኩ
ከፍቺሽ ስጋባ
መች ለቀቀኝ ፍቅርሽ-መች ተፋታኝና
እንደቅል አበባ ሰርክ እየታደሰ
ይህው ሊያንገላታኝ -እንዳምና ካቻምና
ሽምጥ ጋልቦ ደርሶ ያዘኝ እንደገና!
*
*
*
ፍቅርሽን....
.........
በተመሳቀለ
እርጥብ እንጨት መስቀል
ጠርቄ ብሰቅለው
በድን እሱነቱን ከሲዖል ጉድጔድ ውስጥ
አርቄ ባኖረው
ልክ እንደመሲሁ
መቃብር ፈንቅሎ-ገልብጦ ወጣና
ይህው .....
ምስኪን ልቤን ጎበኘው እንደገና!
*
*
*
እኔ 'ምልሽ ውዴ?
ምን ያ'ረግልሻል 'ሳልወድሽ ብወድሽ'
እንደ ንጉስ ት'ዛዝ እዳ ሆነሽ ባዝልሽ
ምን ሊረባሽ ከቶ
ሰቀቀን ቢገርፈኝ "ርግማኔ" ሆነሽ?
*
*
*
ንገሪኛ ውዴ??
ፍላጎቴን ነጥቆ
ሎሌሽ ባደረገኝ-ዕኩይ ሆኖኝ ፍቅርሽ
እንደ ድል አድራጊ
ሃሴት ሊሆንልሽ ተወደድኩኝ ብለሽ??
*
*
*
እን.........ዴ....................!
እረ አትኩራሪበት- እረ ሀፍረት ይግባሽ??
ፈርዶብኝ ነው እንጂ
ወድጄ ነው እንዴ እኔ አንቺን ስወድሽ???
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
ቲሽ!
@getem
@getem
@gebriel_19
(መንግስቱ መርሃፅዮን)
'ርቄ ስሸሸው
ጎዳና አሳብሮ ቀድሞ እየጠበቀኝ
ዋኝቼ ሳመልጠው
ቁልቁል እየሳበ መልሶ ሲደፍቀኝ
ከስርሽ መንግዬ-ነቅዬ ስጥልሽ
እንዳፈሉት ችግኝ-በውስጤ እየበዛሽ
ከቶም ፈውስሽ ላልሆን - ስትሆኚኝ ህመሜ
ስንጥቅ ልቤን ስጠቅም
በትዝታ መርፌ-በናፍቆት ቀምቅሜ
ስወድሽ......ስወድሽ.....ስወድሽ......ስ..................ወድሽ
አፍላነቴ ከስሞ-አጎበጠኝ እድሜ!
*
*
*
እንደኩፍኝ ድውይ "ወጣሽልኝ" ብዬ
ስለቴን ሳገባ
የአብሮነት ውሏችን "አከተመ!" እያልኩ
ከፍቺሽ ስጋባ
መች ለቀቀኝ ፍቅርሽ-መች ተፋታኝና
እንደቅል አበባ ሰርክ እየታደሰ
ይህው ሊያንገላታኝ -እንዳምና ካቻምና
ሽምጥ ጋልቦ ደርሶ ያዘኝ እንደገና!
*
*
*
ፍቅርሽን....
.........
በተመሳቀለ
እርጥብ እንጨት መስቀል
ጠርቄ ብሰቅለው
በድን እሱነቱን ከሲዖል ጉድጔድ ውስጥ
አርቄ ባኖረው
ልክ እንደመሲሁ
መቃብር ፈንቅሎ-ገልብጦ ወጣና
ይህው .....
ምስኪን ልቤን ጎበኘው እንደገና!
*
*
*
እኔ 'ምልሽ ውዴ?
ምን ያ'ረግልሻል 'ሳልወድሽ ብወድሽ'
እንደ ንጉስ ት'ዛዝ እዳ ሆነሽ ባዝልሽ
ምን ሊረባሽ ከቶ
ሰቀቀን ቢገርፈኝ "ርግማኔ" ሆነሽ?
*
*
*
ንገሪኛ ውዴ??
ፍላጎቴን ነጥቆ
ሎሌሽ ባደረገኝ-ዕኩይ ሆኖኝ ፍቅርሽ
እንደ ድል አድራጊ
ሃሴት ሊሆንልሽ ተወደድኩኝ ብለሽ??
*
*
*
እን.........ዴ....................!
እረ አትኩራሪበት- እረ ሀፍረት ይግባሽ??
ፈርዶብኝ ነው እንጂ
ወድጄ ነው እንዴ እኔ አንቺን ስወድሽ???
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
*
ቲሽ!
@getem
@getem
@gebriel_19
ዋኔ! ሀኖሴ!!
።።።።።።።።፡፡
ነይ ትጥቄ!!
ነይ ስንቄ!!
ጎልያድ ጥላቴን፡ ዳዊት ሁነሽ ግደይ፣
በወንጭፍሽ መዳፍ፡ ጠጠር ሁኘ ልታይ፣
ነይ ዋኔ ሀኖሴ፣
ነይ ፋና ፋኖሴ፣
በፈገግታሽ ፀዳል፡ ኑሮ ቤቴ ይድመቅ፣
ባፍቅሮትሽ ብርታት፡ ጥላቻ ቃል ይድቀቅ፣
ወዶ ዘማች ልቤ፡ የልቡ ይሳካ፣
በብርታትሽ ይፅና፡ በግብርሽ ይመካ፣
ውበት ነሽ።
ኪነት ነሽ።
ከቅፍሽ ልጋመድ፣
ከልብሽ ልጣመድ፣
ከጉያሽ ልዛመድ፣
ነይ ቀኔ ንጋቴ!!
ነይ ሳቄ ንቃቴ!!
እንደንስር ጥልቅ አይቸ፡ የህይወትን ሚስጥር ልፍታ፣
እንደትንኝ ቅንጣት ሁኘ፡ ዝሆን ግዝፈትን ልርታ፣
የበደል ቃር ሳይሰንገኝ፡ በፍትሕ ቃልሽ ልቀጣ፣
ባደባባይ በሸንጎ ፊት፡ በፈገግታሽ ሽልም ልውጣ፣
ነይ ጉልበት ብርታቴ፣
ነይ ህይወት እውነቴ፣
እኛም ህዝብ እንሁን፡
እንደወርቅ እንቅለጥ፡ በ'ሳት እንፈተን፣
ሲቀጥፉን ሲገድሉን፡
ሺ ምንተ ሺ ሁነን፡ እንድንገኝ በዝተን፣
ነይ ሳቄ!!
ነይ ሐቄ!!
ወንጌል ፍቅርሽ ነድፎኝ፡ ከልሳኔ ታስረሽ፡
የህይወት ቃል ልስበክ፡ ልጓዝ በጎዳናሽ፡
ነይልኝ እምነቴ!!
ነይልኝ ህብስቴ!!
በወደድኩሽ መውደድ፡ የገረረው ይግራ፣
ባፈቀርኩሽ ፍቅር፡ ድፍርስ ዘመን ይጥራ፣
ዓለም ባንቺ ትዋብ፡ ምድር ባንቺ ትድመቅ፣
የመረረው ይጣፍጥ፡ እፎይታ ይደለቅ፣
ነይልኝ ንጋቴ፣
ነይልኝ ድምቀቴ!!
የኔ ቀን መች ነጋ፡
ከሚል ክፉ ውጋት፡ በብርሃን ስውሪኝ፣
አቋሜን ዘንግቸ፡
በነፈሰ እንዳልነፍስ፡ በቅፍሽ ደግፊኝ፣
ነይ ጌጤ...
ነይ ድምጤ...
ቀና ልበል በቅን፡
ፍክት እንደፀደይ፡ ኮምተር እንደኮሶ፣
መራር ቀኔ ያክትም፡
እኔም ቀን ይንጋልኝ፡ ፅልመት ተገርስሶ፣
ነይ ገዴ ዘመዴ!!
ነይ ጓዴ ጥማዴ!!
ያመመሽ ይመመኝ፡ ቁስልሽ ይሁን ቁስሌ፣
የሳቅሽውን ልሳቅ፡ ድልሽ ይሁን ድሌ፣
ነይ ወኔ ሀሞቴ!!
ነይ ቅኔ ቅኝቴ!!
ቀራንዬ ፍቅርሽ፡ መስቀል ሸክም ሁኖኝ፣
ጎለጎልታ ፍቅርሽ፡ በሰሌን ጠቅልሎኝ፣
ሞትን ድል አድርጌ፡ በህይወት እንድገኝ፣
ነይ...!!
።።።።።።
............
ይህ የእብዱ እስትንፋሰ ብእር ነው!!
ሸጌ ማግሰተ ሰኝት!!💚💛❤️
@getem
@getem
@balmbaras
።።።።።።።።፡፡
ነይ ትጥቄ!!
ነይ ስንቄ!!
ጎልያድ ጥላቴን፡ ዳዊት ሁነሽ ግደይ፣
በወንጭፍሽ መዳፍ፡ ጠጠር ሁኘ ልታይ፣
ነይ ዋኔ ሀኖሴ፣
ነይ ፋና ፋኖሴ፣
በፈገግታሽ ፀዳል፡ ኑሮ ቤቴ ይድመቅ፣
ባፍቅሮትሽ ብርታት፡ ጥላቻ ቃል ይድቀቅ፣
ወዶ ዘማች ልቤ፡ የልቡ ይሳካ፣
በብርታትሽ ይፅና፡ በግብርሽ ይመካ፣
ውበት ነሽ።
ኪነት ነሽ።
ከቅፍሽ ልጋመድ፣
ከልብሽ ልጣመድ፣
ከጉያሽ ልዛመድ፣
ነይ ቀኔ ንጋቴ!!
ነይ ሳቄ ንቃቴ!!
እንደንስር ጥልቅ አይቸ፡ የህይወትን ሚስጥር ልፍታ፣
እንደትንኝ ቅንጣት ሁኘ፡ ዝሆን ግዝፈትን ልርታ፣
የበደል ቃር ሳይሰንገኝ፡ በፍትሕ ቃልሽ ልቀጣ፣
ባደባባይ በሸንጎ ፊት፡ በፈገግታሽ ሽልም ልውጣ፣
ነይ ጉልበት ብርታቴ፣
ነይ ህይወት እውነቴ፣
እኛም ህዝብ እንሁን፡
እንደወርቅ እንቅለጥ፡ በ'ሳት እንፈተን፣
ሲቀጥፉን ሲገድሉን፡
ሺ ምንተ ሺ ሁነን፡ እንድንገኝ በዝተን፣
ነይ ሳቄ!!
ነይ ሐቄ!!
ወንጌል ፍቅርሽ ነድፎኝ፡ ከልሳኔ ታስረሽ፡
የህይወት ቃል ልስበክ፡ ልጓዝ በጎዳናሽ፡
ነይልኝ እምነቴ!!
ነይልኝ ህብስቴ!!
በወደድኩሽ መውደድ፡ የገረረው ይግራ፣
ባፈቀርኩሽ ፍቅር፡ ድፍርስ ዘመን ይጥራ፣
ዓለም ባንቺ ትዋብ፡ ምድር ባንቺ ትድመቅ፣
የመረረው ይጣፍጥ፡ እፎይታ ይደለቅ፣
ነይልኝ ንጋቴ፣
ነይልኝ ድምቀቴ!!
የኔ ቀን መች ነጋ፡
ከሚል ክፉ ውጋት፡ በብርሃን ስውሪኝ፣
አቋሜን ዘንግቸ፡
በነፈሰ እንዳልነፍስ፡ በቅፍሽ ደግፊኝ፣
ነይ ጌጤ...
ነይ ድምጤ...
ቀና ልበል በቅን፡
ፍክት እንደፀደይ፡ ኮምተር እንደኮሶ፣
መራር ቀኔ ያክትም፡
እኔም ቀን ይንጋልኝ፡ ፅልመት ተገርስሶ፣
ነይ ገዴ ዘመዴ!!
ነይ ጓዴ ጥማዴ!!
ያመመሽ ይመመኝ፡ ቁስልሽ ይሁን ቁስሌ፣
የሳቅሽውን ልሳቅ፡ ድልሽ ይሁን ድሌ፣
ነይ ወኔ ሀሞቴ!!
ነይ ቅኔ ቅኝቴ!!
ቀራንዬ ፍቅርሽ፡ መስቀል ሸክም ሁኖኝ፣
ጎለጎልታ ፍቅርሽ፡ በሰሌን ጠቅልሎኝ፣
ሞትን ድል አድርጌ፡ በህይወት እንድገኝ፣
ነይ...!!
።።።።።።
............
ይህ የእብዱ እስትንፋሰ ብእር ነው!!
ሸጌ ማግሰተ ሰኝት!!💚💛❤️
@getem
@getem
@balmbaras
👍1