ግጥም ብቻ 📘
67.6K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
ንግስቲቱ ጎንደር!!!!


ከጉግሳ ወሌ አገር፤ላዩን ቤጌምድር ሰሜንና ቋራ፤
ተገኘች ይሉኛል ፤
አንዲት ደማም ቆንጆ፤
ልክ እንደጣይቱ ልክ እንደታወበች ታሪክ የምትሰራ ።
በፋሲል ከተማ፤በጃንተከል ጥላ ፤በአርባ አራቱ ታቦት፤
እቴጌም ይወልዳል፤ ንግስትም ይወልዳል ይኸ ጎንደር ማለት።
በፍቅር ካልሆነ ፤
አቤት ሆይ እቴጌ፤ብለው ካልገበሩ እግር ከስር ሆነው፤
በጎንደሮች ቀየ፤
እምቢ ያሉ ጊዜ፤ ሞይዘር አምጡ ይላል ሴቱ አባወራ ነው ።
በፍስለታ ማርያም፤ ወይብላ ስትነግስ ሲከብር ታቦቱ፤
ለካ ተወልዳለች፤ የፋሲሎች ሰንደቅ ጎንደር ንግስቲቱ።
ከአርባ አይመታሽ ሃገር፤ከነ ደመቀ ወንዝ ጎንደር ተፈጥረሽ፤
መች ይረሳኝና፤
ነፍስ የሚዘውረው፤
ወልቃይትን አምጡ ጠለምትን መልሱ የሚለው ድምፅሽ፤
የተዋበች ቀለም፤የነ መነን ሰንደቅ ማርትሬዛ ነሽ ፤
ንግስቲቱ ጎንደር ፤ አሁንም አሁንም ፤እንኳን ተወለድሽ።

((( ጃ ኖ ))💚💛❤️

መልካም ልደት ጀግኒት !!!👑👑
@getem
@getem
@balmbaras
1
የት አውቅልሻለሁ!!!!!


አለማጣ ውየ ዞብል አቀናለሁ፤
በአማርኛ አናግሪኝ አናግርሻለሁ፤
አለበለዚያማ፤
የተውሶ ቋንቋ የት አውቅልሻለሁ።

(( ጃ ኖ ))💚💛❤️

@getem
@getem
@balmbaras
😁2🎉1
ትወጂኛለሽ!!!
(በላይ በቀለ ወያ)


.
.
.
እኔ እየፈራሁሽ፣ ልቤ እየደፈረሽ
እኔ እየናኩሽ ፣ ልቤ እያከበረሽ
እኔ እየጠላሁሽ ፣ ልቤ እያፈቀረሽ
ከራሴ ስጣላ...
እኖራለሁ እንጂ ፣ የልቤን ሀቅ ይዤ
አንድም ቀን አልፎልኝ....
ልቤን እንደልቤ ፣ አላውቅም አዝዤ፡፡
አንቺም ልክ እንደኔ...
ልብሽን እንደልብ ፣ ማዘዝ አትችይም
ልብሽ ይወደኛል ፣ ጠላሁህ ብትይም፡፡
ባትወጂኝም እንኳን...
የመጥላትሽ መጠን ፣ የቱን ያህል ቢያክል
አንቺን አላምንሽም ፣ ልብሽ ነው ትክክል፡፡
ት፡ወ፡ጂ፡ኛ፡ለ፡ሽ!!!

(በላይ በቀለ ወያ)

💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️

@getem
@getem
@getem
1👎1
ጡሃራ ሰንደቄ!!!!


የሸሆቼ ልጅ ነኝ የወሎ ደረሳ፤
ከመንገድ ዳር ቁሜ፤
ወተት የመሰለ ፤
ጡሃራ ሰንደቄን በእጄ የማነሳ።
አብሽር ለምትሉ ፤ ሰንደቄን አይታችሁ፤
ወተት የመሰለ፤
በረካና እንጀራ ጀሊሉ ይስጣችሁ ።

((( ጃ ኖ ))💚💛❤️

ሸጋ ጁምኣ!💚

@getem
@getem
@balmbaras
1😁1
#ብዙ_ተባዙ

ሠውን በመፍጠሩ እግዜር ሚጠቀመው
ሠውም በመፈጠር ከግዜር የሚያገኘው
አንዳች ነገር ባይኖር አንዳች ድብቅ ነገር
ምድሪቱን ለመሙላት ከብት ይበቃ ነበር
ኤፍሬም ስዩም

@getem
@getem
@getem
1
ግጥም ገጥሞ ገጥሞ መች ቀልቡ በረደ፤
ዱላውን ሊገጥም ጎንቢሶውን ታጥቆ ራያ ወረደ።

(( ጃ ኖ))💚💛❤️

@getem
@getem
@balmbaras
ተናፋቂው የፋና ብዕር 5ተኛ ዙር የጥበብ ምሽት በአዲስ ዓመት ዋዜማ ቅዳሜ ጷጉሜ 2/13/2011 ዓ/ም አመሻሽ 11:00 ሰዓት በዝዋይ ቱሪስት ሆቴል አዳራሽ ውስጥ
በዕለቱ
ስነ-ግጥም፣ወግ፣
መነባንብ
፣ዲስኩር፣
ሙዚቃ
ከሌሎች ማራኪ ዝግቶች ጋር
አዘጋጅ ፋና ብዕር
--

@tebeb_mereja
@tebeb_mereja
👎2
ያ ማዶ!!!!!!!!!!


ይኸው ይሰማኛል፤ ከወዲያኛው መንደር፤ ወዲያ ማዶ ጋራ፤
ግራ በገባው ህዝብ ፤
የተከበበችው ግራ ገብ ሃገሬ ድረሱልኝ ብላ ጩሃ ስትጣራ ።
የገዳይ ተገዳይ ሙሾ ያልተለያት ኢትዮጲያ ሃገሬ፤
ባዘን የጎበጠች ምንዱባን ሆናለች ይኸው እስከዛሬ፤
መልሶ መላልሶ፤
ያ የደም ታሪኳ ይኮሰኩሳታል እንደ አባ ጨጓሬ ።
ከሞት መቃብር ደጅ የገዳይ አስገዳይ ታሪክ የተማረ፤
በክፋት ብላክ ቦርድ ፤
አይኑ እስኪንቦዣቦዥ ፤
አቢዮት የሚሉት የደም ጠማሽ ፅህፈት ፊደል የቆጠረ፤
ይኸው ዛሬም ቆሟል፤
ወንድሙን ሊገድል የቃየልን ሳንጃ እያገነደረ ።
በመፈክር ብዛት፤
በርእዮት ግርግር ፤
ይመስለን ነበር ሃገር የሚቀና ጎተራ ሚሞላ፤
ይሆን መስሎን ነበር ፤
በእናቸንፋለን፤
በእናሸንፋለን፤ሸለቆ ሚደፈን በአጀብ በሽለላ፤
ለካስ ተራራ አለ ፤የትላንትናውን ኮረብታ ዳገቱን ከወጡ በዃላ ።
አዎን ተራራ አለ ፤
ከግማድ ጥላው ጋር አታልፍም እያለ ዳንኪራ ሚራገጥ፤
ለካስ እዚያ ማዶ ፤
ከዚያ ባሻጋሪ፤ ሌላ ተራራ አለ ተመለስ እያለ አንተው ላይ የሚያፈጥ ።
ግን አትመለስም፤
አታፈገፍግም ይቅር ተውት ብለህ እንዳምና ካቻምና ፤
ተራራ ሚያፈርሰው፤
ዳገት የሚንደው፤ የኤልያስ ቅባት የነ ካሌብ አዋጅ ካንተ ጋር ነውና ።

((( ጃ ኖ ))💚💛❤️



@getem
@getem
@balmbaras
የልብ ቅርፅ
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
ፍቅርን ያህል ነገር...
ተሸክሜ ስኖር ፣ በልቤ ትከሻ
"ቃል አጠረኝ" የሚል....
ቃል ካ'ፌ አይወጣም ፣ ላወድስሽ ስሻ።
........................................................
እንደውም ሳፈቅርሽ ፣ ቃል ነው የተረፈኝ
ሁሉ ያጥርብኛል.....
በልብሽ ቅርፅ ውስጥ ፣ መውደድሽ ሲያገዝፈኝ።
...............................................
ሳፈቅርሽ ይህ ሆነ...
ሰፊ ያልሁት አለም ፣ ባንድ እርምጃ አለቀ
ሳልሄደው ሚደክመኝ...
ተራራና ጋራው ፣ ከግሬ ስር ጠለቀ።
"ሩቅ" ያልሁት ሰማይ..
ሩቅ የሚመስለኝ ፣ ነካሁት በስንዝር
ጨረቃና ፀሀይ....
ከኮከብ ያንሳሉ ፣ ከፍቅርሽ ግዝፈት ስር።
.......................................
ሳፈቅርሽ ይህ ሆነ...
ንጉስን ከዙፋን ፣ ማርከው የሚያወርዱ
የሀያላንን አቅም ፣ በጥቅሻ ሚያርዱ
ቆነጃጅት ሴቶች ...
"ቃል አጠረኝ" በሚል ቃላት የተሞሉ
ከፍቅርሽ ግዝፈት ስር..
ቃል ተገኝቶላቸው ፣ "ፋንጋዎች" ተባሉ።
.........................................
ሳፈቅርሽ ይህ ሆነ...
"ቃል አጠረኝ "በሚል...
ባፍቃሪ አንደበት ፣ ቃል ተትረፈረፈ
ሁሉን አሳንሶ...
በልቡ ቅርፅ ውስጥ ፣ ፍቅሩን አገዘፈ
አለሙን ሰርዞ ፣ ፍቅሩን ብቻ ፃፈ!!!
..........................................
ሳፈቅርሽ ይህን አልሁ...
ፍቅርን ተሸክሞ ፣ የሚኖር ልቦና
ሁሉም ከፍቅርሽ ስር ፣ መሆኑን አውቅና
አንቺን ለማወደስ .፣..እኔም ቃል ያጥረኛል
"ቃል አጠረኝ "ማለት...
ቃል እንደሆነ ግን ፣
ፍቅርሽ ይነግረኛል!!!



@getem
@getem
@getem
2👍1
ለቅዳሚታችን
❤️❤️❤️



እንደ ላስታ ዳገት እንደላሊበላ ፤
ታቹን በሽምሸሃ ላዩን በብልባላ ፤
ልቤን ሰረቀችው፤
ላስታ ከበሩ ላይ ፤ አሸንድየ ብላ ።
ከቤተስኪያን ዳር ነው የልጅቱ ቤት ፤
አላፊና አግዳሚው ከሚያረግድበት ፤
እኔ ልሞት ሆነ ሁሉ እየሳማት ።
ከቄስ ጎበዜ አገር፤
ገነተ ማርያም ላይ፤ ልሳለም ወርጄ ፤
ላስታ ንግስ ቀረሁ፤
ቤዛ ኩሉ አለፈኝ ሸጋ ልጅ ወድጄ ።
እንደ ነአኩተላብ እንደላሊበላ ፤
ቤት ሰራች ይሉኛል ዲንጋዩን ፈልፍላ ፤
ዲንጋዩን ፈልፍላ የሰራችው ቤት ፤
አልባብ አልባብ ይላል፤ ማርያም ገብታበት ፤
ማርያም የገባችለት ፤ ስለቴ ሰመረ ፤
እንግዲህ መባዘን ፤ መንከራተት ቀረ ።
አሸንድየ አበባ ፤ አዝሎ መጣልሽ ፤
በዚህ ቀጭን ወገብ፤ በሚያምረው ባትሽ ፤
ላስታ ከበሩ ላይ ስትምነሸነሺ ፤
ድስትሽ ጦም አደረ ሳሳ ሞሰብሽ ፤
ባዶ ድስት ጥደሽ፤ ባዶ ቤት ይዘሽ ፤
ማነው የሚያገባሽ፤ ማነው የሚያጭሽ፤
የላስታው ጊወርጊስ፤
እሱ ይድረስልሽ እሱ ያግዝሽ።
በአመት አንድ ጊዜ፤
ሻደይ አገልድሜ ፤ አምሮብኝ ስወጣ ፤
እንኳንስ አባቴ ማርያም አትቆጣ ፤
ለሷ ነው እስክሳው ለሷ ነው ማርገዴ ፤
እመቤቴ ሳለች ምን ግዴ ምን ግዴ ።
ሻደይ ሻደይ ብየ ፤ ከቤቴ ገባሁኝ ፤
የማርያም ሙጌራ፤ ተጋግሮ አገኘሁኝ ፤
ያነን እየበላሁ ከቆላ እስከ ደጋ ፤
ክረምቱም አለፈ አዲስ አመት ነጋ ።

(( ጃ ኖ ))💚💛❤️

ሸጋ ሸጊቱ ቅዳሜ!💚

@getem
@getem
@balmbaras

ያቺ
አድዋ

አዳማ ነሐሴ 26

@tebeb_mereja
@tebeb_mereja
እንከን ላጣሽብኝ
----------------

በሰፌድ ላይ ቀመር
በ.....…ላሜዳ* ባየር
ግብሬን አበጥሮ ፥ ልብሽ እንዲቀጥረኝ
ሙያዬን መዝኖ ፥ አይንሽም እንዲያየኝ
ሽርጥ አገልድሜ ፥ እጅጉን ብለፋ
ጋገርራ ገብቼ ፥ ...ቡኮ ሊጥ ባሰፋ
እስቲበስል ብዬ
በትዝታ ቅርቃር ፥ አንገቴን ብደፋ
ተኝቶ ነው ብለሽ
የምጣዴን ክዳን ፥ ያለጊዜው ከፍተሽ
አይኑ የፈዘዘ ፥ …አፍለኛን አውጥተሽ
እኔን ለማባረር…
ምህኛት ብታጪ፥የእንጀራ'ይን ቆጠርሽ
ይሁና ከበጀሽ…
በማይመስል ህጸፅ ፥ መንገድ ከከጀለሽ
ከማይሳሳቱ
መላእክት ሰባእቱ
...ምስለ አሐዱን ከሆንሽ
እንግዲስ እኔው ነኝ…
እንደ ቀትር ጋኔል ፥ አንቺን ሳይ የምሸሽ
ይብላኝልኝና እኔ ምን ተዳዬ
የነጣ ነውና ፥ የራስ ቅል ጓዳዬ
የወጣ እንዳይገባ…
በአሚን መቀነት ፥ ታስሯል ህሊናዬ
፡፡፡፡፡፡፡
ካንቺ ዘንድ ከዋለው
ጅል መስሎ ጥበብን ፥ ከጉያሽ ካለበው
ውስጡ ሳይታወቅ ፥ ብክር ከተናቀው
ከጭምቱ ራሴ ፥ ከሰላው ሀሳቤ
ከ'ሊናዬ እልፍኝ ፥ በትረ ሙሴን ስቤ
እንደ ቀዩ ባህር…
እከፍልበታለው ፥ ..…ልብሽን ከልቤ
እንግዲስ ዳግማይ ፥ እጉያሽ መጥቼ
የተከለከለ እርምሽን ነክቼ
እንደ ብሉይ አካን፥እንዳይመታኝ ቅስፈት
ልቤን አስሪያለው
ኢያሱን ባስነባች ፥ ....በያሪኮ ግዝት
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
አሁን አቦልሽን
ቶና በረካሽን
ጨርሼ አከተምኩት
አዝመራው ሀሳቤን ፥ ውድማ በተንኩት
የሰላውን ማጭድ ፥ ከሰገባ ሳብኩት
እንደ ቅጠል በጣሽ…
ከልብሽ ቅርንጫፍ፥ተስፋዬን ቆረጥኩት
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ቢሆንም ቢሆንም...
ሆነሽኛልና ቆንጥጦ መካሪ
ላመስግንሽ እቱ ፥ እልፍ አመትን ኑሪ
ዮናስን በሆዱ…
ሦስት ቀን እንዳቆየ ፥ የተርሴስ አ'ንበሪ
አ'ርገሽዋልና…
ልቤን እንደልብሽ ፥ ተፍቶ አስተማሪ
.
« ሚኪ እንዳለ» @MMIKU

@getem
@getem
@getem
👍3
ብእሩን ቀለም መግቤ
ከብራና አጣጥሜ
ቃላትን ወረቀት ላይ ጥዬ
ጻፍኩኝ እንዲህ ብዬ

"ዝም" ብዬ
በቃ ዝም ዝም
ከፊደል ቢልቅም
ከሃሳብ ቢርቅም
መሻቴን ይገልጸው
እንደሆን ባላቅም
ከቃላት ውርታ
ሳይሻል አይቀርም
አንዳንዴ ዝምታ

(ካሳሁን ሀብታሙ)

@getem
@getem
@getem
👍1