ግጥም ብቻ 📘
67.6K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#የጨካኝ_ሰው_ጥበብ
-
ለለስላሳው እግሬ ፥ አለት አፍራሽ ጫማ
ለወስዋሳው ልቤ ፥ አፅናኝ ፋጨት ዜማ፣
ስበት ህጉን ሽሬ ፥ ባየር እስክንሳፈፍ
ሸ..ከ..ተ..ፍ! ....... ሸ..ከ..ተ..ፍ!!...
-
እንዲያ ሁኜ ስነጉድ ፥ ከራስ ጋ ውድድር
ከሩቅ ሲሮጥ ታየኝ ፥ አንዱ በባዶ እግር!
..... ወ.ይ.ኔ ... ሲ..ያ..ሳ..ዝ..ን!!
-
ወየው! .... ኧረ ወየው!
መከራን በመፍራት ፥ መከራ ገበየሁ
. እኔ እሱን እያየሁ!!
-
ካሁን አሁን እያልኩ ፥ ስሳቀቅ ስሰጋው
ድንጋይ እንዳይልጠው ፥ እሾህ እንዳይወጋው፣ ...
... ምፅ!
ለሟች ከንፈር መጣጭ ፥ ወዮልኝ ለራሴ
ከጉድጓድ ወድቄ ፥ ተ..ለ..ቀ..መ ጥርሴ!!!
-
-
ያኔ ነው የገባኝ
ምስጢር የተረዳኝ!
-
ከሩህሩሁ ይልቅ ፥ ጨካኝ መሰንበቱ
አለመራመጃው ፥ ሌላ አለማየቱ ፨
----------------//---------------
(በርናባስ ከበደ)

@getem
@getem
@getem
👍1