ግጥም ብቻ 📘
67.5K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
ታሪክማ በግድ እንሰራለን

(ቡሩክ ካሳሁን)

አያቶቻችን ሀገርን ከወራሪ ለመጠበቅ
ከጠላት ጋር ተከሳከሱ
ዘር ብሄር ሳይለዩ ደማቸውንም አፈሰሱ
እኛ ታሪክ መስራት ከብዶን ከአባቶቻችን ስላነስን
ወጉ እንዳይቀርብን በአያቶቻችን አፅም ተጫረስን፡፡


@getem
@getem
@burukassahun
በእሾህ መደገፊያ ከእሾህ መቀመጫ
ወግቶ ለመወጋት ይሄ ሁሉ ሩጫ
ምን ይሆን ነገሩ ምንድነው ሚስጥሩ?
መድሃኒት የሚያሻው ሰዉ ነው ወንበሩ?

@getem
@getem
@paappii

#ምህረት ደበበ
ለወዳጄ
ሰባት ጊዜም አይደል ፈተንኸኝ ኹለቴ
ከጀርባዬ ሳይሆን ተቀምጠህ ፊቴ
በሰባት ፈተና ከሚወደቅ በላይ
በሁለቱ ፈተናህ ተሽመድምጄ ተጣለኩ
ግና ምን ያደርጋል
ቃልህን አምናለው ነገም ዛሬም ብኖር፡፡


ነጽር እኁየ

@getem
@getem
@getem
የሀገሬን ቆዳ
በጂጊ በደቦ ፣ ዳር እስከ ዳር ገፈው ፣
በየቀጣናው ልክ ፣ አንዱን ቀረጣጥፈው ፣
ጊዜ ገባታው ላይ ፣ በቀን ጠፍር ጥፈው ፣
ደቤነት ወጥቷት ....
ለክልሎች ዘፈን ፣ ሰማሁ ስትመታ ፣
እልልታ በሚመስል ፣ በለቅሶ ስሞታ ።

((( ሙሀመድ ሙፍቲ )))💚💛

@getem
@getem
@balmbaras
ቀን በቀን ሲተካ
ያንቺ እንባ መፍሰስ ለሰው በይዋጥም
እመኚኝ ሀገሬ
ለቅሶሽ እየበዛም ባንቺ ተስፋ አልቆርጥም፡፡



መልካም ቀን የግጥም ብቻ ቤተሰቦች!!

@getem
@getem
@getem
መሰጠት ላያጎድል
ስስታም ማንነት በስጋ እያጠላ
ለሚያልፍ እሱነቱ
አለመጥገብ ክፉ ከነፍስ እያጣላ

ስንቱን ባየንባት
የኪራይ መኖሪያ የኮንትራት ዓለም
እመነኝ ወዳጄ
ደግነትን ያህል ሰብአዊነት የለም፡፡

((ልብ አልባው ገጣሚ))

@getem
@getem
@gebreil_19
#ፍኖተ_ፍቅር

እንጀምረው ፍቅርን እንቅመሰው ጣዕሙን
ከሰማይ የሚያደርስ እንጓዝ መንገዱን
እንውጣ እንውረድ
የፍቅር አቀበቱን
የፍቅር ቁልቁለቱን

ጥንድ ጥንድ ሆነው ጓዶቼን ሳያቸው
አእዋፋቱ ሁሉ አፍ ለአፍ ተጋጥመው
እጽዋቱ አዕዋሙ ባንድ ግንድ ተጣብቀው
ተፈጥሮን ሳስተውል ሁሉንም ሳያቸው...
ለካስ እውነት ኖሯል...
ያ ቸር ያ ደግ አምላክ ቃሉን መናገሩ
ያዳም ብሕትውና መክፋት ማስቸገሩ
ከሔዋን ውጭ ሕይወት እንደሬት መምረሩ
ለካስ እውነት ኖሯል...
አጥንቷን ካጥንቱ ደሟን ከደም ሥሩ
ከአዳም ሰውነት ሔዋንን መፍጠሩ

ተጠርተሻል ውዴ ከሽሽጉ ቤቴ
ነይና እንጋጠም ከጎድን አጥንቴ

(📝ል.ግ.ኢ)

@getem
@getem
@getem
///ከዛች ጢሻ ስር////

ከእለታት ባንዱ ቀን ከወንዙ ባሻገር
አንድ ወጣት ተማሪ በጠዋት ሲሻገር
ቤተስኪያን ስሞ ሊመለስ ያሰበዉ
ዉርጅብኝ ዱብዳ በድንገት ገጠመዉ።

በቤተስኪያን ዉስጥ እርሱን ያስተማሩት
የ ደብሩ አለቃ ሠዉን ሀሉ ያፈሩት
አገኛቸው እርሱ ወንዙ ዳር ተቀምጠው
ከአንዲት ኮረዳ ጋር አፍ ለ አፍ ገጥመዉ።

በድንጋጤ ላይ ሆኖ ለመደበቅ ሲፍጠረጠር
ከቆመበት ድንጋይ ላይ ወደ ዛፍ ዉስጥ ሲፈነጠር
ድንገት በመምሬ አይን ዉስጥ ገባ
ተማሪዉ ወደ ቁጥቋጦ ሲገባ።

ብልህ የነበረዉ መምሬ ስላልነበር የዋዛ
............ የልጁን ፍራቻ አይተዉ
ሊደልሉ ተነሱ በዛ በተማረ ለዛ
"ልጄ አንተ ብሩህ ነህ መለወጥ ምትሻ
ለማንም ካልነገርክ ያየኸዉን ከዚ ጢሻ
አሳድግሀለዉ ከቀዳማይ ወደ ካልዓይ
አሁን ከዚህ ጥፋ ግራ ቀኙን ሳታይ።"

ተማሪዉ ለጥቆ ማዉራቱን ቀጠለዉ
"መምሬ አይፍሩ ይሄ እኮ ቅንጣት ነዉ
ከዚህ የበለጠ ስንቱን አይቻለዉ።

የጋሽ ተምትሜ ሚስት እትዬ በለጡ
ከዛ ማር ቆራጭ ጋር እዚህ እየመጡ
ሲዲሩ እየዋሉ ሲዳሩ እያመሹ
ሰዉ እንዳያያቸው ሲፈሩ ሲሸሹ
እኔ እንደ ልማዴ ስሄድ ቤተስኪያን ልስም
እዚህ ቁጭ ብለዉ አይን ለአይን ግጥም።

ብቻ እኔን አያርግህ ያላሉኝስ የለም
ፊደል እንድቆጥር እንዳዉቅ ይህን አለም
ተማሪ ቤት ወስደዉ ሊያስተምሩኝ
እንዳልናገር ቃል አስገቡኝ ።

ይቺ ብቻ መስሎት እንዳይዘናጉ
የራሶ ባለቤት እማማ መፅአጉ
ከከንቲባው ጋራ እዚህ እየተቀመጡ
የቤቱን ወጣወጥ ዳቦ እና እንጀራ ከዚህ እያመጡ
............... ሲበሉ ሲጠጡ
ያዉ እንደ ልማዴ ከወንዙ ስሻገር
ሚስቶትን አየኋት ምሳ እቃ ስታስር።

እርሶ እንደማይበሉ ጠንቅቄ ስለማዉቅ
በጥርጣሬ ዉስጥ ሄድኩኝ ተከትያት
የፈራሁት ደርሶ ከዚሁ አገኘኋት
ከከንቲባው ጋራ ሲጓረሱ ያዝኳት።

ሚስቷም ያዩኝ ጊዜ ጠርተዉ አናገሩኝ
ይህንን ዉርደቷን ለሰው ካልነገርኩኝ
አስር ሽልንግ ሙሉ ሊሰጡ ማሉልኝ።

ብቻ ግን መምሬ ፍፁሙን አይፍሩ
ከዚች ኮረዳ ጋር ከጢሻዉ ሲዳሩ
ያየሁትን ሁሉ እንዳለ ሆኜ
እኔ እኖራለዉ በዉስጤ ቀብሬ።

ልጅ ሞሌ

@getem
@getem
@getem
ሙዚቃ ጥይቴ !!!!!


ክፋት ደመና ነው፤
እንደሃምሌ ሰማይ በነጋ በጠባ ሞት ያረዘርዛል ፤
ጥላቻ መርዝ ነው፤
የደግነትን ክንድ በሸር እያቦካ በቂም ይደልዛል ።


አለም በጨለማ፤ በቁር ስትታሰር ሲጨፈግግ ፊቷ ፤
ፍቅር ለመቃረም፤ ወኔዋ ሲከዳት ሲደክም ጉልበቷ፤
ፍቅርን ለመተረት ፤ መውደድን ለማውጋት ሲዝግ አንደበቷ፤
ይህች የኛ ህይወት ፤
ሃኪሟ ማን ይሆን ፍቱን መድሃኒቷ ??
የክፋት ወታደር ፤
የምቀኛ ተኳሽ ፤የቂም በቀል አንጋች ፤
የመጠላለፍ ጓድ ፤
የእንግደል የእናጥፋ ፤ የእነ እንበለው ዘማች ።
በክፋት ነፍጣቸው ፤
በንፁህ አለም ላይ የጨለማን ባሩድ ተግተው እየረጩ ፤
በህፃናት ስቃይ በእናቶች እንባ ላይ ጠግበው እያፏጩ፤
በዚህ ድንጋዜያቸው ፤
በክፋት መድፋቸው እየደነዘዘ ትውልድና ዘመን ጠፍቶ ሳያበቃ ፤
ይለሰልስ እንደሁ የገረረው ህይወት ያዳም ልጅ ሰቆቃ ፤
ዜማየን ልተኩስ ፤
ቅኔየን ላቀባብል እንደ ጀግና ሞይዘር እንደጦር ባዙቃ ፤
ናልኝማ ጊታር እምቡም እምቡም በል ቅኝትህን አንቃ ፤
በዝማሬ ጥይት ተኩሼ ልግደለው ሞትን በሙዚቃ ።

((( ጃ ኖ )))💚💛

@getem
@getem
@balmbaras
እናተ በውጪ የምትኖሩ ወገኖቼ በሙሉ ምናልባት በዚህ ፈተና በተሞላባት አለም ውስጥ ለራስ እንኳን መኖር በከበደበት ጊዜ ላይ ሰውን ማስጀገር በጣም ከባድ ነው እኔ ግን ልጄ የምታዬት ነገ ተምራልኝ ትጦረኛለች ስል 2 ኩላሊቶ ፌሌ አድርጎ ከአልጋ ላይ ጣላት እኔም ምንም ስራ የሌለኝ በምኔ ላሳክማት
ልጄ #የነገ ተስፋዬን
ልጄ #ጦሪዬን
ልጄ #አለሜን
ልጄ #መመኪያዬን
#አድኑልኝ #እርዱኝ #አበርቱኝ
ሁላችሁን በየ እምነታችሁ ለምታደርጉልኝ ነገር ሁሉ ፈጣሪ ብድራችሁን ይከፈላችሁ ከእነደዚ አይነት ሰቀቀን እናተንም ልጆቻችሁንም ይጠብቃቹ
አባቷ አቶ እሸቱ አበበ
አድራሻ
0913908438 አባቷ አቶ እሸቱ አበበ
account number
👉1000238917933 እሸቱ አበበ
_ረቡኒ_________

ከማውራት ያለፈ ተግባሩን የሚያሳይ
ከስሜት እርካታ ከዳንስ ከዝላይ
ለእውነት እየኖረ ሀሰትን ሸንግሎ ከልቡ 'ሚሰቃይ
ልብወለድ ያልሆነ ተውኔታዊ ሀሳብ መፅሐፈ ግላጭ የምናብ ነዋሪ
ለገንዘብ የማይኖር በእምነቱ የፀና በአምላኩ የታመነ እጅጉን አክራሪ
ሆኜ ለመገኘት ሆኖ የሚያሳየኝ ሀቀኛ ትክክል የፍቅር አፍቃሪ
አሁንስ ናፈቀኝ የእውነት ረቡኒ
ተፃፈ
21/09/08
አብርሃም እንዳለ ገዳ

@getem
@getem
@getem
👍1
ሀያል ፍቅር.2

(ቡሩክ ካሳሁን)

ያፈቀረ ጊዜ እውቀትና ምክንያት ከውስጡ እራቁ
ታምር አማኝ ሆነ የዝግመተ ለውጥ አስተማሪ ሊቁ
ባ”ንዳች ሀይል ተገፍታ ትመጣ ይሆናል በውስጡ እያለ
ከቤተስኪያን ሄዶ ዣንጥላ ተሳለ!!!



@getem
@getem
@burukassahun
ዮዲት መኮንን(ናኒ)

(አይነጋልሽም ወይ)
ሌሊትሽ ረዝሞ ንጋትሽን ሳናይ
በይነጋል ተስፋ ሰማይ ሰማይ ስናይ
ሊነጋ ሲል ይጨልማል እያልን ስንተርት
ወራቶች አልፈውን ስንጠብቅ አመታት

ይኸው እኛም አለን አንቺም እንደጨለምሽ
እንኳንስ ሊነጋ ጠፍተው ክዋክብትሽ
ኩራዝ የሚያበራ ጠፍቶ ከልጆችሽ
ወጠ ሰሪ ሳይሆን አማሳይ በዝቶብሽ
ይኸው እኛም አለን አንቺም እንደጨለምሽ

የቃል ኪዳን ሀገር መሆንሽ ተረስቶን
እኔ እኔ ስንል እኛ ማለት ትተን
አንድ ማዕድ ላይ መቅረቡ ተስኖን
ይኸው ዛሬም አለን እንደተበታተን

ወንዙ ሳይደርቅብን እህሉ ሳይጠፋን
በረሀብ አልቀናል
በጥማት ደርቀናል
ቀድቶ የመጠጣት ብልሀቱ እየጠፋን

ይኸው እኛም አለን አንድ መሆን አቅቶን
የአቤል እና ቃዬል ታሪክ እየደገምን
ወንድም በወንድሙ መሳሪያ እያነሳ
ልጅም በአ'ባቱ ላይ ሽቅብ እየተነሳ
አለን እንላለን
ሀገሬ እጆቿን ለግዜር እስክታነሳ

አለን እንላለን ባምላክ ላይ ተማምነን
ነገ አዲስ ቀን ነው የሚል ተ ፋ ይዘን
ሊነጋ ሲል ይጨልማል የሚል ቅኔ ዘርፈን
ሰምና ወርቅ ስንል ዘመን እያስቆጠርን

ይኸው እኛም አለን አንቺም እንደጨለምሽ
እንደጨለመብን እንደጨለመብሽ

@getem
@getem
@getem
👍1
//የእግዜር ስዕል//

እንግዲህ ይታዩኛል
የመኖርን አክሊል አስኬማዋን ደፍተው
በ'ልፍ ማርያም ማሪያት
በእግዜ'ር ኪነ-ጥበብ ከማህፀን ተገፍተው
በአፍንጫቸው ስንጥር
የህይወትን ጣዕም መዓዛ ሊያሸቱ
ከተጋረደ ዓለም
ወደ ገሀድ ዓለም ድንገት ሲከሠቱ
የፈጠራቸውን በእምባ እያባበሉ
ከዚህ ርካሽ ዓለም አታምጣን የሚሉ
አልቃሻ ህፃናት እዚያ ይሠማሉ
ደግሞም ይታዩኛል
የውዲቷን መሬት መዓዛ እውነቷን አሸተትን ብለው
ከውሀ ከእሳቱ በእኩል ተማምለው
የምድር አተካራ ውሉ ሳይገባቸው
ስጋ ከነፍስ ጋር እኩል ፈትኗቸው
ሲሆን ስጋን ስለማትረፍ ነፍስን የመከቱ
አሊያም ነፍስን ስለመታደግ በሀይል የዘመቱ
ዓለም ሆይ ጣዕምሽን
ምድር ሆይ ለዛሽን
አያሳጣን ብለው
ለዳንኪራሽ ሲመት
ለዋዜማሽ ቁመት
ከሲመትሽ ወዲያ ትችትና ጩኸት

ማዕረግና ክብር ዕድገት ተሠጧቸው
የእድሜ ነበልባሉ እሳት የፈጃቸው
ደግሞም የጭንቁ'ለት ነጠላ አገልድመው
ልብን ከፀሎት ጋር እኩል አሳርገው
አቤቱ የሚሉ
ፍፃሜ በሌለው ጠመዝማዛ መንገድ
ነፍስን ወይም ስጋን አንዱን ለመነገድ
ባገኙት አውድማ የሚንጠባጠቡ
ፅድቅና ኩነኔን እኩል የሚጣቡ
ቡሩካን ነን ባዮች
የራስ ሸንጎ ዳኛ በዳይ ተበዳዮች
የፍጥረት አንበሳ የፍጥረት ተባዮች
ህይወት ነን የሚሉ እነሱ ራሳቸው
ጥበብና መጥበብ በአንድ ተሠጥቷቸው
ሰብዕናን ሊዳኙ መዝገብ የጠፋቸው
የእሳት ልጅ እሳቶች
የእሳት ልጅ አመዶች
ከእቶን የፈለቁ ነበልባል ነዲዶች
ከሳሚ መብረቆች
ማዕረግ ተሸልመው ህዝብ ሚሸልቱ
ቃላትን ሸቅጠው ሀገር የሚሸጡ
ምንምን ታቅፈው ከምንም አጋማጅ
መልዓክት ነን ባዮች የነ አሽቆልቁል ወዳጅ
አመፅና ድጋፍ እያስተባበሉ ይዜያዜሙብኛል
በመረዙት ድንጋይ መንገድ ሲያበጃጁ ከሩቅ ይታዩኛል
ደግሞም በዚያ ግድም

ገንዘብን በሀያ
ልብን በአርባ እያሉ ሲተርቱ ሠምቶ
በድፍን አርባ ዓመት አርባ ልብ ገዝቶ
"አቤት የኔ ጌታ ምኒሽሩ ጓንዴ
ጠላት አብረክራኪ ጠላት አሰግዴ"
ተብሎ ተዘፍኖለት
ተብሎ ተዚሞለት
ጀግንነቱን ትቶ
ከጓንዴው ተኳርፎ ከሀይሉ ተጣልቶ
ቆፈን ባየለበት
ቀጭን ኩታ ጥሎ ሀሳብ ሲያገለድም
ልብ ግዛ ባሉት
ዕልፍ ሀሳብ ገዝቶ ሲያዘግም ሲያገድም
ሀሳብ ሲቀጣጥል ሀሳብ ሲደመድም
አንዱን እየካበ አንዳንዱን ሲያፈርስ
በአንደኛው ሲባረክ በሌላው ሲረክስ
ደግሞ እዚች ከተማ እዚች አደባባይ
አርባ ነሽ ያሏትን ያችን ገናዥ እውነት
በጩኸት ሊያደባይ
ይሄ አጉል አፍላነት ፈቶ የለቀቀው
በግማሽ እድሜው ልክነት የራቀው
ጎረምሳ ይሉት ጎልማሳ
መልካ መልኩን ለማሸነፍ ቁንጅናውን ድል ሊነሳ
መስተዋት ፊት ቆሞ
እንደ እናቶች ገንቦ ወደ ምድር ዘሞ
"ወይ ውበት" እያለ በመልኩ ተደሞ
በአቋሙ ተገርሞ
ወዲህና ወዲያ ቀረብ ራቅ እያለ
አርባ ዓመት ነህ ሲሉት አስራ ስምንት ያለ
አዎ "ያ" ጎረምሳ ማለቴ ጎልማሳ
አቁማዳ ቦርጩን የእኩሊት ቀንፎ
ለውበት ምላሶች አጓጉል ተነድፎ
ውበት ያሸነፈው
ውበት የገረፈው
መስተዋት ፊት ቆሞ ለጉድ ሲሽቀረቀር
ለጉድ ሲጭበረበር
ልቡን ጥቃት ገባው ድንገት ተሸበረ
ያመሻሿ ቀለም የሚፈራት ሽበት በቅላበት ነበረ
ለጎሪጥ አይቷታል
በውጭም በውስጥም እኩል ረግሟታል
ታዲያ
እንዲያ ሲቅበጠበጥ እንዲያ ሲብሠለሠል
ልቡን ፍርሀት ገባው
ማርጀቱን ተረዳው
ግን እኮ....
እዛ የ'ሡ ቢጤ ቢሮ ላይ ቁጭ ያለው
ሺበት ያልታደለው
ሽበት ያመለጠው
እድሜና እውቀቱ
ልክ እንደ መቅቢያ ቅል ፀጉሩን የመለጠው
እግዜ'ሩ አዝኖለት
ገንዘብ እና እድሜዉን ፊደል አስቆጥሮት
ፊደል አስከብሮት
አዲሱ ሚኒስቴር ከአዳዲስ ኮረዶች በአንድነት ደምሮት
ቢሮ ቁጭ ብሎ ሩቅ ተመሥጦ
ከአዕላፍ ሰነድ ውስጥ
የሴቶችን ቁጥር መዝገብ አገላብጦ
ለእንኮይ ልጃገረድ ሙሉ ልቡን ሰጥቶ
ስንቱን ሽማግሌ
እንደ ጌሾ ብቅል ቢሮው ላይ አስጥቶ
ሲያላግጥ የኖረ "ያ" ብኩን ጎልማሳ
ስላ'ገር ስለ ሚስት ስለ ሴት ተጨንቆ
በአስመሳይነት ላይ ልቡ ተጨማልቆ
ጊዜ የመሸበት
ጊዜ ያረጠበት
አዎ ይታዩኛል
በስዕል ሸራ ላይ
ያ'ንድ ሠዓሊ እጅ ያቀናበራቸው
ህብረ ቀለም ዘርቶ
በሰውነት ዙፋን ሰው የመሆን ጥበብ ያጎናጸፋቸው
ስዕል ላለመባል
ደብዝዘው ሊጠፉ ከሸራ 'ሚላፉ
ሰርክ እንጥፋ ባዮች
የጥፋት እንቢልታ መለከት 'ሚነፉ
ደግሞም
ለሸራው መጠንከር ጉልበት ያነገሱ
ምርኩዝነት ሽተው ፍቅር የደገሱ
አዎ ይታዩኛል
ሀገር ማለት ሸራ ሠዓሊው ፈጣሪ
ስዕሏ ህዝቤ ነው ቀለም ኑሮ ኗሪ
ከዚህች ሠፊ ሸራ ቀርቦ ላስተዋለ
በስዕሉ ግርጌ እግዜሩ ፊርማ ላይ እንዲህ የሚል አለ
"ህያው በሆነ ቃል
በጉራማይሌ ቅብ የተጠበብኩባት
ይችን የኔን ሸራ
በመለኮታዊ ጥበቤ የሳልኳት
ያረጀች መስሏቸው
ያረጁ ጠቢባን ቢያስቡም ሊያድሷት
ሺህ ቢያደበዝዟት
ልፋት ነው ‘ምሳቸው
ድካም ነው ግብራቸው
እውነት እላችኋለሁ
ሰማይ ምድር ይለፍ ህያው ነው ቃሌ
የአዳኞች መዳኛ
የአጥፊወች መጥፊያ ናት በሷ ላይ ነው ሀይሌ!!!”

ግንቦት 01-2011 ዓ.ም
ባህር ዳር - ኢትዮጵያ
በጋሻዬ ንጉሴ(ታመነ)


@getem
@getem
@getem